Saturday, April 18, 2015

የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶርክተር ብርሃኑ ነጋ ዌንዲ ሼርማን ስለተናገረችው መልስ ሰጡ

የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶርክተር ብርሃኑ ነጋ ከጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ጋር ዌንዲ ስለተናገረችው የሰጡት አጭር ቆይታ ከዚ ቀደም ዌንዲ ሼርማን ኢራንን በተመለከተ ተናግራ የሆነ ነገር ይቅርታ እንድታደርግ ተደርጋለች። እኔ እንደሚመስለኝ ምን ያህል ጭንቀት ውስጥ ወያኔዎች እንደገቡ እንዳለ ነው የሚያመላክተኝ እንደው ይሄን ነገር ተናገሪልን ብለው ለምነው ያናገሯት ነው የሚመስለው ምክንያቱም እንደሚታወቀው በሁሉም አቅጣጫ ይሄ ስርዓት ሊቆጣጠረው የማይችለው የህዝብ አመፅ እና ግፊት ውስጥ እየገባ ነው ያለው ይሄንን በህዝብ የሚመጣ ግፊት እንደው ትንሽ አሜሪካ የሆነ ነገር ከተናገረች ሰዎ መለስ ይልልኛል ከሚል ቅዥት የተነሳ አንድ ነገር ብትልልኝ ብለው ነው የሚመስለኝ። ለኔ በጣም እታየኝ ያለው ሁኔታ በቀላሉ ከቁጥጥር ውጭ ሊወጣ እንደሆነ ህብረተሰቡ በፍጹም እያመፀ እንደሆነ በደንብ የተረዱት ይመስለኛል። እና እቺ የመጨረሻ ለማረጋጋት ይቻል እንደሆነ ለመሞከር የተደረገ ነው የሚመስለው በአሜሪካኖች በኩል ይሄ ግን የሚገርመው ነገር ለዴሞክራሲ እና ለነፃነት ለእኩልነት የሚደረግን ትግል አሜሪካ አንድ ነገር ተናገረች፣ እራሺያ አንድ ነገር ተናገረች፣ ቻይና አንድ ነገር ተናገረች የሚቆም ነገር አይደለም ህብረተሰቡ ነው ኑሮውን የሚያውቀው ያ ህብረተሰብ ያለበትን ኑሮ አይቶ በቃኝ ብሎ ከተነሳ ማንም የሚያቆመው ሀይል የለም። ሙሉውን ቃለ መጠየቅ ታች ያለውን የኢሳት ሬዲዮ ተጭነው ያድምጡ http://ethsat.com/esat-radio-17-april-2015/


No comments:

Post a Comment