Monday, April 2, 2018

አሜሪካ ለዶክተር አብይና መንግስታቸው ድጋፌን እሰጣለሁ አለች

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2010)ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ለተመረጡት ዶክተር አብይ አህመድ አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት መንግስታት፣እንዲሁም ታዋቂ ሰዎች የደስታ መግለጫ አስተላለፉ።
ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ለዶክተር አብይና መንግስታቸው ድጋፏን እንደምትሰጥ አረጋግጣለች።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም እንዲነሳ ጥሪዋን አቅርባለች።
አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩልም ባወጣቸው መግለጫ በዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው መንግስት አፋጣኝ ዲሞክራሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን እንዲያመጣ ድጋፍ እንደምትሰጥ የገለጸችው ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም እንዲነሳ ጥሪዋን አቅርባለች።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣የአፍሪካ ሕብረት ኮሚስን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ፣የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሙሐመድ አብዱላሂ ፎርማጆ ሹመቱን ተከትሎ የደስታ መግለጫቸውን ካስተላለፉት ውስጥ ይጠቀሳሉ።
የሶማሌ ላንድ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የደስታ መግለጫ አስተላልፈዋል።

No comments:

Post a Comment