Thursday, August 3, 2017

የአገሪቱን ከባድ ሚስጢር ለኢሳት አሳልፎ ሰጥቷል በተባለው የኢንሳ ሰራተኛ ላይ የቀረበው የክስ ቻርጅ አገዛዙ ለሳተላይት አፈና በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እንደሚያወጣ አረጋገጠ

በዝግ ችሎት የታየው የክስ ሂደት እልባት አግኝቷል።
ጸጋዬ ተክሉ ይባላል። በመከላከያ ዩኒቨርስቲ ከ1992 ዓም ጀምሮ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ተምሮ፣ በዚሁ ተቋም ውስጥ ተቀጥሮ ሰርቷል። ምርጫ 97ትን ተከትሎ በከፍተኛ የህልውና ስጋት ውስጥ የወደቀው የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ከውጭ አገር ወደ አገሪቱ የሚተላለፉ ሚዲያዎችን ማፈን አስፈላጊ ነው ብሎ በማመኑ የተለያዩ የማፈኛ መሳሪያዎችን ለመግዛት የውጭ ገበያዎችን ማሰስ ጀመረ። ለስራው ያስፈልጋሉ ያላቸውን ታማኝ ኢንጂነሮች እያፈላለገ ቀጠረ። የአፈናውን ስራ እንዲሰራ ደግሞ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) የተባለ ተቋም ለመጀመሪያ ጊዜ በ1999 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 130/1999 መሠረት አቋቋመ፡፡ የኤጀንሲውን ተግባር እና ኃላፊነት እንደገና ለማሻሻል ደግሞ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 250/2003 እንዲሁም በድጋሚ በ2006 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 808/2006 የኤጀንሲው ተግባሮች እና ኃላፊነቶች ተሻሽለው እንዲቋቋሙ አደረገ። በርካታ በሳይንስና በሌሎችም የትምህርት ዘርፎች የሰለጠኑ ሰራተኞች ሲቀጠሩ ጸጋዬም በ1998 ዓም ተቀጠረ።

የኢንፎርሜሽን ደህንነት ኤጀንሲ ብዙውን ጊዜ በእንግሊዝኛ ምህጻረ ቃሉ ኢንሳ እየተባለ በሚጠራው ተቋም ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ጥብቅ የተባሉ አገራዊ ሚስጢሮችን የመጠበቅ ግዴታ ተጥሎባቸዋል። ግዴታቸውን በማይወጡት ላይ በአገር ክዳት ወይም በስለላ ወንጀል ተከሰው እስከ ሞት የሚደርስ ቅጣት ይጠብቃቸዋል።
የኢንሳን መረጃ ለኢሳት ተላልፎ እየተሰጠ ነው በሚል በርካታ ሰራተኞች በጥርጣሬ ሲታሰሩና ሲባረሩ ጸጋየም በጥርጣሬ ከተያዙት ውስጥ አንዱ ነው። ጸጋዬ የቀረበበት ክስ “የኢንፎረሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ባለሙያ ሆኖ ሲሰራ በሃላፊነቱና በሙያው የአገሪቱን ጥቅም ለማስጠበቅ በሚስጢር እንዲጠብቅና እንዳይገለጽ የተደረገውን ሚስጢር ሆን ብሎ” ለኢሳት ገልጿል የሚል ነው። ክሱ ሁለት መልክ ያለው ሲሆን አንደኛው በአገር ክዳት ሌላው ደግሞ ለመንግስት ጠላት ለሆነ እና የግንቦት7 የሽብር ቡድን ልሳን ለሆነው ኢሳት የስለላ ስራ መስራት የሚል ነው።
የኢንሳ ጠበቆችም ክሳችንን ያስረዳልናል ያሉዋቸውን የሰነድ ፣ የኢሜል እና የድምጽ ማስረጃዎችን አቅርበዋል።
ለኢሳት ተሰጠ የተባለው ከባድ ሚስጢር የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ኢሳትን ጨምሮ ሌሎችን ወደ ኢትዮጵያ የሚተላለፉ ስርጭቶችን ለማፈን የሚጠቀምባቸውን ቴክኖሎጂዎችና ወጪያቸውን በዝርዝር የሚያመለክት ነው።
የኢንፎርሜሽን ደህንነት ኤጀንሲ “ ከ2007 ዓም ጀምሮ በተቋሙ ኮሜርሻል ሚዲያዎችን ሳይቀር እያፈነ መሆኑ፣ የኢትዮጵያ መንግስት የማፈኛ መሳሪያ ጣቢያዎች እንደ ራዲዮ ጣቢያ እንደሚሰሩ፣ 24 ሰአት ሙሉ ሰታላይት ስርጭቶች በትራንስሚተር ጃም እንደሚደረጉ፣ ለዚህም ስራ የተለያዩ የጃሚንግ ስዊቺንግ ቴክኖሎጂ እንደሚጠቀም፣ መሳሪያውም ዘመናዊ ( አድቫንስ) እንደሆነ፣ የጃሚንግ ኦፐሬሽን ለመስራት ምን ያክል ወጪ እንደሚደረግ፣ መሳሪያው ለ3 ሰአታት እንደሚሰራ ፣ ትራንስሚተሮቹ ጃም እያደረጉ አሉት የኤርትራ፣ የኦነግ፣ የኢሳትና ከተለያዩ ስቴሽን የሚመጣ ሲግናልን የሚችሉ ከ12 በላይ እንዳሉና እነዚህም ተቀናጅተው የሚሰሩ መሆኑን፣ የሳተላይት ቴሌቪዥን ካውንተር ጃሚንግ ያላቸው ትራንስሚተሮች ያሉዋቸው መሆኑን፣ የማፈኛ መሳሪያዎች ኖርማል የሬዲዮ ጣቢያ እና ሳተላይት ትራንስሚተር እንደሆኑ ፣ እነዚህ መሳሪያዎች ተሸካሚውን በ200 ሜጋ ሀርዝ ኬሩን ከፍ በማድረግ በፍርኩዌንሲ እንዴት እንደሚተላለፍ ፣ መረጃ እንዴት እንደሚሰበሰብ፣ የተሰበሰበው መረጃ በባለሙያ ተተንትኖ ወደ ሚመለከተው እንዴት እንደሚተላለፍ በዝርዝር መረጃ ሰጥቷል” የሚል ክስ አቅርቧል።
ጸጋየ ለኢሳት የሰጠውን ሚስጢራዊ መረጃው የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ብቻ የሚያውቁት መሆኑን፣ ፕሮጀክቱ ከ1997 በሁዋላ በአገሪቱ ተፈጥሮ በነበረው ችግር ምክንያት የአገሪቱን ሰላም ለማስጠበቅ የተሰራ ሆኖ በሚስጢር መያዝ ያለበት መሆኑን ፣ ሚስጢር የሚሆነው የጃሚንግ ሳይንሱ ሳይሆን ተቋሙ በጃሚንግ ቴክኖሎጂ አማካኝነት እየሰራ ስለነበረው ስራ መግልጽ መሆኑን ኢንሳ ዘርዝሮ አቅርቧል።
ኢንሳ በተለይ “ ብዙ ትራንስሚተር ስላለ 24 ሰአት ጃሚንግ የማድረግ አቅም ያለ ስለመሆኑ፣ የጃሚንግ መሳሪያው አድቫንስድ ሆኖ ስፖትታይፕ እና ስዊጂንግ ቴክኖሎጂ የሚባሉ ያሉ መሆኑን ፣ ስፖትታይፕ ቴክኖሎጂው አንድ ፍሪኩዊንሲ ብቻ ላለው እንዲሁም ስዊጂንግ ቴክኖሎጂው የተለያዩ ፍርኩዌንሲዎች ላላቸው ማሰራጫዎች ስርጭቱን ለማጥፋት እንደሚጠቀሙ፣ የጃሚንግ ኦፐሬሽንን ለ3 ሰአት ብቻ የምትሰራው አንዷ መሳሪያ 2.4 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላት መሆኑን፣ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተተከሉ እያንዳንዳቸው ከ100 እስከ 150 ዋት የሚሸከሙ ከ4 የተለያዩ ስቴሺኖች የሚመጡ ሲግናሎችን መሸፈን የሚችሉ ከ12 በላይ ተቀናጅተው የሚሰሩ ትራንስሚተሮች ያሉ መሆኑን ፣ ጃሚንጉን የሚሰራው ክፍል የኢንፊርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ መሆኑን ፣ የሳተላይት ቴሊቪዥን ካውንተር ጃሚንግ ትራንስሚተሮች ያላቸው መሆኑን” እና ስራውን ለመስራት በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየፈሰሰ መሆኑን በመናገር የአገሪቱን ሚስጢር አሳልፎ መስጠቱም ተመልክቷል።
ኢንሳ ተላልፈው የተሰጡት መረጃዎች የአገሪቱን መንግስት ጥቅም የሚጎዱ፣ ጠላት በማንኛውም ጊዜ ሊጠቀምባቸው እንደሚችሉ በመግለጽ በዝርዝር ቢያቀርብም፣ ጸጋዬ ግን ሚስጢር ለኢሳት አሳልፎ አለመስጠቱን ገልጿል። በጸጋዬ ላይ የቀረበው የድምጽ ማስረጃ የአገሪቱን ሚስጢር ለመጠበቅ ሲባል በዝግጅ ችሎት ይሰማልኝ ባለው መሰረት ፣ ዳኞቹ በዝግ ችሎት እንዲሰሙት ተደርጓል። በድምጽ ላይ የሚናገረው ሰው ዳንኤል ንጉሴ የሚባል ሲሆን፣ ኢንሳ ስሙ ሆን ተብሎ የተቀየረ እንጅ ድምጹ የጸጋዬ ነው የሚል መከራከሪያ አቅርቧል።
ጸጋዬ “ የአፍ መፍቻ ቋንቋዬ ትግርኛ ሲሆን ፣ እኔ የምናገረው የአማርኛ ቋንቋ የትግርኛ የአነጋገር ዘይቤ ተጽኖ ያለበት ነው። በቀረበው የድምጽ ማስረጃ ላይ ግን የሌላ ቋንቋ ተጽእኖ የሌለበት መሆኑን ፣ መረጃውን አሳልፎ የሰጠው ሰው የእኔ አይነት የትግርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋው እንደሌለው የሚያሳይ ነው” ሲል ተቃውሞውን ገልጿል።
ጸጋዬ በድምጹ ላይ የሚናገረው ግለሰብ “ ያቀረበው የቴክኖሊጂ ይዘት ሰፊና የተለያዩ የደህንነት የሙያ ዘርፎች የሚዳስስ ነው። ይህ ደግሞ አንድ ግለሰብ እንደዚህ አይነቱ ጥልቀት ባለው መንገድ ዝርዝር መግለጫ መስጠት የሚችለው የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የመራና የተገበረ እንዲሁም በእነዚህ የተለያዩ የሙያ ዘርፎች የአጫጭር ይሁን የረጅም ጊዜ ስልጠናና ጥናት ያካሄደ ሞያተኛ መሆኑን ለመገመት አይከብድም። በአንጻሩ ደግሞ እኔ በጃሚንግ ዲፓርትመንት ከሶስት ወር የማይበልጥ ጊዜ የቆየሁ መሆኔን እንዲሁም በኤሌክትሮኒክስ ሴኩሪቲ ዲፓርትምንት ደግሞ ከስድስት ወር በማይበልጥ ጊዜ ተመድቤ የቆየሁ በመሆኔ ፣ በተጨማሪም የጃሚንግ እቃው ሲተከል ፣ ሲገዛ ወይም ለግዢ የሚያስፈልገው መስፈርት ያላዘጋጀሁ መሆኔን እና በዛን ጊዜ በነበረኝ የሙያ ክህሎት እነዚህን ጥልቅ የሙያ ዶክመንቶች ለማዘጋጀት የሚያስችል በቂ እውቀት የነበረኝ ግለሰብ ባለመሆኔ” ሚስጢር አሳልፎ ሰጥቷል በሚል መከሰሴ ትክክል አይደለም ብሎአል።
ጻጋዬ አክሎም “ በመረጃ ደህንነት ህግ አንድ ግለሰብ ወይም የአንድ ዲፓርትመንት ሰራተኛ የሌላውን ክፍል ስራ አግባብ ባልሆነ መንገድ ለማወቅ ከሞከረ ወይም ከሰጠ ሰጪውም ተቀባዩም በህግ የመጠየቅ ግዴታ አለባቸው ። ይሁንና የመረጃ ሰጪው በሌለበት ሁኔታ ተቀባይ ሊኖር አይችልምና ለእኔ መረጃውን የሰጠኝ የሌላው ዲፓርትመንት ሰራተኛ ስም ያልተገለጸ በመሆኑ በእኔ ላይ የቀረበው ክስ ትክክል አይደለም ብሎአል።
ጸጋዬ ኢንሳ መረጃውን አሳልፎ የሰጠውን ሰው ማግኘት አለመቻሉንና እርሱን ለምን ተጠያቂ እንዳደረገው እንዲህ ሲል ይገልጻል “ እኔ ከአሜሪካ ሃገር ወደ ኢትዮጵያ ስመለስ በኢትዮጵያ ኤርፖርት ድርጅት የፍተሻ በር በቀጥታ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የቀረበልኝ ጥያቄ ይሁን የተደረገልኝ ፍተሻ የለም። በተጨማሪም የመከላከያ የከፍተኛ ቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪ አመራሮች በግል ለቴክኖሊጂ ስራ እገዛና ድጋፍ እንዲሁም በአካል ተገኝቼ ለከፍተኛ ኢንጂነሮች ስልጠና እንድሰጥና ለወደፊቱ ደግሞ በኮንትራት ስራዎችን እንድወስድ ጥሪ ቀርቦልኝ ወደ ኢትዮጵያ ስመጣ ምንም አይነት ክትትልና የማጣራት ስራ አልተሰራም። ይህ ሁኔታ የሚያመለክተው ደግሞ ክሱ የተቀነባበረው እኔ ወደ ኢትዮጵያ መጥቼ ለሁለት ወር ያክል ወደ 10 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ለኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ኢንጂነሮች የሰራሁት ስራ በታወቀ ማግስት ነው። ክሱ በእኔ ላይ እንዲመሰረት የተደረገው የቢዝነስ ክፍተቱን በመሙላቴ እንደሆነ በግልጽ ያሳያል”
የፌደራሉ አራተኛ ወንጀል ችሎት ፣ ኢንሳ ያቀረበው ማስረጃ ሚስጢሩን ጸጋዬ አሳልፎ ሰጥቷል ብሎ ለመናገር በቂ አለመሆኑን በመግለጽ ጸጋዬ ከአንድ አመት እስር በሁዋላ ግንቦት3 ቀን 2009 ዓም በነጻ እንዲሰናበት ፈርዶለታል።
ሚያዚያ 10 ቀን 2009 ዓም ባቀረበው ዘገባ ጸጋዬ ለኢሳት አገራዊ ሚስጢር አሳልፎ ሰጥቷል በሚል መከሰሱን ፣ በእርሱ ላይ የቀረበው ክስ ከሌሎች ተከሳሾች ተነጥሎ በዝግ ችሎት እንዲታይ መደረጉን ዘግቦ ነበር።
ለኢሳት የደረሰው ማስረጃ እንደሚያሳየው የህወሃት ኢህአዴግ አገዛዝ ኢሳትን ጨምሮ ሌሎችን ከውጭ የሚተላለፉ ስርጭቶችን ለማፈን በየጊዜው በሚሊዮኖች ዶላር በማውጣት የአገሪቱን ሃብት እያባከነ ነው። ከነጋዴዎችና ከአርሶአደሮች በግብር ስም የሚሰበሰበው የደሃው ገንዘብ ለአፈና ስራ መዋሉ እንደሚያንገበግባቸው መረጃውን የላኩልን የደህንነት ሰራተኞች ይገልጻሉ። ኢንሳ ሰራተኞችን ከጊዜ ወደ ጊዜ በጥርጣሬ እንደሚያያቸው ፣ ድርጅቱን የሚለቁ ሰራተኞች ከአገር ካልወጡ በስተቀር ክትትል እንደማይለያቸው ሰራተኞች ይገልጻሉ። ኢሳትን ለማፈን የሚወጣው ገንዘብ ከፍተኛነት ብቻ ሳይሆን መረጃው በተለያዩ መንገዶች ለህብረተሰቡ መድረሱ አመራሮችን በእጅጉ የሚያበሳጭ ጉዳይ መሆኑን እንዲሁም የጃሚንግ ቴክኖሎጂን ለመግዛት በሚል የኢንሳ አመራሮች ከፍተኛ ገንዘብ እየዘረፉ መሆኑን የድርጅቱ ሰራተኞች ይገልጻ


No comments:

Post a Comment