Friday, April 27, 2018

በሽንሌ እና አጎራባች አካባቢዎች ሕዝብ እና ታጣቂዎች ተፋጠዋል።

በዛሬው ዕለት ድሬዳዋ በተቃውሞ ሰልፍ ስትናጥ፣ጅግጅጋ ደግሞ በሥራ ማቆም አድማ ጸጥ ረጭ ብላ ውላለች።ሕዝባዊ ቁጣውና ተቃውሞው በሚቀጥሉት ቀናት አድማሱን በማስፋት በርካታ አጎራባች ወረዳዎችን እና ከተሞችን እንደሚያዳርስ ከአካባቢው የሚወጡ ዜናዎች ይጠቁማሉ።
-የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ዶናልድ ያማሟቶ፣ በወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ለመወያዬት ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል።ዘግይቶ በደረሰን ዜና ያማሟቶ ከአኦቦ በቀለ ገርባ፣ ከዶክተር መረራ ጉዲና፣ከአቶ አንዷለም አራጌ እና ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጋር ተወያይተዋል።
-ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ -ለአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሽልማት መስጠታቸው ከፍ ያለ ሕዝባዊ ቅሬታ አስከትሏል።

“በፈጸሙትና ባስፈጸሙት የግድያ ወንጀል ለህግ መቅረብ የሚገባቸውን ሰው ኒሻን መሸለም በሟቾች ቀብር ላይ መደነስ እና በቤተሰቦቻቸው ሀዘን ላይ መቀለድ ከመሆኑም በላይ ፣ሕዝብን መጨፍጨፍ የሚያሸልም እንጂ የሚያስጠይቅ ተግባር እንዳልሆነ መልዕክት በማስተላለፍ- ወንጀልን እና ወንጀለኞችን ለመከላከል የሚደረግን ጥረት የሚያጨናግፍ ነው” በማለት በርካታ ኢትዮጵያውያን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ-ለአቶ ኃይለማርያም የሰጡትን ሽልማት እየኮነኑ ነው።
“በትዕዛዝ አላስገደሉም” ቢባል እንኳ አቶ ኃይለማርያም መጠየቅ ያለባቸው ግድያውን ማስቆም ባለመቻላቸው ጭምር መሆኑ ሊጤን ይገባል የሚሉት አክቲቪስቶች፣ “እንደውም ማዘዝ በማይችሉበት ትልቅ ሥልጣን ላይ ተቀምጦ ለገዳዮች ሽፋን መስጠት የከፋው ወንጀል ነው”ይላሉ።
-ይሕ በእንዲህ እንዳለ “የጡረታ ጊዜያቸው አልፎ ከወንበራቸው መነቃነቅ የማይፈልጉ በጣም በርካቶች አሁንም እኛ ውስጥ አሉ” ሲሉ ዶክተር አብይ አህመድ መናገራቸው ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።
አቶ ስብሀት ነጋን፣ አቶ አባይ ጸሀዬን፣ ዶክተር አርከበ ዕቁባይን፣ አቶ በረከት ስምዖንን እና አቶ አዲሱ ለገሰን ጨምሮ በርካታ በዕድሜ የገፉ የኢህአዴድ አመራሮች በሥልጣን ወንበር ላይ እያሉ ወደ መጃጀት ያመሩ ሲሆን፣ዶክተር አብይ “ የጡረታ ጊዜያቸው አልፎ ከሥልጣን ወንበራቸው መነቃነቅ የማይፈልጉ”በማለት የወረፏቸውም እነዚህን እና መሰሎቻቸውን እንደሆነ ብዙዎች ያምናሉ።
-በህገ ወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠው ወደ ደቡብ አፍሪቃ ሊያመሩ ሲሉ ይዣቸዋለሁ ያላቸውን 26 ኢትዮጵያውያን ማሰሩን የሞዛምቢክ ፖሊስ አስታውቋል።
የማኒካ ግዛት ፖሊስ አዛሽ የሆኑትን ሚስተር ኤሊሲዲያ ፍሊፔን ጠቅሶ ራዲዮ ሞዛምቢክ እንደዘገበው፣ ስደተኞቹ ከ 19 እስከ 40 የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆኑ፣ ሁሉም ወንዶች ናቸው ፡፡
የእነዚህን ዜናዎች ዝርዝር እና ሌሎች ወቅታዊ ፕሮግራሞችን ከትንሳኤ ያዳምጡ።
ትንሳኤ- የእርስዎ ራዲዮ!

No comments:

Post a Comment