Friday, November 21, 2014

ፕሮፌሰር በየነ ጼጥሮስ ዲያስፖራውን ወቀሱ “ዲያስፖራው ገዥው ፓርቲ የሚሰራው ሥራ ሁሉ ጥፋት ነው ብሎ ራሱን አሳምኖ ቁጭ ያለ ነው”

ከአንድ ዓመት ላላነሰ ጊዜ በአሜሪካን ሀገር በቺካጎ ከተማ በሚገኝ አንድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሲያስተምሩ ቆይተው በቅርቡ ወደሀገር ቤት መመለሳቸውን የተናገሩት የወቅቱ የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ዲያስፖራውን ወቅሰዋል።

ፕሮፌሰሩ በዛሬው ዕለት ለንባብ ከበቃው መንግስታዊው ዘመን መጽሄት የጥቅምት 2007 ዕትም ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ “ዲያስፖራው ተስፋ የቆረጠና የተናደደ ነው፡፡ ተስፋ ስለቆረጠና ስለተናደደ ገዥው ፓርቲ የሚሰራው ሥራ ሁሉ ጥፋት ነው ብሎ ራሱን አሳምኖ ቁጭ ያለ ነው፡፡ በዚህም የሚናደድና የሚንቦገቦግ ነው፡፡

እናም ከእነዚህ ጋር ውይይት ማድረግ አይቻልም፡፡» ብለዋል። ፕሮፌሰር በየነ በዚሁ ቃለምልልሳቸው “ዲያስፖራውን ለመምከር እንሞክራለን» ካሉ በኃላ በአሜሪካ ቆይታቸው ወቅት እርሳቸው ንግግር እንዲያደርጉ የተጋበዙ ሰዎች እንዲበተኑ እንደተደረገ ተናግረዋል።

መጽሄቱ በእሳቸው ላይ ይህ ለምን እንደተደረገ ጠይቆአቸው በሰጡት ምላሽ “እኔ እውነቱን ስለማወጣ ነው» የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ኢህአዴግ በአንድ በኩል እኛን ትክክል ባልሆነ ምስል ያስቀምጠናል ያሉት የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ዲያስፖራው ደግሞ የባሰ በመሆኑ መቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡


No comments:

Post a Comment