Thursday, August 9, 2018

በምዕራብ ጉጂና ጌዲዮ አካባቢ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ተደረገ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 3/2010) አለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበርና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ከደቡብ ክልልና ኦሮሚያ አወሳኝ ቦታዎች በምዕራብ ጉጂና ጌዲዮ አካባቢ ለተፈናቀሉ ሰዎች ድጋፍ አደረጉ።

ቀይ መስቀል በምዕራብ ጉጂና ጌዲዮ አዋሳኝ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ መስጠት መጀመሩን አስታወቋል።


በኦሮሚያና ደቡብ አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረ ግጭት ባለፈው ሚያዚያና ሰኔ ወር ላይ እስከ 1 ሚሊዮን የሚደርሱ የአካባቢው ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል፡፡

በግጭቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ ንብረት የወደመባቸው ግን በርካታ ናቸው።

በምዕራብ ጉጂና ጌዲዮ አካባቢ ለተፈናቀሉ ሰዎች በመንግስትም ሆነ በረድኤት ድርጅቶች በቂ ድጋፍ ሳይደርግ ቆይቷል።

አሁን ባለው ሁኔታ ግን ከተፈናቃዮቹ መካከል አለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበርና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ባለፈው ሳምንት ለ10ሺ ቤተሰቦች እርዳታ ሰጥተዋል፡፡

በተሰጠው ድጋፍም እስከ 60 ሸህ የሚደርሱ ተፈናቃዮች ተጠቃሚ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

እርዳታው የፕላስቲክ መጠለያዎች ፣ምንጣፎች፣ ብርድ ልብሶችና የውሃ መቅጃዎች፣ የምግብ ማብሰያና ንፅህና መጠበቂያዎችን ያካተተ ነው፡፡

የአለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር የኢኮኖሚ ደህንነት ልዑክ ዤን ፒሬ ሱማህ ማህበሩ ለተፈናቃዮቹ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

No comments:

Post a Comment