Friday, March 6, 2015

በአፋር ወጣቶች ለስለላ እየታፈሱ ነው

የካቲት ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአፋር ነጻ አውጭ ድርጅቶች በአካባቢው እያደረሱት ያለው ተጽአኖ ያሰጋው መከላከያ፣ በአፋር የተለያዩ የጠረፍ ከተሞች የሚገኙ ወጣቶችን በማፈስ ላይ ነው። ስማቸው ለደህንነት ሲባል እንዳይጠቀስ የጠየቁት ወላጆች በደርግ ጊዜ የቀረው አፈሳ በክልሉ እንደ አዲስ መጀመሩን ተናግረዋል።

በርካታ ወጣቶች አፈና በመፍራት ጫካ መግባታቸውንም ነዋሪዎች አክለዋል። አርዱፍ፣ አፋር ጋድሌና የአፍዴራ ወጣቶች በቅርቡ ግንባር መፍጠራቸውን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል። በጉዳዩ ዙሪያ የክልሉን የጸጥታ ዘርፍ ክፍል ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።


No comments:

Post a Comment