Monday, October 10, 2016

ዢው ፓርቲ ከወጣቶች ጋር እርቅ ለመፍጠር ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

መስከረም ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ አንዳሳ በሚባለው አካባቢ ከጎበዝ አለቆች ጋር እርቅ መፍጠር እንፈልጋለን በሚል ገዢው ፓርቲ ያቀረበውን ጥያቄ ወጣቶች ውድቅ አደረጉት። ወጣቶቹ፣ ማንኛውም ሰው፣ ፖሊስም ሆነ ወታደር ረብሻ ቢፈጥር እርምጃ እንወስዳለን በማለት የተማማሉ ሲሆን፣ አካባቢያችንን ከእንግዲህ እኛ የመረጥናቸው እንጅ እናንተ የምትመርጡት አያስተዳድረውም በማለት በፖሊሶች እና በአመራሮች ላይ ድንጋይ በትኖ አባሯቸዋል።
ሰባት አሚት በሚባለው አካባቢ ደግሞ የቀበሌ አመራሮችን ለመምረጥ የተደረገው ሙከራ ከሽፏል። የአካባቢ ካድሬዎች ምርጫ እናስደርጋለን ብለው ቢሄዱም ህዝቡ ፈቃደኛ ሳይሆን የቀረ ሲሆን፣ የቀበሌውን ቁልፍ በመቀየር ቀበሌውን በእጁ አስገብቷል።

No comments:

Post a Comment