Saturday, April 11, 2015

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ በሚገኙት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ ወክባ እየተፈጸመ ነው ተባለ።

ሚያዝያ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድምጻችን ይሰማ እንደገለጸው፤ቀደም ካለ ጊዜ አንስቶ በሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እስረኞች ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ በደል ሲፈጽም የቆየው የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ሰሞኑን ደግሞ በከሰዓቱ
የእስረኞች መጠየቂያ ክፍለ ጊዜ ጠያቂ እንዳይገባላቸው እገዳ ጥሏል።
የማረሚያ ቤቱ አ
ስተዳደር ይህን እገዳ የጣለው ከኡስታዝ ያሲን ኑሩ ወላጅ እናት ማረፍ ጋር በተያያዘ በርካታ ህዝብ ሀዘኑን ለመግለጽና ለማፅናናት ወደ እስር ቤቱ በመሄዱ እንደሆነ ተገልጿል።
እስረኞች በጠያቂዎቻቸው የመጎብኘት ህገ መንግስታዊ መብት እስካላቸው ድረስ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር “ጠያቂ በዛ” በሚል ምክንያት እገዳ የመጣል አንዳችም ህጋዊ መብት እንደሌለው የጠቀሰው ድምጻችን ይሰማ፤ “ድርጊቱ ህግን የጣሰ ነው” ብሏል።
በተመሳሳይ ሁኔታ ከቀናቶች በፊት ከቂሊንጦ ወደ ቃሊቲ የተመለሰው ኡስታዝ አቡበከር አህመድ የእስረኛ አያያዝ መብትን በሚፃረር መልኩ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደሮች ከፍተኛ ጫና እየተደረገበት መሆኑም ትምልክቷል።
ሌሎች እስረኞች ለእርሱ እንክብካቤ በማድረጋቸው ምክንያት እየተበሳጩ ያሉት የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች ከእሱ ጋር የሚቀርቡ ሰዎችን ዞናቸውን ጭምር ከመቀየር ፣ከማዋከብና ከማስፈራራት አልፈው እርሱ የሚያድርበትን ክፍል መቀየራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
“ሊሳካላቸው ባይችልም የማረሚያ ቤቱ አስተዳደሮች ገና ከጅምሩ አንስቶ ይህን መሰል አሳፋሪ ምግባር ላይ የተሰማሩት ወኪሎቻችን ተስፋ እንዲቆርጡ እና ሞራላቸው እንዲነካ ለማድረግ ነው”ያለው ድምጻችን ይሰማ፤ “ውጤቱ ግን መንግስት ከፈለገው በተቃራኒ ራሱን
ለታላቅ ትዝብት ያጋለጠበት እና በሚፈጽማቸው አሳፋሪ ተግባራት ሽንፈቱን ራሱ ላይ እንዲመሰክር የተገደደበት አድርጎታል፡፡”ብሏል።
በተመሳሳይ ዜናም በማእከላዊ እስር ቤት ታስራ የምትገኘው ወጣት ፖለቲከኛ እየሩሳሌም ተስፋው ቤተሰቦቿ እንዳይጠይቋት መከልከሏን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
እየሩሳሌም ከብርሃኑ ተክለያሬድና ፍቅረማርያም አስማማው ጋር በሽብረተኝነት ወንጀል መከሰሷ ታውቋል። በደፋርነቷ የምትታወቀው በ20ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የምትገኘው እየሩሳሌም የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባል ነበረች።
ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ታስራ በዋስ ተለቃለች።
እየሩሳሌም ብርሃኑና ፍቅረማርያም ከሶስት ሳምንት በሁዋላ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።


No comments:

Post a Comment