Saturday, March 14, 2015

ወይዘሮ አዜብ መስፍን በደህንነት ሹሙ ጥርስ ውስጥ ዳግም መታኘክ ጀምረዋል::

መውደቂያው የደረሰው ወያኔ እርስ በርሱ መበላላት ጀምሯል: ወሳኝ ወቅት ላይ ነን ፤የደህንነት ሹሙ ጌታቸው ማለት እንደ ወይዘሮ አዜብ አነጋገር “…ሰታዊ መሲሉ ክምተመን ዝናከስ..” እንደሆነ ሲታወቅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወይዘሮ አዜብ በቤተሰቦቻቸው ስም ያቋቋሙት ድርጅት እና ያፈሩት ሃብት እና ንብረት ላይ ክትትል እንዲደረግ አቶ ጌታቸው አሰፋ ቡድናቸውን ማዘዛቻው ወይዘሮዋ በደህንነት ሹሙ ጥርስ ውስጥ ዳግም መታኘክ መጀመራቸው
ወዳጆቻቸውን ተገን በማድረግ በቤተሰቦቻቸው ስም የሚገቡ ከባድ እና ቀላል መሳሪያዎች እንዲሁም የተለያዩ ቁሳቁሶች ቀረጥ ስለማይከፈልባችው ጥያቄ በአዜብ መስፍን ላይ ቢያስነሳም ወይዘሮዋ ከተጠየቅን አብረን ነው መጠየቅ ያለብን ሲሉ ከዚህ ቀደም መልስ መስጠታቸው እና ከዘረፋ ጋር ጋር የተያያዘ ጥቄዎች ሲነሳባቸው በጄኔራሎች ካኪ ስር መደበቅ ተግባራቸው መሆኑ ለደህንነት ፈላጭ ቆራጮ እንዳልተዋጠላቸው ታውቋል::

ከዚህ ቀደም በቤተመንግስቱ የውስጥ ሽኩቻ ውስጥ ቂም በቀል እንዳለባቸው የሚነግርላቸው የደህንነቱ ሹም አቶ ጌታቸው ወይዘሮ አዜብን አጥምዶ የሰው መሳቂያ ለማድረግ ከማሴር አልተቆጠቡን ሲሉ የወይዘሮዋ የቅርብ ሰዎች በምሬት ይናገረሉ:: ወዳጅ መሳይ ተናዳፊ እባብ ሰታዊ መሲሉ ክምተመን ዝናከስ ብላ አዜብ የምትጠራው ጌታቸው በዘመዶቿ ስም ያፈራችውን ንብረት የመውረስ እና ሸጦ ገንዘቡን በሌላው እንደለመደው ከሃገር የማሻገር እቅድ እንደያዘ የቅርብ ወዳጆቿ አክለው ገልጸዋል:: በደህንነት ሰዉየውና በሴትየዋ መካከል ያለውን ቅራኔ ፈትቶ ጉዳዩን ለማረጋጋት አቶ በረከት ስምኦን እና ጄኔራል ሳሞራ ጥረት ላይ መሆናቸው ታውቋል::

በውጪና በውስጥ ስልጣኑን ለህዝብ እንዲያስረክብ ትልቅ ጫና የበዛበት ወያኔ ከሃገር እና ህዝብ ሃብት በተጨማሪ እርስ በርሱ መበላላት እና መዘራረፍ የጀመረ ሲሆን ኢትዮጵያውያን ትግላችንን አጠናክረን በመቀጠል ይህንን የበሰበሰ ዘራፊ ስር አት ለማስወገድ በጋራ እና በአንድነት በመታገል የዜግነት ሃላፊነታችንን መወጣት አለብን::


No comments:

Post a Comment