Thursday, April 2, 2015

ሕወሓት የብአዴን እና ኦሕዴድ ሰዎችን በልማት እንቅፋትነት ሰበብ ሊያሰናበት መሆኑ ታውቋል

የብአዴን አባላት አሁንም ፈዘው የሕወሓት የበላይነት እንዲያበቃ ራሳቸውን እና ሕሊናቸውን ለመጠየቅ ያልቻሉበት ደረጃ ላይ ናቸው:የመሻሻል ምልክቶች ቢታዩም መልሰው ይከስማሉ ያሉት የዚህ መረጃ አድራሾች ብኣዴንን አዳክሞ በአማርኛ ተናጋሪ ሌሎች ብሄሮች በተሻሻለ መልኩ ለመተካት በሕወሓት በኩል እየተሸረበ ያለው ሴራ በውስጡ ሰርገው በመግባት ድርጅቱ እንዲነቅዝ አድርገዋል ያላቸውን አባላቱን ሁሉ ነቅሰው በማውጣት በብልሃት መዋጥ የሚሉ ስልቶች በብአዴን ካድሬዎች ዘንድ ጥያቄዎችን አጭሯል::ሕወሓት ኢሕኣዴግ ላይ እንከን ይፈጥሩ ይሆናል ለማሸነፍም ይሁን ለማጭበርበር እንቅፋት ይሆናሉ ያላቸውን የብኣዴን በማግለል የጀመረውን ጉዞ መቀጠሉ ሲታወቅ ኦሕዴድ በበኩሉ ከተለያዩ ጸረ ልማት የፖለቲካ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ጋር ግንኙነት አላቸው የበላይ የወረደ ትእዛዝ ሊፈጽሙ አልቻሉም ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ሰንሰለት ሰርተዋል የተባሉትን አባላቱን በልማት እንቅፋትነት ሰበብ ሊያሰናበት መሆኑ ታውቋል::

የአገዛዝ እድሜውን ለማስረዘም የማይቧጥጠው ነገር ያሌለው ሕወሓት በኢሕኣዴግ ድርጅቶች መካከል የተስፋፋው የውስጥ ሰላም ማጣት እና አለመተማመን ስላሰጋው በመጀመሪያ በብኣዴን ውስጥ ያሉትን እና ያሰጋሉ የተባሉ ባለልጣናትን እና ካድሬዎች ማስወገድ ስለሆነ ይህንኑ ስራውን በወያኔ ሚዲያ ላይ ባሰማራቸው ሰዎች ላይ እንደሚጀምር ታውቋል::በተለያየ የስልጣን እርከን ላይ የነበሩ የብኣዴን ሰዎች በእረፍት ስም እቤታቸው እንዲቆዩ የተደረጉ ሲሆን ካድሬዎችም እንዲሁ እረፍት እንዲወስዱ ፎርም እንዲሞሉ ሊደረግ መሆኑ ታውቋል::ከእረፍት ከመመለሳቸው በፊት ለእያንዳንዱ በግል አርፎ እንዲቀመጥ ማስጠንቀቂያ የሚሰጥ የደህነንት አካል መዘጋጀቱን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል::


No comments:

Post a Comment