Friday, April 13, 2018

ባለፈው ቅዳሜ በደረሰው የጎርፍ ጉዳት እስካሁን ከ7 ያልበለጠ አስከሬን መገኘቱ ታወቀ

(ኢሳት ዜና- ሚያዚያ 5 ፣ 2010 ዓም)
የአካባቢው ነዋሪዎእ እንደገለጹት ባለፈው ቅዳሜ በጅግጅጋ ቀበሌ 10፣ 17 እና 18 የተፈጠረውን ጎርፍ ተከትሎ በርካታ ዜጎች በጎርፍ ተወስደው ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፣ ኢሳት ዘገባውን ባቀረበ ማግስት የክልሉ ፖሊስ እና መከላከያ ፍለጋ ጀምረው እስካሁን የ7 ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል። የበርካታ ዜጎች አስከሬን አሁንም ድረስ አለመገኘቱን፣ በጎርፍ ከተወሰዱት መካከል የንግድ ባንክ ስራ አስኪያጅ የሆነ ግለሰብም እንደሚገኝበት የክልሉ ዘጋቢያችን ገልጿል። 
በጎርፉ አንድ የመብራት ሃይል መኪና እና 4 አይሱዙ መኪኖች በጎርፍ ተወስደዋል። አንድ ኮካ ኮላ የጫነ መኪና እስከሙሉ ጭነቱ የተገለበጠ ሲሆን፣ የጫነው ኮካ ኮላም በጎርፍ ተወስዷል። በመኪኖች ላይ የነበሩ ሰዎችም በጎርፍ ተወስደዋል። 
ጎርፉ በምስራቅ ሃረርጌ ዞን ጭናክሰን ከተማ በዘነበው ዝናብ ምክንያት የተፈጠረ ነው::

No comments:

Post a Comment