Monday, March 16, 2015

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ከሥራቸው ተባረዋል:: 

"ተወይኖብኛል" ይላሉ
"ዩኒቨርሲቲው እኛን harass ከሚያደርግ የተጭበረበር ዶክመንት ይዞ ፕሮፌሰር የሆነውን ሰውዬ (ቆስጠንጢኖስ በርሄ) ወዲያውኑ አታባርርም? ፀሓይ የሞቀው ውሸት እንደሆነ ግልጽ ሆኗል ብዙ ሰው ነው አንጀቱ የራሰው ልንገራችሁ እሱ አሁን ተዋርዶ መባረር ነበረበት"

"አሁንማ ጉድ ፈልቷል እኔ የዲግሪ ተማሪዎችን አቆሜ ነበር፣ ለሁለት ዓመታት:: በተገቢ ሁኔታ ያልተማሩ ልጆች ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ:: ተማሪዎች ሲወድቁ ደግሞ አትጣሏቸው C እና D ስጧቸው ይላሉ:: F ከሰጠህ አስተማሪ አንተ በደንብ ስላላስተማርክ ነው፣ በደንብ አስተምራችው...ሥራ ይበዛብሀል:: ስለዚህ C እና D እየሰጠህ ዝም ብለህ ማሳለፍ ነው:: ስለዚህ ይኼ አንድ ቦታ መቆም አለበት:: የትምህርት ሥርዓቱ ቀውስ ውስጥ ነው::"

"ትምህርት ቀውስ ውስጥ ገብቷል! ዝም ብሎ ቁጥር ...number...እነሱ በፖሊሲ 10ሺህ PHD, 50ሺ MA ይልሀል በ5 ዓመት... ከዚያ ይህን ያህል ተገበርን ይልሀል። እኔማ ተረከቡኝ ብያለሁ የሚረከበኝ አጣሁ:: ይሄ PHD የሚባል ስም... ዶክትሬቴን ውሰዱሉኝና አቶ በሉኝ ብያለሁ:: እባካችሁ ተዘከሩኝ "አቶ ዳኛቸው በሉኝ!"


No comments:

Post a Comment