Wednesday, April 29, 2015

በባሌ ጎባ ሰማያዊን ለማውገዝ የተጠራው ሰልፍ ተበተነ

በባሌ ጎባ አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በሚል ሰማያዊን ለማውገዝ የተጠራ ሰልፍ ህዝቡ ፈቃደኛ ባለመሆኑ መበተኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ሚያዝያ 20/2007 ዓ.ም በባሌ ጎባ በተጠራው ሰልፍ የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ደም ከማፋሰስ ተግባሩ ይቆጠብ›› የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን ይዘው እንዲወጡ ከማድረግ ባሻገር ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ አሸባሪ ነው›› በሚል ህዝቡን ቀስቅሰው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
ሆኖም ሰልፉ በሚደረግበት ጎባ ከተማ በተመሳሳይ ሰዓት ሰማያዊ ፓርቲ በመኪና ቅስቀሳ እያደረገ ስለነበር ሰልፉ ላይ ሰማያዊን እንዲያወግዝ ተጠርቶ የነበረው ህዝብ ‹‹አሸባሪ የምትሏቸው ሰዎች ሰላማዊ ቅስቀሳ እያደረጉ ነው፡፡ አሸባሪ ከሆኑ ለምን የምርጫ ቅስቀሳ ያደርጋሉ? አሸባሪ ያልሆኑትን ሰዎች ለምን አሸባሪዎች ናቸው ትሉናላችሁ?›› በሚል ሰልፉን ጥለው በመሄዳቸው ሰልፉ እንደተበተ ተሰምቷል፡፡ ህዝቡ ሰልፉን ጥሎ በመሄዱ የቀሩት ካድሬዎችም ወደ ቀበሌ የስብሰባ አዳራሽ በመሄዳቸው ሰልፉ ወደ ስብሰባ ተቀይሯል ተብሏል፡፡


No comments:

Post a Comment