Thursday, November 27, 2014

ጋዜጠኛ መልካም ሞላ በድጋሚ ተከሰሰች!

የ‹‹ ቆንጆ ›› መፅሔት ዋና አዘጋጅና የ‹‹ ጃኖ›› መፅሔት ዓምደኛ የነበረችው መልካም ሞላ ሀምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ዜና እወጃ ላይ ‹‹ህገ-መንግሥቱን በኃይል ለመናድ በመንቀሳቀስ፣ ህዝቡን ለዓመፅ ማነሳሳትና የሽብር ስራን ለምስራት ማቀድ ›› በሚል የፍትህ ሚኒስቴር ክስ የመሰረተባት መሆኑን በዜና አቅራቢው ተመስገን በየነ በኩል የተከሰሰች መሆኑን የሰማችና ከዚያም ባሉት ተከታታይ ቀናት የማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ለጥያቄ እንደሚፈልጋት ጥሪ ከደረሳት በኋላ የምትወዳትን ሀገሯን፣ ሙያዋንና ቤተሰቦቿን ትታ ዿግሜ 4 ቀን 2006 ዓ.ም ከሀገር መሰደዷ ይታወቃል ፡፡

ይሁን እንጂ የማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ቢሮ በያዝነው ህዳር ወር 2007 ዓ.ም ከሀገር ከመውጣቷ በፊት በዋና አዘጋጅነት ትሰራበት ለነበረው የ‹‹ቆንጆ›› መፅሔት ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ካሣን የወንጀል ምርመራ ቢሮ በማስቀረብ በጥር ወር 2006 ዓ.ም ማለትም ከአንድ ዓመት በፊት ‹‹ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መ/ቤት ምን እየሰራ ነው ? በሚል ርዕስ ሥር በኢትዮጵያ የግብረ ሰዶማዊነት መስፋፋትን በተመለከተ በፃፈችው ፁሁፍ ‹‹ ህዝቡ በመንግሥት ላይ እምነት እንዲያጣ አድርጋለች ›› በሚል ክስ እንደመሰረተባትና ለጥያቄ እንደሚፈልጋት በመግለፅ ሥራ አሥኪያጁ እንዲያቀርባት ታዟል፡፡ ይሁንና ጋዜጠኛ መልካም ሞላ በሀገር ውስጥ የሌለች በመሆኑ ከዚህ በፊት በሎሚ፣ በጃኖ ፣በአዲስ ጉዳይና በሌሎች የመፅሔት አሳታሚዎች ላይ እንደቀረበው የአሸባሪነት ክስ በቆንጆ መፅሔት አሳታሚ ላይም ይህ የክስ ፋይል እንደሚከፈት የታመነ ሲሆን ለጊዜው ግን ከአንድ ዓመት በፊት በፃፈችው ፁሑፍ ‹‹ ህዝቡን በመንግሥት ላይ እምነት እንዲያጣ አድርጋለች›› በሚል ክስ የቀረበባት ጋዜጠኛ መልካም ሞላን ካለችበት ቦታ አስሮ እንዲያቀርብ የፌደራል ፖሊስ የከባድ ወንጀል ምርመራ ክፍል የታዘዘ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

No comments:

Post a Comment