Friday, August 5, 2016

በፎገራ ወረዳ የሚገኙ ስምንት ቀበሌዎች በጎርፍ አደጋ ተጠቁ፡፡

ሐምሌ  ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ጎንደር በ2 ቢሊዮን 400 ሚሊዮን ብር በመገንባት ላይ ያለው ርብ ግድብ ከመፍረሱ ጋር ተያይዞ ከ17 በላይ ሰዎች መሞታቸው እንዲሁም ከ60 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ጉዳት ከደረሰባቸው በሁዋላ፣ የግድቡ ውሃ በፎገራ ወረዳ የሚገኙ ስምንት ቀበሌዎችን ማጥለቅለቁ ታውቋል፡፡በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች ወደ መንገድ ዳርና ወደተራራ ቦታዎች በመሄድ ለመስፈር ሙከራ እያደረጉ ነው።

ግድቡ በ4 አመታት ይጠናቀቃል ተብሎ የተጀመረ ቢሆንም፣ ከ8 አመታት በሁዋላም ግንባታው ፈቅ አላለም።

No comments:

Post a Comment