Friday, August 5, 2016

ባህርዳር የሚገኘው የአቶ ካሳ ተክለብርሃን ቤት በድንጋይ እየተደበደበ ነው ተባለ

ኢሳት (ሃምሌ 29 ፥ 2008)

የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጊዜው ያለፈበትና ምላሽ ያገኘ መሬቱም የትግራይ ነው በማለት መግለጫ የሰጡት የአቶ ካሳ ተክለብርሃን ቤት በድንጋይ እየተደበደበ ነው።
የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት፣ ባህርዳር ከተማ የሚገኘው የአቶ ካሳ ተክለብርሃን ባለሁለት ፎቅ መኖሪያ ቤት መደብደብ የጀመረው አርብ ምሽት ሲሆን፣ ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በድንጋይ እየተደበደበ ይገኛል። ተቃውሞው በከተማዋ እየሰፋ መገኘቱንም መረዳት ተችሏል።

የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትርና የብዓዴን ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ካሳ ተክለብርሃን ባለሁለት ፎቅ መኖሪያ ቤታቸውን አከራይተው መኖሪያቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ቢሆንም የከተማዋ ወጣቶች ለተቃውሞ መግለጫ የባለስልጣኑን ንብረት በመደብደብ ላይ መሆናቸው ተመልክቷል።
አቶ ካሳ ተክለብርሃን በሳምንቱ አጋማሽ ወልቃይት የትግሬ ነው በማለት ከውጭ ሃገር ለሄዱ ኢትዮጵያውያን መኖራቸው ሲታወስ፣ ከጠ/ሚኒስቴር ሃይለማሪያም ደሳለኝም ጥያቄው ተመልሷል በማለት መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።
ይህ የባለስልጣናቱ መግለጫ በጎንደር ቁጣ እንደቀሰቀሰና ተቃውሞ እንዲያገረሽ አድርጓል። የፊታችን ዕሁድ በባህርዳር ለሚካሄደው ተቃውሞ ዝግጅት መጠናቀቁምንም አስተባባሪዎች በመግለፅ ላይ ናቸው።

No comments:

Post a Comment