Friday, August 19, 2016

በህወሃት/ኢህአዴግ ባለቤትነት የሚተዳደረው ፋና በግል ድርጅት ስም የንግድ ቴሌቪዥን ፈቃድ ተሰጠው

ኢሳት (ነሃሴ 13 ፥ 20108)
የህወሃት የግል ንብረት የሆነው ሬዲዮ ፋና በግል ድርጅት ስም የመጀመሪያን የንግድ ቴሌቪዥን ስርጭት ፈቃድ ተሰጠው። 
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን የቴልቪዥን ፍቃድ የመስጠት ስልጣን የተሰጠው ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ለማንም የግል ድርጅት ፍቃድ ሳይሰጥ ቆይቷል። 
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባለፉት ጊዚያቶች ይፋ እንዳደረገው ከሆነ፣ የግል ንግድ ቴሌቪዥን ስርጭት ለመጀመር ጥያቄ ያቀረቡት የህወሃት ኢህአዴግ ኩባንያዎች የሆኑት ሬዲዮ ፋና፣ ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከልና ድምጸ ወያኔ መሆናቸው ታውቋል። 

ከእነዚህ የፓርቲ ንብረት የሆኑት ድርጅቶች ውስጥ የመጀመሪያውን የግል ቴለቪዥን ፍቃድ ከብሮድካስቲንግ ባለስልጣን ሬዲዮ ፋና እንደተሰጠው የገለጹት የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ወልዱ ይመስል፣ ለሰራተኛውና ፍቃዱን ሲጠብቁ ለነበሩ ሁሉ የደስታ መግለጫ አውጥተዋል። “ በሃገራችን የሚዲያ ታሪክ ውስጥ የግል ቴለኢቪዥን ሲፈቀድ የመጀመሪያ ተጠቃሚ ሬዲዮ ፋና መሆኑ ድንቅ ዜና ነው” በማለት የገለጹት አቶ ወልዱ ይመስል በቅርብ ጊዜ ስርጭት እንደሚጀምሩ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጥእን ፍቃድ የገኘው ሬዲዮ ፋና፣ እንዲሁም ፍቃድ በመጠባባቅ ላይ ያሉት ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከልና ድምፀ ዋያኔ ከህወሃት/ኢህአዴግ ቀጥተኛ ድጋፍ የሚያገኙ ሲሆን፣ የአራቱም ድርጅቶች ስራአስኪያጆች የህወሃት/ኢህአዴግ አመራሮች መሆናቸው ታውቋል።

No comments:

Post a Comment