Tuesday, July 4, 2017

ህወሃት መራሹ መንግስት ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፈውን የቴሌቪዥና የራዲዮ ስርጭት ሙሉ በሙሉ ለማፈን የሚያደርገው እንቅስቃሴ ለማክሽፈፍ ነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያውያን በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀናጅተው እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ቀረበ

ኢሳት ሰኔ 27/2009
ህወሃት መራሹ መንግስት ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፈውን የቴሌቪዥና የራዲዮ ስርጭት ሙሉ በሙሉ ለማፈን የሚያደርገው እንቅስቃሴ ለማክሽፈፍ ነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያውያን በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀናጅተው እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ቀረበ።
የኢሳት ዋና ዳይሬክተር አበበ ገላው ጉዳዩን በማስመልከት ለኢሳት በሰጠው መግለጫ አንዳስገነዘበው ህወሃት መራሹ መንግስት በከባድ ፈተና ውስጥ ባለበት በዚህ ወቅት ከመቶ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መድቦ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑ ገልጿል።
የህውሃት/ ኢህአዴግ አገዛዙ የስለላና የአፈና መረብ በሆነው ኢንሳ በተባለው ድርጅት አማካኝነት በቅርቡ
ከ25 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚገመት የአገልግሎ ውል ዩቴልሳት ከሚባለው የሳተላይት አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ ጋር ያደረገ ሲሆን የውሉ ዋነኛ አላማ ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርገውን ስርጭት የበለጠ ማወክ እንደሆነ ማኔጂንግ ዴሬክተሩ አስረድቷል። ውሉን በዩቴልሳት በኩል የፈረሙት የድርጅቱ የንግድ ሃላፊ ማይክል አዚበርት ሲሆኑ ህወሃት መራሹን መንግስት በመወከል የኢንሳ ዋና ዳይሬክተር ገብረሚካኤል ተክለማሪያም መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
አሳት እንደ እሳካሁኑ ሁሉ መሰናክሎችን ሁሉ ተቋቁሞ ስርጭቱን እንደ ሚቀጥል ያስገነዘቡት አቶ አበበ ገላው የኢሳት ደጋፊዎችም የበለጠ ተቀናጅተው መስራት ይገባቸዋል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ጉዳዩንም በማስመልከት በጁላይ 6 የፊታችን ሃሙስ በሲያትል ከተማ ውይይት ስለሚደረግ ነጻነት ናፋቂው ኢትዮጵያዊ ሁሉ በ 16500 Southcenter Parkway በሚገኘው ደብል ትሪ ሆቴል በመገኘት የውይይቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።
በዚሁ የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ኢሳትን በመወከል ዳይሬክተሩን ጨምሮ የኢሳት ጋዜጠኞች የሆኑት ሲሳይ አጌና እና ተቦርነ በየነ እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል።

No comments:

Post a Comment