Thursday, July 13, 2017

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ የተከሰሱበትን የሽብር ክስ ወደ ተራ ወንጀለኝት እንዲቀየር የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሰነ

ኢሳት ሐምሌ-6/2009 የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ የተከሰሱበትን የሽብር ክስ ወደ ተራ ወንጀለኝት እንዲቀየር የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሰነ። ፍርድ ቤቱ በሽብር ወንጀል ከተከሰሱት 22 የተቃዋሚ የፖለቲካ መረጃዎችና አባላት 17ቱ እንዲከላከሉ የጥፋተኝነት ውሳኔ አሳልፎባቸዋል። 5 ተጠርጣሪዎች ደግሞ በነጻ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ውስኗል ። ፍርድ ቤቱ በቀጥታ በሽብር ወንጀል ተሳትፈዋል ተብለው ተከሰው ከነበሩት መካከል ጎርሜሳ አያና፣ ደጀኔ ጣፋ፣ አዲሱ ቡላላ፣ አብሏታ ነጋሽ፣ ገላና ነገራ፣ ጌቱ ግርማ፣ በየነ ረዳ እና ተስፋዬ ሊበን በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ መሳተፍ ወደሚል ተቀይሮ በአዋጅ አንቀፅ 3 ወደ አንቀፅ 7 ንዑስ ቁጥር 1 ተቀይሮ ይከራከሩ ሲል ክሳቸውን አሻሽሏል። አቶ በቀለ ገርባ ላይ የቀርበው ማስረጃ የሽብር ወንጀልን የማያቋቁም ስላልሆነ ከፀረ-ሽብር አዋጅ ወጥቶ በወንጀልኛ መቅጫ ሕጉ አንቀፅ 257/ሀ/ ስር የተሰናዳ ግዙፍ ያልሆነ መሰናዳትና መገፋት ክስ ተቀይሮ እንዲከላከሉ ወስኗል። የአቶ በቀለ ገርባ የሽብር ክስ በማስረጃ የተረጋገጠ አይደለም ቀሪ ቢደረግም ለምን ወደ ወንጀል ክስ አደገና እንዲቀየር ፍርድ ቤቱ እንደወሰነ ግልጽ አይደለም ተብሏል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ የተከሰሱበት የሽብር ክስ ቀሪ በመደሩጉ የዋስትና መብታቸውን የመጠበቅ መብት እንዲኖራቸው እንደሚያደርጉ አዲስ ስታንደርድ ዘግቧል። በኢትዮጵያ በሽብር የተከሰሰ ማንኛውም ሰው ዋስትና የመጠበቅ መብት የለውም። ይህም ሆኖ ግን አቶ በቀለ ገርባ አሁንም ጥፋተኛ የተባሉበት ወንጀል ክስ ከሕገመንግስቱ ውጭ አመፅን ቀስቅሰዋል ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን ተፃረዋል እና የእርስበርስ ጦርነት እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆነዋል ስለሚል ከባድ ቅጣት እንደሚያስከትልባቸው በዘገባው ተመልክቷል። በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት ከክሱ ነፃ የተደረጉት ጌቱ ግርማ፣ ጌታቸው ደረጀ፣ በየነ ፊዳ፣ ደረጀ መርባ እና ሐልቄኖ ቆንጨራ ናቸው። በሽብርተኝነት እንዲከላከሉ ከተበየነባቸው 16ቱ ተከሳሾች መካከል ደግሞ ጎርሜሳ አያኖ፣ ደጀኔ ጣፋ፣ አዲሱ ቡላላ፣ አብደታ ኔጌሳ እና ገላና ነገራ ይገኙበታል። 16ቱ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በሽብር ወንጀል ከተፈረደባቸው ከ5 እስከ 10 ዓመታት እስር እንደሚጠብቃቸው የሕግ ባለሙያዎች ይገልፃሉ። ተከሳሾቹ በሽብር ከተፈረጀው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር/ኦነግ/ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል እንደሆነ የተወነጀሉት የአቃቤ ሕግ ሰነድ ያመለክታል። ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን የመከራከሪያ ሀሳቦችን ለማድመጥ እ/አ/አ ለነሐሴ 17/2017 መቅጠሩን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።


No comments:

Post a Comment