Sunday, June 22, 2014

በአዋሳ ችግር የገጠመው አንድነት ፓርቲ 

ኢሳት ዜና :-በመጪው እሁድ በአዋሳ የሚካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ በቅስቀሳ ላይ የሚገኘው አንድነት፣ ሶሰትአባሎቹ እንደታሰሩበት አስታውቛል።

አዲስ አበባ መስተዳድር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ያሬድ አማረ በቅስቀሳ ላይ የነበሩ 3 ሰዎች መያዛቸውን ገልጸዋል።

መስተዳድሩ የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ለመስጠት በሂደት ላይ በመሆኑ መቀስቀስ አትችሉም መባላቸውን የገለጹት አቶ ያሬድ፣ የእውቅና ጥያቄ ካስገቡ አንድ ወር ሞላቸው በመሆኑ በመስተዳድሩ የቀረበውን ምክንያት እንደማይቀበሉት ተናግረዋል።

የመስተዳድሩ ባለስልጣናት አዋሳ ከተማ ውስጥ የድምጽ ማጉያ  መጠቀም አይቻልም የሚል አቋም እንዳላቸው የገለጹት አቶ ያሬድ፣ ሰልፉን እሁድ እንደሚያካሂዱ በእርግጠኝነት ገልጸዋል።

አንድነት “የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል አላማ ሰልፉን የሚካሂድ ሲሆን፣ በኦሮምያ መንግስት የወሰደውን እርምጃ፣ በክልሉ ከማንነት ጋር በተያያዘ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ፣ የሙስና መበራከትና ሌሎችም ጉዳዮች አንስቶ ያወግዛል።

መድረክ በቅርቡ በአዋሳ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጉ ይታወሳል።


No comments:

Post a Comment