Tuesday, July 4, 2017

ብአዴን ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካና ርእዮተአለም ብልሽት አጋጥሞታል።

ሰኔ ፳፯ ( ሃያ ሰባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “ ብአዴን ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካና ርእዮተአለም ብልሽት አጋጥሞታል። በ40 እና 50 አመታት ጊዜ ውስጥ የበለጸገ አገር የሚፈጥር መስመር ሆኖ እያለ፣ ይህንን መስመር በብቃት ባለማወቃችን ምክንያት ይህን መስመር እየተከላከልነው አይደለም” የሚሉት ባለስልጣኑ፣ በእኛ የአመለካከትና የአስተሳሰብ ብልሽት ምክንያት ከመስመራችን በተጻጻሪ ለቆሙ ሃይሎች አቅም ሆነን እንታያለን ሲሉ በተሃድሶ ስብሰባ ላይ ምሬታቸውን ይገልጻሉ። ለአስተሳሰባችን መበላሸት ማሳያ ከሆኑት ምክንያቶች መካከል በክረምት ወራት የገጠመን ከፍተኛ ትርምስ አንዱ ነው የሚሉት ባለስልጣኑ፣ የደርግን ስርዓት አንኮታኩተው የጣሉትን ህወሃትን ከኢህአዴግ ጋር ለማጣላት፣ ህወሃትን በብአዴን ላይ ለማነሳሳትና ከፍተኛ ግጭት ለመፍጠር ጸረ ሰላም ሃይሉ ሃይሉን አሟጦ ሲሰራ ቆይቷል ይላሉ። “ይህ የተጠነሰሰው ሴራ ባግባቡ ያልገባው የእኔ
ቢጤ የዋህ’ ልክ ነው ብአዴን የአማራን ህዝብ ጥቅም አያስከብርም፣ የህወሃት የበላይነት አለ’ እያለ የጸረ ሰላም ሃይሉ መሚያ ሆነን ድርጅታችንን ስናብጠለጥል ከርመናል” በማለትም የድርጅት አባሎቹን ወቅሰዋል። የኢትዮጵያ መካለከያ ሰራዊትና አመራር ዘሩ ሲቆጠር ከርሟል የሚሉትን ባለስልጣኑ፣ መከላከያ ሰራዊቱ እሱ እየተሰዋ እኛን እየጠበቀን እያለ እኛ ግን እሱን ልናፈርስ ስንሯሯጥ ከርመናል የሚሉት ባለስልጣኑ፣ የብልሽታችን መጠን እስከዚህ ደርሷል ብለዋል የአርማጭሆ አርሶአደር በክረምት ወራት የመከላከያ ሃይላችንን ፊት ለፊት ጦር ገጥሞ 11 የመከላከያ አባላት ሲሞቱ፣ አንድም አርሶአደር እንዲቆስል አላደረገም ሲሉ ለመከላከያው ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል። “የመከላከያ ሰራዊት አመራር አባላት እዚህ ብሄር ናቸው እየተባለ ይባላል፣ የመከላከያ ሰራዊት ጄኔራል ማግኘት ካስፈለገ ምንጩ እግረኛ ነው። እዚህ ክልል ለእግረኛ ወታደር የሚመዘገብ የለም፣ ታዲያ እግረኛ ከሌለ፣ ምንጩ ከሌለ ወንዝ ልታገኝ አትችልም” ሲሉ የክልሉ ነዋሪዎች ለመካለከያ ስለማይመዘገቡ ፣ ጄኔራል የሚሆን ሰው መጥፋቱን ገልጸዋል። “ክረምት ላይ የኢኮኖሚ ተቋሞቻችን ሲዘመቱባቸው ለመከላከል አልቻልንም የሚሉት ባለስልጣኑ፣ በተሃድሶዎቻችን እንዲህ አይነት የአስተሳሰብ ብልሽቶችንና መበሳበሶችን ማስወገድ አለብን” ሲሉ ምክራቸውን ለግሰዋል።

No comments:

Post a Comment