Monday, June 15, 2015

ፍርድ ቤቱ በዞን ዘጠኝ አባላትና ጋዜጠኞች ላይ ለብይን ቀጠሮ ሰጠ

ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ፣ ልደታ ምድብ ሰኔ 8/2007 ዓም በዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ላይ በቀረበው የሽብረተኝነት ክስ ላይ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ
13/2007 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።
ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ጥቁር ለብሰው ፍርድ ቤት የተገኙ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም ከዚህ ቀደም በቀረበለት የቪዲዮ ማስረጃ ላይ ውሳኔ ሰጥቷል። አቃቤ ህግ በአንደኛ ተከሳሽ ላይ የሲ.ዲ ዶክሜንተሪ ማስረጃ ማቅረቡን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ
ሲ.ዲው በችሎት መታየቱን ተገቢ ሆኖ ስላላገኘነው ለዳኞች ብቻ ተመልከተውት በማስረጃነት እንዲያዝ እንዲደረግ ወስኗል። ይህን ተከትሎ ተከሳሾች በብይኑ ላይ አለን ያሉትን አቤቱታ በጠበቆቻቸው አማካኝነት ያሰሙ ሲሆን ፣ ፍርድ ቤቱ
ግን ብይን ባገኘ ጉዳይ ላይ አቤታቱውን ከመመዝገብ ውጭ ለውጥ እንደማይኖረው ገልጿል።
ፍርድ ቤቱ ሐምሌ 13/2007 ዓ.ም ተከሳሾች ለቀረበባቸው ክስ ይከላከሉ ወይስ በነጻ ይሰናበቱ በሚለው ጉዳይ ላይ ብይን ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጋዜጣው ዘግቧል።


No comments:

Post a Comment