Thursday, February 12, 2015

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሀት) ካድሬዎች ፣የደህንነት ሰዎች እና የመከላከያ አባላት፤አዲስአበባ የተለያዩ አካባቢዎች እየዞሩ፦‹‹ለህወሓት በዓል ማክበሪያ ገንዘብ አዋጡ›› በማለት እየቀሰቀሱ መሆናቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ።

የካቲት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህወሀት 40ኛ ዓመት የፊታችን የካቲት 11 የሚከበርሲሆን፤ ለበዓሉ ማክበሪያ በግዳጅና በጫና ከባለሀብቶች ብቻ 45 ሚሊዮን ብር እንደተገኘ መመዘገባችን ይታወሳል።
ህወሀት ከመንግስት ካዝና የሚጨምረውን ሳያካትት ለአንድ ጊዜ በዓል ማክበሪያ ብቻ ይህን ያህል ብር የሰበሰበ ቢሆንም፤ ከነዋሪዎች ተጨማሪ ገንዘብ ለማሰባሰብበ ካድሬዎች አማካይነት ቅስቀሳ መጀመሩን የአዲስአበባው ዘጋቢያችን ያጠናቀረው ሪፖርት ያመለክታል።
ከዚህ ባሻገር በአዲስአበባ፣ መቀሌ እና በየክልሎቹ የሚደረገው የበዓል ዝግጅት ላይ ካድሬዎች ደምቀው እንዲገኙ የልብስ መግዣ ገንዘብ እየተሰጣቸው እንደሆነ ተመልክቷል።
በዚህም መሰረት ለሴቶች የሀበሻ ቀሚስ መግዣ 4 ሺህ ብር ፣ ለወንዶች ደግሞ ለቁምጣና ለሌሎች ባህላዊ አልባሳት ተብሎ 2 ሺህ ብር እየተሰጠ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።


No comments:

Post a Comment