Tuesday, January 17, 2017

የኢሳት የሰሜን ጎንደር ወኪል እንደዘገበው፣ ከዚህ በፊት የጥምቀትን በአል ለማክበር ይደረጉ የነበሩ ዝግጅቶች በዚህ አመት አልተደረጉም

ጥር ፱ ( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት የሰሜን ጎንደር ወኪል እንደዘገበው፣ ከዚህ በፊት የጥምቀትን በአል ለማክበር ይደረጉ የነበሩ ዝግጅቶች በዚህ አመት አልተደረጉም። የሃይማኖት አባቶች የሆኑት የአቡነ አብርሃ እና አባ ቀለመወርቅ መታሰር እንዲሁም በዞኑ የሚፈጸመው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ የሃይማኖት አባቶች በአሉን በተቀዛቀዘ ስሜት ለማክበር እንዲወስኑ አድርጓቸዋል። የወረዳው ከንቲባና ሌሎች ባለስልጣናት ህዝቡ ቢያምንበትም ባያምንበትም በአሉ እንዲከበር የሚል ትእዝዛ ለሃይማኖት አባቶች ሰጥተዋል። በወገራ ወረዳ አምባጊዮርጊስ ከተማ ደግሞ ታቦቱ ቤ/ክርስቲያኑን ዞሮ እንዲገባ እንጂ በፊት የሚደረገው ስነስርዓት እንዳይከናወን ወስነዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአገረ ስብከቱ ሃላፊ አቡነ ኤልሳዕ በአቡነ ቀለምወርቅ እና በበአሉ አከባበር ዙሪያ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ለማግኘት ቢፈልጉም፣ ሳይሳካላቸው ቀርቷል።

No comments:

Post a Comment