Monday, July 17, 2017

በደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በሚገኘው አርባ ምንጭ ከተማ አንድ ባልሁለት ፎቅ ህንጻ ተደርምሶ 4 ሰዎች ሞቱ። 11 ሰዎች ደግሞ ቆስልዋል

(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 10/2009) በደቡብ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በሚገኘው አርባ ምንጭ ከተማ አንድ ባልሁለት ፎቅ ህንጻ ተደርምሶ 4 ሰዎች ሞቱ። 11 ሰዎች ደግሞ ቆስልዋል በተደረመሰው ሕንጻ ፍርስራሽ ስር ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች መቀበራቸውንም ዥንዋ በዘገባው አመልክቷል። የከተማዋ ከንቲባ አቶ ኢዞ ኢማጎ የሕንጻው ባለቤት ደረጃውን ያልጠበቅ የህንጻ ግንባታ አካሂደዋል በሚል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል። በህንጻው ስር የተቀበሩት ሰዎች ስላሉበት ሁኔታና ሰዎቹን ለማዳን እየተደረገ ስላለው ርብርብ የተገለጸ ነገር የለም።

No comments:

Post a Comment