Friday, July 25, 2014

ሁለት ከአማራው ክልል በመጡ የደህነንት የበታች ሃላፊዎች በአቶ ኢሳይያስ ጠባቂዎች መገደላቸው ተዘገበ

ምኒልክ ሳልሳዊ

ባለፈው ማክሰኞ ከምሽት ጀምሮ ቦሌ መስመር ወሎ ሰፈር ከአይቤክ ሆቴል ፊትለፊት ገባ ብሎ ከሚገኘው የደህንነት ቢሮ ውስጥ በተደረገ ስብሰባ ላይ በተፈጠረ የፖለቲካ አለመግባባት ከአቶ ኢሳያስ ወ/ጊ ጠባቂዎች በተተኮሱ ጥይቶች ሁለት ከአማራው ክልል በመጡ የደህንነት የበታች ሃላፊዎች ላይ ግድያ መፈጸሙን ታውቋል።

በአማራው ክልል ያሉ እና በህግ በተመዘገቡ ፓርቲዎች ሽፋን የህገወጥ ዲያስፖራ ፓርቲዎችን አላማ የሚያራምዱ የተቃዋሚ አመራሮች ላይ ከምርጫው ቀደም ብሎ ሊወሰድ ስለሚገባው እርምጃ ለመወያየት የተሰበሰበው የደህንነት ጓድ በስብሰባው ወቅት ከፍተኛ አለመግባባት ፈጥሮ እንደነበር የታወቀ ሲሆን በወቅቱም ከአዲስ አበባ ከ13 አመት በፊት ተመልምለው ወደ አማራው ክልል የተላኩት በክልሉ ምስጢራዊ የሆኑ የግድያ እና የአፈና እንዲሁም የስለላ መመሪያዎችን በመቀበል ለጽጥታ ሃይሎች በማስተላለፍ ሲያስፈጽሙ እና ሲፈጽሙ የነበሩ እና በደህንነት ኮድ ስማቸው (አለልኝ እና ብቸናው) የተባሉ የደህንነት የበታች ሹሞች እዛው ስብሰባው መሃል በጸጸት እና በብሶት በቁጣ የተሞላ ጠንካራ ጥያቄዎች በማቅረባቸው በተፈጠረ አለመግባባት የማያዳግም እርምጃ እንደተወሰደባቸው ታውቋል።


የሕወሓት የደህንነት ከፍተኛ ሹሞች ምን ያህል በጥጋብ እና በትእቢት እንደተወጠሩ የሚያመለክተው ይህ ግድያ በስብሰባው ላይ ያሉትን የደህንነት ጓዶች ለማሸበር እና ለመጪው ምንም ዓይነት ጥያቄ እንዳያነሱ እና አለመግባባት እንዳይፈጥሩ ለማስደንገጥ የተደረገ እንደሆነ በግልጽ ያሳያል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰራዊቱ ውስጥ እና በደህንነት ተቋማት ውስጥ ያሉ አገልጋዮች ጥያቄዎችን እያነሱ ሲሆን እንዲሁም ከአገር በሚወጡበት አጋጣሚ ሁሉ ወደ ሃገር ቤት እንደማይመለሱ ታውቋል። ባለፈው አመት ለደህንነት ትምህርት ወደ እስራኤል ከተላኩ 67 ጓዶች ውስጥ 23 ወዴት እንደጠፉ የማይታወቅ መሆኑን መረጃውን ያደረሱን ምንጮቻችን ገልጸውልናል።


No comments:

Post a Comment