Friday, August 5, 2016

የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ሰራተኞች ተቃውሞ እያሰሙ ነው

ሐምሌ  ፳፱ ( ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) አስተዳደር ያለሰራተኞቹ ፈቃድ ለአባይ ግድብ በሚል የአንድ ወር ደሞዛቸውን  ከነሐሴ ጀምሮ እንደሚቆርጥ ማስታወቁን ተከትሎ ሰራተኞቹ ተቃውሞውአቸውን የገለጹ ሲሆን፣ የሰራተኛው ተቃውሞ ያስፈራው አስተዳደሩ ውሳኔውን ለሚቀጥለው ወር መተላለፉን አስታውቋል።

ሰራተኞች ውሳኔውን አንቀበለም በማለታቸው ደሞዛቸው የታገደ ሲሆን በዚህም ምክንያት  ለከፍተኛ ችግር ተዳርገው ይገኛሉ፡፡ ሰራተኞቹ  እኛ የምናዋጣው ከምናገኘው ጋር ተመጣጣኝ አይደለም በማለታቸው ከፍተኛ አለመግባባት የተፈጠረ ሲሆን የኮርፖሬሽኑ ስራ በተቃውሞው ምክንያት መቆሙን ምንጮች ገልጸዋል።
በጄ/ል ክንፈ ዳኘው የሚመራው የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ከሰራተኞቹ እንዲህ አይነት ጠንከር ያለ ተቃውሞ ሲያጋጥመው ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሎአል።

No comments:

Post a Comment