Wednesday, April 18, 2018

ድምጻዊ ታምራት ደስታ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

Image may contain: 1 person, smiling, sunglasses and selfie(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 10 ቀን 2010 ዓ/ም) ድምጻዊ ታምራት ደስታ ለሕክምና ወደ ስላሴ ክሊኒክ በመኪና እየተጓዘ እያለ በድንገተኛ አደጋ ራሱን ስቶ ሕይወቱ አልፏል። ድምጻዊ ታምራት ደስታ ባለትዳርና የ5 ልጆች አባት ነበር። በሻሸመኔና ሃዋሳ ከተማ አማካኝ ላይ በምትገኘው በጥቁር ውሃ ከተማ በ1971 ዓ.ም የተወለደውና በሻሸመኔ ከተማ ያደገው ድምጻዊ ታምራት ደስታ ለቤተሰቦቹ 2ኛ ልጅ ሲሆን ሁሉም ወንዶች ናቸው። በተወለደ በ39 ዓመቱ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ለተለየው ድምጻዊ ታምራት ደስታ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶቹና ለአድናቂዎቹ የዝግጅት ክፍላችን መጽናናትን ይመኛል።

No comments:

Post a Comment