Thursday, April 12, 2018

በሙስና ተከሰው የነበሩት የሕወሃት አባላት ተፈቱ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 4/2010)በሙስና ተከሰው የነበሩት የሕወሃት አባላቱ አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሔርና አቶ ገብረስላሴ ገብሬ በዋስትና መፈታታቸው ተነገረ።
በሕጉ መሰረት ቢሆን ኖሮ በሙስና የተከሰሰ ሰው የዋስትና መብት አይፈቀድለትም።
በእነ አቶ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ ተከሰው የነበሩት የነጻ ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሔር በ750ሺ ብር የኮሜት ኩባንያ ባለቤት አቶ ገብረስላሴ ገብሬ ደግሞ በ5 መቶ ሺ ብር ዋስ ተለቀዋል።
ሁለቱ ተከሳሾች በሙስና ወንጀል ከታሰሩ ከ5 አመት በላይ ሆኗቸዋል።
በእነ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት የነጻ ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሔርና የኮሜት ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤት አቶ ገብረስላሴ ገብሬ በሙስናና ግብር በመሰወር ተወንጅለው ነበር።

ሁለቱም የሕወሃት አባል እንደሆኑ የሚነገርላቸው ተከሳሶች ግን የሙስና ክስ የዋስ መብት የሚከለክል ቢሆንም ከእስር እንዲለቀቁ ተደርጓል።
አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሔር በ750ሺ ብር ዋስ ሲፈቱ አቶ ገብረስላሴ ገብሬ ደግሞ በ500ሺ ብር ዋስትና ተለቀዋል።
ዋስትና በተፈቀደላቸው በዚሁ ክስ ፍርድ ለመስጠትም ለሚያዚያ 24/2010 ቀጠሮ መሰጠቱ ተነግሯል።
አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሔር የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር የነበሩትን አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ ባለቤትን ኮለኔል ሃይማኖትን በወር 33 ሺ ብር ደሞዝ እየከፈሉ በድርጅታቸው ውስጥ ቀጥረው ሲያሰሩ እንደነበር ቀደም ሲል በተከሰሱ ጊዜ መገለጹ ይታወሳል።
አቶ ነጋ ከአቶ ገብረዋህድ ጋር በመሳተር ለረጅም አመታት እቃ ያለቀረጥ ያስገቡ እንደበርም ተገልጿል።
ለረጅም አመታት ሕወሃትን ሲደግፉ የቆዩት ሁለቱ ተከሳሾች በዋስ ሲለቀቁ እነ አቶ መላኩ ፈንታ ግን አሁንም በእስር ቤት በመማቀቅ ላይ ይገኛሉ።

No comments:

Post a Comment