Thursday, August 2, 2018

ይድረስ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ።(ወ/ሮ ሃይማኖት አበራ ተገኘ እባላለሁ፣የረዳት አብራሪ ኃይለ መድህን አበራ ታላቅ እህት)

Image may contain: 1 person, hat and closeupከሁሉ አስቀድሜ የአክብሮት ሰላምታዬን አቀርባለሁ፡፡
ወ/ሮ ሃይማኖት አበራ ተገኘ እባላለሁ፣የረዳት አብራሪ ኃይለ መድህን አበራ ታላቅ እህት ስሆን የምኖረው ጀርመን ነው።
ዛሬ ለእርስዎ ለመጻፍ ያነሳሳኝ በቅርቡ የታወጀው የምህረት አዋጅ ያሳደረብኝ ተስፋ ነው።
እንደሚያውቁት ወንድሜ ከየካቲት 2006 ጀምሮ በስዊትዘርላንድ አገር በእስርቤት እና በስደት እየተንገላታ ይገኛል። ወደ አገሩ እንዳይመለስ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍርድቤት የ 19 አመት ከ6 ወር እስር ፈርዶበታል።
ጉዳዩን በተመለከተ የተሟላ መረጃ እንደሚኖርዎት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በአጭሩ ለመግለጽ ያህል፡ የስዊትዘርላንድ ፍርድ ቤት የቀረበለትን የባለሙያ ሪፖርት መሠረት በማድረግ በወንጀል ተጠያቂ እንዳይሆን፣ ሆኖም በሕግ ጥበቃ ስር ሕክምና እንዲከታተል ወስኖበት ውሳኔውም ተፈጻሚ ይሆን ዘንድ በጄኔቫ ከተማ አካባቢ በጥበቃ ስር ይገኛል፡፡ እስካሁን ባለኝ መረጃ መሠረት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ባይኖር ኖሮ የኢትዮጵያ መንግሥት የስዊትዘርላንዱን ፍርድ ቤት ውሳኔ በአገራችን ተፈጻሚ ለማድረግ ተስማምቶ ኃይለመድህንን ወደሚወዳት አገሩ እንዲመለስና ከናፈቁት የቤተሰቡ አባላት በተለይም ከአረጋውያን እናትና አባቱ ጋር እንዲገናኝ ማድረግ ይችል ነበር ብዬ አምናለሁ፡፡

በዚህ መሠረት ለወንድሜ ይሄን ፍርድ እንዲያስነሱለትና ወደሚናፍቃት አገሩ ተመልሶ በእውቀቱ አገሩንና ህዝቡን እንዲያገለግል፤ ከሁሉም በላይ በእድሜ የገፉት እናትና አባታችን ቀሪ የእድሜ ዘመናቸውን በናፍቆትና በሀዘን እንዳያሳልፋ በመራራት ለወንድማችን ምህረት ያሰጡት ዘንድ ቤተሰቦቼን ወክዬ በታላቅ ትህትና ተማጽኖአችንን አቀርባለሁ።
ሃይማኖት አበራ
ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ አዲስ አበባና ባህርዳር ያሉትን የቤተሰባችንን አባላት በአካል አስቀርበው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
1. ዶ/ር እንዳላማው አበራ 0984623786 አዲስ አበባ
2. ዶ/ር መድኃኒት አበራ 0911862487 አዲስ አበባ
3. ዶ/ር ንዋየ መድህን አበራ 091103048 አዲስ አበባ
4. ኢ/ር ተወልደ መድህን አበራ 0911227220 አዲስ አበባ
5. አቶ አበራ ተገኘ /አባታችን/ 0918765333 ባህርዳር
6. ወ/ሮ የዝባለም ሥዩም /እናታችን/ 0939285262 ባህርዳር

No comments:

Post a Comment