Tuesday, January 3, 2017

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ዛሬም ግጭት እንደነበር ተገለጸ

አሊ አመር በሚባለው አካባቢ በተፈጸመ ጥቃት በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት መገደላቸውን የቤንሻንጉል ነጻነት ንቅናቄ መሪ አቶ አብዱል አላዲህ ገልጸዋል።
የደረሰውን ጉዳት ተከትሎ ወደ አካባቢው በብዛት የተጓዙት ወታደሮች በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጥቃት መፈጸማቸውን እንዲሁም በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን ሃላፊው ገልጸዋል።
በገዢው ፓርቲ ወታደሮች እና በእነሱ ታጋዮች መካከል የሚደረገው ውጊያ ለሳምንታት መቆዩቱን የሚናገሩት መሪው ፣ በርካታ የገዢው ፓርቲ ወታደሮች መገደላቸውንም ይገልጻሉ።

ከተለያዩ የኢትዮጵያ ሃይሎች ጋር በመተባበር አገሪቱን ከህወሃት አገዛዝ ለማላቀቅ እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውንም የድርጅቱ መሪ ተናግረዋል
ድርጅቱ አደረስኩ ስላለው ጉዳት በገዢው ፓርቲ በኩል የተሰጠ መግለጫ የለም።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልሉ የተለያዩ የነጻነት ሃይሎች እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment