Wednesday, August 20, 2014

የዓረና-መድረኽ ሰለማዊ ሰልፍ ለሁለተኛ ግዜ ተከለከለ…!

ዓረና-መድረኽ ለእሁድ 18 / 12 /2006 ዓ/ ም በመቐለ ከተማ ሊያካሂደው ያሰበው ህዝባዊ ሰለማዊ ሰልፍ ኣስቀድመው የተያዙ የህዝብ በኣላትና መንግስት የያዛቸው ዝግጅቶች፣ ህጋዊ ያልሆነ በከተማው ኣስተዳደር የተዘጋጀ የሰለማዊ ሰልፍ ስነ ስርዓት ፎርም መሙላት ኣለባቹ በሚል ተልካሻ ምክንያት እንዳይካሄድ ኣዝዘዋል።

መቐለ ህወሓት ደግፈህ ካልሆነ ተቃውመህ ሰልፍ የማታደርግባት ብቸኛ የኢትዮዽያ የክልል ከተማ ናት። ህወሓት የመቐለ ጎዳናዎች በየቀኑ ማርሽ ባንድ ኣጅቦ እየዞራቸው እንደሚውል የከተማው ኑዋሪ የሰለቸበት ተግባር ነው።

ህወሓት ጠንቋይ ሰለማዊሰልፍ ከፈቀድክ ከስልጣንህ ትወርዳለህ ብሎ የተናገረው እስኪ መስል ድረስ ሊፈቅድ ኣልቻለም። ለነገሩ ኣባባ ታምራት ኣንድ ወቅት “…ከኣንድ ሰው በቀር ሁሉም የኢኣዴግ ሚኒስትሮች መጥተው ሰግደውልኛል….” ማለቱ ይታወቃል።

መቐለና የመቐለ ህዝብ ተቃውሟቸው በሰለማዊ መንገድ፣ ባደባባይ እንዲገልፁ ኣልተፈቀደላቸውም።
ከዚህ በፊትም ሰላም የሚያስከብር በቂ የፖሊስ ሃይል የለንም በማለት ሰለማዊ ሰልፍ እንዳይካሄድ መከልከላቸው የሚታወስ ነው።

ህወሓት በ 1968 ዓ/ ም ያወጣው ፕሮግራሙ “… የትግራይ ህዝብ ሃሳቡ፣ ተቃውመውና ድጋፉ በነፃነት በሰለማዊ ሰልፍ እንዲገልፅ እታገላለው..” የሚል ነበረው። ክልከላው ሊዚህ ዓለማ የተሰዉ ከ60 ሺ ሰማእታት ከንቱ የሚያስቀር ተግባር ነው።

የተከበራቹ ኢትዮዽያውያን ህወሓት መቐለ ከተማ ብቻው የሚፈነጫባት ከተማ ኣድርጓታልና መቐለ ከተማ ሰለማዊ ሰልፍ ይፈቀድ…! ብላቹ ሰልፍ ኣድርጉልን።

ይኸው እኛም ይሄ መብት ለማረጋገጥ ተግተን እየታገልን እንገኛለን።
የክልከላው ደብዳቤ ትናንት የተሰጠን ሲሆን እነሱ ግን ወድያው እንደደረሳቸው መልስ የሰጡበት ለማስመሰል ወጪ የተደረገበት ቀን ወደሁዋላ መልሰው ፅፈውታል።

ለምን እንደዚህ እንዳደረጉ ስንነግራቸው ኣምሽተው እንደፃፉትና ቢሮኣችን እንዳላገኙን ሳያፍሩ ነግረውናል።

ነፃነታችን በእጃችን ነው…!


No comments:

Post a Comment