Wednesday, July 30, 2014

የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ጋዜጠኞችን ክስ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ (አስቂኙ ክስና አስቂኙ ማስረጃ)

አገራችን ኢትዮጵያ በጥሩ ልትጠራባቸው የምትችላቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው በድህነት በሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ በሙስና እና ሃሳብን ነጻነት በመግለጽ መብት የተለመዱ የምናፍርባቸው ጉዳዩች ሆነውመቀጠላቸው እሙን ነው፡፡ ሃሰብን በነጻነት መግለጽን አስመልክቶ ሶስት ወራትን ከፈጀ ምርመራ በኋላ በብዙ የፓሊስ ድብብቆሽሂደት የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላይ ባለፈው አርብ ክስ መመስረቱም አብሮ ይታወሳል:

ጓደኞቻችን ከታሰሩ ጊዜ ጀምሮ መንግሰት ያቀረበውን ውንጀላ አስመልክቶ በተለያየ ወቅት ሃሳባችንን ለመግለጽ አስበን ምናልባትየምንሰጠው ሃሳብ አሁንም በመንግሰት እጅ የሚገኙት ጓደኞቻችን ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽእኖ በመፍራት እነዲሁም ለመንግሰትእድሉን በመስጠት ኦፌሻል ክሱን እስክናይ ድረስ በጠቅላላ ሃሳቦች ላይ አስተያየት ከመስጠት ውጨ ብዙም ሳንል ቆይተናል፡፡ አሁንግን ክሱ አንድ የዞን 9 ጦማሪን ጨምሮ በይፋ በመመስቱ እነዲሁም በክሱ ላይ ተጠቀሱት ክሶች አንዳቸውም እውነት ባለመሆናቸውክሱን አስመልክቶ ዘርዘር ያለ ማብራሪያ መስጠት እነዳለብን ተሰምቶናል፡፡

በአስሩ ተከሳሾች ላይ የተጠቀሱት የክስ አይነቶች ሁለት ሲሆኑ አንዱ የሽብር ተግባርን ማቀድ ማሴር ማነሳሳትና መፈጸም ሲሆን(የጸረ ሽብር ህጉ አንቀጽ አራት) ሁለተኛው ህገ መንግሰታዊ ስርአቱን በሃይል መናድ( የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ አንቀጽ 238)የሚሉ ናቸው ፡። ክሱ ላይ በፓርላማ በሽብተኝነት ላይ ከተፈረጁ ድርጅቶች ቀጥታ ትእዛዝ በመቀበል በህቡእ በመደራጀት የሽብርተግባር ላይ መሰማራት እና የመሳሰሉት ክሶች በዝርዝር ቀርበዋል፡፡ ከሶቹ ሲጠቃለሉ



1. ከግንቦት ሰባት ጋር እና ከኦነግ ጋር ግንኙነት መፍጠር ትእዛዝ መቀበል

2. ስሙ ባልተጠቀሰ የህቡእ መደራጀት እና ስራ ክፍፍል መፍጠር

3. Security ina boxን ጨምሮ ስልጠና መውሰድ
4. አመጽ ቡድኖችን ማደራጀትና አመጽ ማነሳሳት  የሚሉት ዋናዋናዎቹ ናቸው፡፡



ከዚህ በፊትምእነደተናገርነው  ማንኛቸውም የዞን9 ጦማርያን በፓርላማ በሽብርከተፈረጁ ወገኖች ጋር ምንም ግንኙነት የለንም፡፡  ብዙ  የዞን9 ነዋሪያንንም አንደሚረዱት አብዛኛዎቹ የዞን9 ጦማርያን እነዚህአካላት ላይ በሚያደርጉት ከፍተኛ ትችት እየታወቁ ጉዳዩን ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ለማያያዝ መሞከር ፣መንግስት የፈረጃቸውንድርጅቶች እነደፈለገ ማንንም ሰው ለመክሰስ አንደሚጠቀምበት ከማሳየት ባለፈ ትርጉም የማይኖረው ነው፡፡ ለማጠቃለል ያህልማንኛቸውም የዞን9 አባላት አገር ውስጥም ሆነ ውጪ አገር ያለ የፓለቲካ ደርጅት አባላት አይደሉም፡፡ ይህንን የሚያሳይ መረጃምመንግሰት ለማቅረብ አንደማይችልም አናውቃለን፡፡ ( የማስረጃ ዝርዝር ላይ ወደታች የምንመለስበት ይሆናል)



በክሱ ላይ ስሙያልተጠቀሰ የህቡእ ሽብር ድርጅት በመመስረት ተከሰናል፡፡ በመሰረቱ መንግስት ዞን9 የሚለውን ስም አንድም ቦታ በክሱ ላይለመጠቀም ያልፈለገው የጦማርያኑን ቡድን ይበልጥ ታዋቂ እነዳይሆን ለማድረግ አንደሆነ አንገምታለን፡፡ ይህ አስቂኝ ክስ አንድምቦታ ላይ የዞን9 ስም ባያነሳም በደፈናው በህቡዕ መደራጀት ብሎ ከሶናል፡፡ በመሰረቱ መንግሰት እኛን ለማግኘት ምንም አይነትየደህንነት ስራ እነዳላስፈለገው አናውቃለን፣. ምክንያቱም ሁሉም የዞን ፱ ጦማርያን ስማቸውና ፎቶአቸውን ማስቀመጣቸው ቋሚየምንስማማበት እሴት ስለነበር ነው፡፡ የምንጽፈው ነገር በተናጠል ሃላፊነትን አንድንወስድ አንዲሁም ሌሎችን ሃሳብ መግለጽንለማበረታታት በማሰብ በአደባባይ  እነዲታይ የወሰነውን የጦማርያንንስብስብ ‹‹ህቡዕ›› ብሎ መጥራት ማንን ለማሞኘት አንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ ዞን፱ ድብቅ እነዳልሆነ እያንዳንዱ ጽሁፍምበተናጠል ሃላፊነቱን የሚወስድ ጸሃፊ የቡድን ጽሁፎች ሲሆኑ ደሞ የቡድን ሃላፌነት አንደምወስድ ማንም የጦማራችን አንባቢያውቀዋል፡፡ መንግስት የዞን፱ አይነት ጦማሮችንም ሆኑ የአንተርኔት አንቅስቃሴዎቸን የሚመዘግብበት አሰራር አለመኖሩ ደሞ የእኛጥፋት ተብሎ ሊቆጠር አይችልም፡፡ተሰብስቦ መጦመርን የሚከለክል ምንም አይነት የህግ ክልከላም የለም፡፡ በመሆኑም ተሰብስበንመጻፋችን  ራሳችንን ገልጸን ሃሳባችንን መግለጻችን የጣስነው ምንምሕግ የለም፡፡ፓሊስም ሆነ መንግሰት ሶስት ወር በፈጀ ምርመራው ህቡዕን ትርጉም ትርጉም በሚገባ አለማወቁም ጉዳዩን አስተዛዛቢባስ ሲልም መሳለቂያ ያደርገዋል፡።



Security in a box
እስካሁን በእጃችን የደረሰውን የማስረጃ ዝርዝር በሶሰት ከፍለን ማየት አንችላለን ፡፡ከማስረጃ ዝርዝሩ ውስጥ አብዛኛውን ቦታ የሚይዘው በተለያየ ወቅት የተጻፉ የጦማርያኑ ጽሁፎች ሲሆኑ ጋዜጠኞቹ ላይ ደሞ ጭራሽየመረጃ ዝርዝር ለማቅረብም አልተቻለም፡፡(አቃቤ ህግ የሁሉንም የበይነ መረብ ዘመቻዎች መግለጫ እና እቅድ እንደማስረጃአቅርቧል)  በሁለተኛ ደረጃ የቀረቡት የተለያዩ የጉዞ ትኬቶችአለም አቀፍ ስብሰባ ማስታወሻዎች አንዲሁም ፕረዘንቴሽኖች  ሲሆኑሁሉም ጦማርያኑ ያደረጓቸው አለም አቀፍ ጉዞዎችን የሚያሳዩ የተሳተፉባቸው ሰብአዊ መብትና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትየተመለከቱ የአፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባኤ የተደረጉ ጉዞዎችን ናቸው፡፡

በማስረጃ ዝርዝር ውስጥከተካተቱት የሽብር ተግባር የተደረጉ ጉዞዎች ተብለው መሆኑ ይበልጥ ክሱን አሳፋሪ ያደርገዋል፡፡ መንግሰት ጉዞዎቹ የተደረጉትምሆነ የስልጠና ግብዣዎቹ የመጡት ከአለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት አንደሆነ እያወቀና እና ማስረጃው ላይም በግልጽእየታየ የሽብር ቡድኞች ብሎ ግንቦት ሰባትና ኦነግን ጣልቃ ማስገባቱ አስገራሚ ነው፡፡ (የፍርድ ሂደቱ ላይ እነዚህ ተቋማት ጋርየተደረጉ ግንኙነቶቸን አንዴት ብለው በፓርላማ ከተፈረጁ የሽብር ተቋማት ጋር እነደሚያገናኛቸው አብረን የምናየው ይሆናል)  በሶስተኛ ደረጃ የተቀመጡት ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ የተደረጉ የስልክልውውጦች ሲሆኑ በፍርድ ቤት ሂደቱ ውስጥ በዝርዝር የምናያቸው ይሆናል፡፡ በመጨረሻም ተከሳሽ ቤት ተገኘ የተባለውና ፓሊሶች ራሳቸው ያመጡት ከግንቦት ሰባት ጋር የተገናኙ ዶክመንቶች እናየአባላት መጽሄት ሲሆን በፍተሻው ወቅት ፓሊሶች ራሳቸው ፍሪጅ በስተጀርባ አገኘን ብለው በፍተሻ ወቅት ከፍተኛ አለመግባባትተፈጥሮ የራሳቸውን ምስክሮች ብቻ አስፈርመው መሄዳቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

እንዲሁም ፓሊስ 18 የሰው ማስረጃ ለማሰማት የስም ዝርዝር ማስገባቱን እና የስም ዝርዝሩም እጃችን ላይ የሚገኝ ቢሆንም ከፍርድቤት ለሚመጣው የፍርድ ውጤት ሳይሆን በአጠቃላይ የፍትህ ስርአትን ማክበር ሃላፊነት ስላለብን ብቻ እዚህ ጽሁፍ ውስጥ ላለማካተትወስነናል፡፡

የዞን፱ ጦማርያን ከዚህ በፊትም በተለያየ ወቅትአንደተናገርነው የመንግሰት ይህን ሁሉ ጊዜ ወስዶ ይዞ የመጣው ማስረጃ የአደባበይ ጽሁፎች እና በተለያየ ወቅት የተደረጉ የአደባባይሁነቶች( public events) ጥርቅም መሆኑ የክሱን ፓለቲካዊነት ያረጋገጠ ነው፡፡ ጦማርያኑ የፍርድ ቤት ስርአቱን የተለያዩአለም አቀፍ የወንጀል ስነስርዓት ደረጃን በጠበቀ መልኩ ህጉን አክብረው የሚከታተሉ ሲሆን እኛም ሂደቱን በተቻለ መጠን ለዞን ፱ነዋሪያን ለማሳየት ለማሳወቅ የምንጥር መሆኑን ለማሳወቅ አንወዳለን፡፡ በተደጋጋሚ ተፈትኖ የወደቀው የአገራችን ፍርድ ቤት እና የፍትህስርአት ገለልተኝነት ይህንን እድል በመጠቀም ራሱን ለማሻሻል መፍቀዱን እነዲያሳይና ፍርድ ቤቱ ማስረጃዎቹን አይቶ ክሱን እነዲዘጋጥሪ እያደረግን ይህንን በማድረግ የአገሪቱን የፍትህ ሂደት አንድ ደረጃ የማራመዱን እድል ዳኞች እንዲጠቀሙበት መንግስትን ከወራትበፌት የሰራውን ስህተት ለማስተካከል እድሉ ዛሬም ያልመሸ መሆኑን ለማስታወስ አንወዳለን፡፡

የታሰራችሁ ጦማርያንን እና ጋዜጠኛ ወዳጆቻችን ለከፈላችሁት መስዋእትነት ውለታችሁ አለብን፡፡ እንኮራባችኋለን!!

ማስረጃ ተብለው የቀረቡ ሰነዶች ለፈገግታ ያህልዞን ዘጠኝ ላይ የታተሙ ጽሁፎችነጻነትና ዳቦሳንሱር ዋጋ ያስከፍላልስደትና ፍቅርዋኤል ጎኒሞ ኢትዮጵያዊ ቢሆን ኖሮ ….?ልማታዊ ጋዜጠኝነት ወይስ ይሁንታን ማምረት?ድምፃችን ይሰማእንዴት እንደመጥየመለስ ውርስ እና ራዕይየቅድመ ምርመራ ቅድመ ምርምራትግራይና ሕዋሐት ምንና ምን ናቸው ?ህግ ምርኩዝ ነው ዱላ



ከበፍቃዱ ብሎግ(www.befeqe.com) የተገኙ “መንግስት የለም ወይ ?”ስለ ዞን 9 ዘመቻዎች globalvoicseonline.orgበናትናኤል በኩል ለርዕዮት ዓለሙ ቤተሰቦች ከ Article 19


No comments:

Post a Comment