Sunday, March 1, 2015

እንደግብጻውያን ገዳማት እና ሀገራችን እንዳይፈርሱ ዘብ እንቁም (ከ ዘአብርሃም ብሎግ)

በአለም መፋረጃ ወቅት ላይ እንገኛለን። ካልጠፋ ቦታ ለሺ ዘመናት ስነምህዳሩን ጠብቆ ተከብሮ የኖረውን የዋልድባ ገዳምን ማረስ እንዲሁም የዝቋላ ገዳም ላይ እንውጣና ክርስትና ያልሆነ ሌላ እምነት /የእሬቻ በዓልን/ እናክብረበት  ማለት  ፍርጃ እንጂ ምን ይባላል። ከድሮ ጀምሮ ቤተክርስቲያን ሲያቃጥሉ ታቦት ፤መስቀል፤ ወድ የብራና መጽሃፍት ሲሰርቁ ኖረው አሁን ደሞ  የሁለት የተለያዩ ዕምነት ተከታዮችን ለማጣላት ጀመሩ።

በኢትዮጵያ አብያተ ክርስትያናት ላይ ብቻ ሳይሆን  ጥንት ጳጳስ ትልክልን የነበረችው የግብጽ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን የአባ መቃርዮስ ገዳምም እንደዋልድባ ገዳም ካልታረሰ ተብሎ ተፈርዶበታል። ገዳሙ በ360ዓም ኣካባቢ በታላቁ ኣባት ቅዱስ መቃርስ የተመሰረተና ታዋቂዎቹ የቤተክርስቲያን ኣባቶች  እንደ ሙሴ ጸሊም፥ዮሃንስ ሓጺር፥ የ አሌክሳንድሪያው ቅዱስ መቃርስ የመሳሰሉት ኣባቶች  ፈለጋቸውን መከተል የጀመሩበት ነው።።እኚሕ ኣባ መቃርስ ከግብጽ አልፎ ለ ኢትዮጵያ፥ ለግሪክ፥ ለፍልስጤም፥ ለአርመን፥ለእስያውያን፥ለስፔን፥ለጣልያን  ሰዎች ምንኩስናን ያሳዩ  ከአራት ሺህ  በላይ ተከታዮች ያፈሩ  መንፈሳዊ አባት መሆናቸው በሰፊው ተጽፏል።



አይሲስ የግብጽ ክርስቲያኖችንና ገዳም

የቅዱስ መቃርስ ገዳም  ከካይሮ ደቡብ ምዕራብ 72 ማይል ርቀት ወደ በረሃማው አለክሳንድሪያ ኣቅጣጫ ሲሄዱ በዋዲ አል ናትሩን ጥንታዊ ከተማ ላይ የሚገኝ ሲሆን ፋዩም የተባለች ኣውራጃን ከዖሲስ ጋር የሚያገናኝ መንገድ ስራ በዚህ ገዳም መሃል ማለፉ ነው ችግሩን ያመጣው። የዚህ የመንገድ ፕሮጀክት የገዳሙን የዉሃ ቧንቧ የሰበረ እንዲሁም የገዳሙን  ልማት የሚያጠፋ መሆኑን ለግብጽ መንግስት ቢያሳውቁም ምላሽ ኣላገኙም። የግብጽ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያንና መነኮሳቱ አማራጭ ፕላን ቢያቀርቡም እንደኛው የዋልድባ ገዳም በገዳማቸው ካላለፍኩ የሚለው መንግስት ሲያዘናጋ ቆይቶ ቡልደዘር ላከባቸው። ገዳሙ በተለይም ደቡባዊ ክፍሉ የመጥምቁ ዮሃንስና የነብዩ ኤልሳዕ  መቃብር ላይ ያረፈ መሆኑ  በ 11ኛውና 16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተገኙት የታሪክ መዛግብት የመሰከሩለት ጥብቅ የአርኪዎሎጂ ሳይት በመሆኑ ጉዳዩ የሚመለከተው የግብጽ Antiquity ሚንስቴር በሃሳብ ደግፏቸው ነበረ።

ከወርሃ መስከረም መባቻ እንደተጀመረ የሚነገረው ተቃውሞ ኣይሎ ከ 85 በላይ  የሚሆኑ የኮፕቲክ መነኮሳት ጥንታዊ ቦታችንን አናስነካም በማለት ቡልደዞሮቹ የሚሄዱበት መንገድ ላይ በመነጠፍ  መንገድ በመዝጋታቸው ፕሮጀክቱ ለጊዜው ቆሟል። ተቀጣሪ የመንገድ ሰራተኞቹም ኣላሁዋክበር በማለታቸው ትኩረቱ እስላሞች  ቤተክርስቲያንን የማጥፋት ዘመቻ  አድርገው የቆጠሩት  ግን ሞልተዋል።

በተለይ አይሲስ የተባሉ ጸረ ታሪክና ጸረ ሰው ቡድኖች 21 የግብጽ ኮፕቲክ ክርስቲያኖችን አንገት እንደጎመን ከቀነጠሱ በኋላ ክርስቲያኖቹ ሆድ ብሷቸዋል። የዛን ጊዜ ታሪክ አሁን እያመጡ ያባብሱታል። ጥንታዊ መዛግብትን  የአርኪዎሎጂ ጥናት ቦታዎችን መጠበቅ  ሁሉም ሊያከብረው የሚገባ ሃላፊነት ነው ።  የኋላ ታሪካቸውን ለማየት ለ ጂሃዳውያኑ ኣይሲሶችም ይጠቅማሉ። የምናየው ቅዱስ ቁርኣንን ብቻ  ነው ካሉም “ከጅሃድ አላማዎች አንዱ አይሁድ እና ክርስቲያኖችን ማጥፋት ሳይሆን የአይሁድ እና የክርስቲያን ቤተ አምልኮዎችን ከጥቃት መከላከል ነዉ “ የሚል ጽሁፍ በቅዱስ ቁርኣን 22፥39-40 ተጽፏል ።  ቡሃሪ እንደዘገቡትም  “ሽታዋ አርባ አመታት ከሚያስኬድ እርቀት ላይ የሚገኝ ቢሆንም ሙስሊም ያልሆነን ሰላማዊ ሙአሂድ) የገደለ የጀነትን   የሚለው መመሪያ  አይሲስና አክራሪነት  አላማ ያላቸው ሊያውቁት ያስፈልጋል። ከእስልምና ዲን አስተምህሮ ዉጪ አንገት መቅላት ከጓሮ ጎመን እንደመቀንጠስ ሲቆጠር ዝም ብሎ ማየት አንድም መጨንገፍ ነው አለበለዚያም ተባባሪነት ነው።ተባባሪነቱም የደም ምስ ላለበት ለሰይጣን አምላኪ እንጂ ፈጣሪን አያቅም።

እስላማዊ ግዛት ለመመስረት ነው ብሎ በቅርቡ ማርሽ ቀይሮ የተነሳው  አይሲስ

ሙስሊሞችን ጨምሮ ያፈኗቸው፥ በ ኣሰቃቂ ሁኔታ የገደሏቸው ሰዎች ብዛት የትየለሌ ናቸው

የሱኒ ሙስሊም ቤተመጻህፍት፥የ205  አመት ዕድሜ ያለው የዱሜኒካን ገዳም፤ በጣም ጥንታዊ ነው የሚባልለት የሞሱል ከተማ ላይብራሪን መመዝበር ከ ታህሳስ እንደጀመሩና ይህም በጣም ልብን እንደሚነካ አንድ ስሙ እንዳይነገር የፈለገ የሙስል ዩኒቨርሲቲ መምህር ተናግሯል። ይህ ታሪክን የማጥፋት ነውጠኝነት ከቀጠለ የ አሌክሳንድሪያ ላይብራሪ የግብጻውያን ፒራሚዶች ወዘተ በ አረቡ አለም ያሉ አይከኖች  መውደማቸው ኣይቀርም።



አይሲስ  በኢትዮጵያ ዋልድባና ዝቋላ ገዳማትን

እንደ አምስት አመት  የአረቦቹ አይሲስ ዕቅድ ከሆነማ  ኢትዮጵያን ጨምሮ ከምድር ወገብ በላይ ያሉትን የአፍሪካ ሀገራት በሙሉ እስላማዊ ግዛት ለማድረግ ተወጥኗል።ይህ ኢትዮጵያን፤ሱዳንን  ቻድን፤ ሶማሊያን ኤርትራን ያካትታል ለሚባለው ኢምሬት The LAND of Habesha /የሃበሻ ግዛት/ የሚል ካርታ ካለፈው ሃምሌ ጀምሮ ተነድፏል።  ኦሮሚያን ለመገንጠል እንጂ ሃብሻ ተብሎ ለመጠራት የሚከብዳቸው ኦሮሞዎች ቢኖሩም ከምድር ወገብ በላይ እስከ ግብጽ ያለው በሙሉ የሃበሻ ግዛት ተብሎ እንደሚጠራ አረቦቹ ጅሃዳውያን የኛዎቹ ላይ ከታሪክ ማህደር ጠቅሰውባቸዋል። እነሱ ግንየወሃቢዝም ሱኒ ዕምነት አክራሪነት ለኢትዮጵያ ጨዋ ሙስሊም አይሆንም ብለው መከራከሩን ተተው አይሲስን በማውገዝ ፋንታ  እኛ ኦሮሞዎች ሶማሌዎች ሃበሻ ስላልሆንን ለምን አይሲስ ከሃበሾች ጋር ካርታ ሰራልን አያሉ ጊዜያቸውን እንደሚያጠፉ ላነበበ ለሰማ በጣም ያሳዝናሉ። እንግዲህ በስንቱ እንባላ?

በኢትዮጵያ ካልጠፋ ቦታ ለ700 ዓመታት ያህል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ይዞታ ስር በሚገኘው በታላቁ የዝቋላ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም ውስጥ የእሬቻን የአምልኮ ሥርዓት እፈጽማለሁ በማለት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት   ወሰነ ። ወስኖም አልቀረም በብሔራዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ ጭምር ቀን ቆርጦና ወስኖ ዜናውን አስነገረ ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ መነኮሳት ቅዱስ ፓትርያርኩ  አቡነ ማትያስ በደብዳቤ ፣ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕም በደብዳቤ ፣ የገዳሙ ማኅበረ መነኮሳት ግን በግንባር ተቃውሞአቸውን አቅርበዋል ። ቅዱስነታቸው እንደውም በሚድያ የክልሉ መንግሥት ያስተላለፈውን በጽኑ በመቃወም ማስተካከያና ስህተት መሠራቱን ጭምር በዚያው በሚድያ የክልሉ መንግሥት እንዲያርም አሳስበዋል።

ይሁን እንጂ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በቅዱስ ፓትርያርኩ ፣ በሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ፣ በገዳሙ መነኮሳትና ፣ በኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን የቀረበለትን ሁኔታው አደጋ አለውና ይስተካከል የሚለውን የተማጽኖ ቃል ወደ ጎን በመተው ይባስ ብለው “እንደውም እናንተ መጣችሁብን እንጂ አልመጣንባችሁም ፣ ስትፈልጉ ወደ ክልላችሁ ሂዱ ፣ በዝቋላ እንኳን ሃውልት ማቆምና የእሬቻን ማክበር አይደለም ውሻ አርደን መስዋዕት ብናቀርብ እንኳ መብታችን  ። የሚከለክለንንም የሚል ዛቻ እየተሰማ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል በቅድስናው ቦታ እርኩስት ቆሞ ስታይ አንባቢው ያስተውል ይላል ቅዱስ መጽሃፍ።ያ የአለም ፍጻሜ መድረስ ምልክት ነው።

ይህ ነገር እዚህ ላይ በእንጭጩ ካልተቀጨና ማረሚያ ካልተደረገለት በቀር ወደፊት በሃገራችን በኢትዮጵያ በሕዝቧ እና በእምነቶች መካከል ከፍተኛ የሆነ መቃቃርና ያለመተማመን ይፈጠራል እያለ ስጋቱን ይገልጻል በስብከት አገልግሎቱ የሚታወቀው መምህር ዘመድኩን በቀለ። “ካልጠፋ ቦታ ባለቤቱን እንኳን ሰው ሰይጣን ራሱ የሚያውቀውን ቅዱስና ታሪካዊ ሥፍራ መተናኮል ለማንኛችንም አይበጅም ። በእስራኤል ብዙ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ሥፍራዎች በፍልስጤማውያን አረብ የእስልምና እምነት ተከታዮች ነው በክብር ተጠብቀው የሚገኙት ። በተለይ ጌታ በተወለደባት የቤተልሔም ዋሻ ፤ ቤተ መቅደሱ የሚገኘው በፍልስጤም ሲሆን ባለቤቶቹ ክርስተያኖች ናቸው ። ጠባቂዎችና ተንከባካቢዎቹ ደግሞ ፖሊስና ወታደሮቹ ጭምር ሙስሊሞች ናቸው ። እነዚህ ሙስሊሞች ክርስቲያኖችን ልቀቁልን ፣ ጥፉ ከዚህ ፣ አይሉም  ብለውም አያውቁም ።

ጌታ የተሰቀለበትን ቀራንዮ ፣ የተጠመቀበትን ዮርዳኖስን ሌሎችም ብዙ የክርስቲያን ይዞታዎች በእስራኤል አይሁዶች ሀገር ውስጥ ነው ያሉት  አይሁድ ደግሞ ኢየሱስ የሚለውን ስም መስማት እንኳን የማይፈልጉ ናቸው ። አይሁድ ጌታን የገረፉት ፣ የሰቀሉት ፣ የገደሉት ፣ እነሱ መሆናቸውን በኩራት እየተናገሩም ቢሆን ። ክርስቲያኖችን ውጡልን ፣ ተመለሱ ፣ እዚህ ጋር ሙክራብ ሠርተን መስገድ መብታችን ነው ብለው ክርስቲያኖችን ተተናኩለው አያውቁም ። እንደውም ክርስቲያኖች የአምልኮ ስርአታቸውን ሲፈጽሙ የሚረብሻቸው ነገር እንዳይፈጠር ዘመናዊ መሳርያ በታጠቁ የተደራጁ ወታደሮች 24 ሰዓት ሙሉ ዓመት እስከ ዓመት ጥበቃ ያደርጋሉ እንጂ ።

የእኛን ጉዳይ ግን አሁን በዝቋላ የተፈጠረውን ክስተት ማለትነው ነገሩን  በአትኩሮት ላየው  ” ጠብ ያለሽ በዳቦ ይመስላል

ከዝቋላ ገዳምን ከመዳፈራቸው በፊት በተቃውሞ የተነሳ ተቋርጦ የነበረው በዋልድባ ገዳም የሚያልፈው የመንገድ ግንባታም እንደገና መጀመሩን ኢሳት ቴሌቪዥንና ራድዮ  በዚሁ የካቲት ወር መዘገቡ ይታወሳል።

ከወልቃይት ተነስቶ በዋልድባ አብረንታት ገዳም አድርጎ ወደ ማይፀብሪ የሚሰራው መንገድ በ2004 ዓም በገዳሙ ፣በአካባቢው ሕብረተሰብ እና  በውጭ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጠንካራ ተቃውሞ የተነሳ ተቋርጦ የቆየ ቢሆንም መንግስት ወደ ገዳሙ የሚገባው ለአፈር ምርምር እንጂ መንገድ ለመስራት አይደለም በሚል የመንግስት ካድሬዎችና አንዳንድ መነኮሳትና የቤተክነት ሃላፊዎች  የሀሰት ምስክርነት እንዲሰጡ አድርጎ ህዝቡን ካዘናጋና “ገዳሙ አይታረስም ብለው የሚቃወሙትን ጠንካራ መነኮሳት” ከገዳሙ ካስወጣ በኋላ፣  አሁን የመንገድ ስራውን እንደገና መጀመሩ ህዝብንም ሃይማኖትንም መናቅ ነው።

በመነኮሳቱና ህዝቡ አቋም የተናደዱት ባለስልጣኖች “ስታስቀሩት እናያለን” በማለት በመነኮሳቱ ላይ እስከመዛትም ደርሰዋል።

በሶ በስንቱ ልበጥበጥ እንዳለችው ሁሉ እነዚህ ጸረ ቤተክርስቲያን እና ጸረ ኢትዮጵያ አካላት ሲያሻቸው በሰሜን ዋልድባ ሲያሻቸው ከመሃል ሃገር ዝቋላ ተነሱ እያሉ ይበጠብጡናል። እነዚህ  ለሚሰራው ስራ መንገድ ጠራጊ  ሚና የሚጫወቱ ሹማምንት  ካሁኑ እረፉ ሊባሉ

ካልሆነ ግብጻውያን የ አባ መቃርዮስ ገዳም ከሚታረስ ትራክተሩ በኛ ላይ ይሂድ ብለው  መሬቱ ላይ እንደተነጠፉ እኛም ስለዋልድባ ና ዝቋላ ገዳም በጠቅላላው ለሃገራችን ልንዋደቅ የምጽኣት ቀን ኣሁን ነው።


No comments:

Post a Comment