Wednesday, May 10, 2017

በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኛ ኤልያስ እና ፖለቲከኛ ዳንኤል የጤና እክል እንደገጠማቸው ተገለጸ

የቀድሞ አንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የነበረው ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ የጤና ችግር እንደገጠማቸው ተገለጸ፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሳችኋል ተብለው ለእስር ከተዳረጉ አምስተኛ ወራቸውን የደፈኑት ሁለቱ ወጣቶች፣ ሆኖም እከሁን ድረስ የእነሱን ጉዳይ በኃላፊነት ሊወስድ የቻለ አካል አለመገኘቱ በተደጋጋሚ ሰገለጽ ቆይቷል፡፡ አሁን ደግሞ ታስረው በሚገኙበት እስር ቤት የጤና ችግር እንዳጋጠማቸው የቅርብ ሰዎቻቸው ተናግረዋል፡፡


ጋዜጠኛው ኤልያስ እና ፖለቲከኛው ዳንኤል የአስር ጊዜያቸውን እና አሁን ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ደብዳቤ መጻፋቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በደብዳቤው ላይም የእነሱን ጉዳይ ኃላፊነት ወስዶ እየተከታተለ ያለ አካል ባለመኖሩ፣ ያለ አንዳች ምክንያትም ሆነ ክስ በእስር እየማቀቁ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል፡፡ ‹‹ወይ ከሳሽ አግኝንተን አልተከሰስን ወይም አልተፈታን፡፡›› ሲሉም በደብዳቤያቸው ላይ ገልጸዋል፡፡

እነ ኤልያስ ገብሩ በታሰሩበት ወቅት አብሮ ታስሮ የነበረው ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ፣ ከአራት ወራት በኋላ ከእስር መለቀቁ አይዘነጋም፡፡ አናንያ ታስሮ የነበረው እንደነ ኤልያስ ሁሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣስ ሲሆን፣ ታስሮ የነበረውም ከእነ ኤልያስ ገብሩ ጋር እነደነበር ይታወቃል፡፡ ጋዜጠኛውን እና ፖለቲከኛውን አስሯቸው የሚገኘው የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ፣ እነሱን የመክሰስ ሰልጣን እንደሌለው በመግለጽ ወደ ማዕከላዊ ወስዷቸው የነበረ ቢሆንም፣ ማዕከላዊም እነሱን ለመቀበል ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡

© BBN ቢቢኤን

No comments:

Post a Comment