Thursday, July 24, 2014

ከፍተኛ ድብደባ የተፈጸመባት ወይዘሪት ወይንሸት ሞላ በድጋሜ ተቀጠረች

ኢሳት ዜና :-ባለፈው አርብ የኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች በሙስሊም ኢትዮጵያውያውያን ላይ ያደረሱትን ኢ ሰበአዊ እርምጃ ተከትሎ በአካባቢው ስትንቀሳቀስ ተገንታለች በሚል ሰበብ የተያዘቸው የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክርቤትና የሴቶችጉዳይ አባል ወይዘሪት ወይንሸት ሞላ ለሐምሌ 24 ቀን 2006 ዓ.ም በድጋሜ ተቀጠራለች፡፡

ወይንሸትጭንቅላቷ አካባቢ የተመታች ሲሆንእጇም በፋሻ እንደታሰረበስፍራው የነበሩ ጓደኞቿ ለኢሳት ገልጸዋል።

ችሎቱን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት ካቀኑት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መካከል አቤልኤፍሬም በፖሊሶች መወሰዱ ታውቋል። ችሎቱን ለመከተታል የተገኘችው የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነችው እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፖሊሶቹ ችሎቱን ለመከታተል በተገኙት ሰዎች ላይ ይናገሩ የነበሩት ንግግር ” ከፖሊስ የማይጠበቅ” መሆኑን ተናግራለች። ኢህአዴግ እያወሰደ ያለው እርምጃ፣ አገዛዙ የመጨረሻ እድሜው ላይ መገኘቱን እንደሚያሳይም አክላ ገልጻለች

No comments:

Post a Comment