Monday, August 22, 2016

በአውስትራሊያ ለኢሳት ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተካሄደ

ኢሳት (ነሃሴ 16 ፥2008)
ነዋሪነታቸው በአውስትራሊያ ሲድኒ ከተማና አካባቢዋ የሆነ ኢትዮጵያውያን የኢሳትን ስድስተኛ አመት የምስረታ በዓል በማስመልከት በሳምንቱ መገባደጃ ቅዳሜ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አካሄዱ።
በአውስትራሊያ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች በመካሄድ ላይ ያለው የዝግጅት አካል በሆነው የሲድኒው 6ኛ አመት የኢሳት የምስረታ ዝግጅት በርካታ ኢትዮጵያውያን በመታደም ለኢሳት ያላቸውን ድጋፍ በተለያዩ መልክ መግለጻቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። 
በዚሁ የሲድኒ ዝግጅት ኢሳትን ለመደገፍ 35 ሺ ዶላር አካባቢ መሰብሰቡንና ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በክብር እንግድነት በመገኘት ከታዳሚው ጋር ኢሳትን በተመለከተ ውይይት አካሄዷል።

No comments:

Post a Comment