Thursday, June 5, 2014

በደብረዘይት ነዋሪዎች በግዴታ ብሄራቸውንና ሃይማኖታቸውን እንዲያስመዘግቡ ተደረጉ

ኢሳት ዜና እንደዘገበው በደብረ ዘይት ነዋሪዎች ብሄራቸውንና ሃይማኖታቸውን እንዲያስመዘግቡ መገደዳቸው አስግቶዋቸዋል። በከተማዋ ቀበሌ አንድ የሚገኙ ነዋሪዎች እንደገለጹት ፖሊሶች ከስቪል ሰራተኞች ጋር በመሆን ቤት ለቤት እየዞሩ የነዋሪዎችን ብሄር እና ሃይማኖት ሲመዘግቡ ውለዋል።
“የምዝገባው አላማ ሰዎችን እየመረጡ ለማፈናቀል ሊሆን ይችላል” በማለት ስጋታቸውን የገለጹት ነዋሪዎች፣ብሄርን መመዝገቡ ለምን እንዳስፈለገ ሲጠይቁ ከላይ የተላለፈ መመሪያ ነው በሚል እንደተነገራቸው ገልጸዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የከተማውን ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሃላፊዎች ለማግኘት ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።
አንዳንድ አስተያየት የጠየቅናቸው ነዋሪዎች በበኩላቸው ምዝገባው  ከመጪው ምርጫ ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
በክልሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ ያለው አለመረጋጋት እና በገዢው ፓርቲ እንደተቀነባበረ የሚታመኑ አልፎ አልፎ የሚነሱ አካባቢን ማእከል ያደረጉ ግጭቶች በቀበሌው ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ተጨማሪ የስጋት ምንጭ ሆኗል።
ምዝገባው በመላው የክልሉ ከተሞች ይካሄድ አይካሄድ ለማወቅ አልተቻለም

No comments:

Post a Comment