Thursday, December 8, 2016

ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የታሰሩት የደ/ር መረራ ጉዲናን መታሰር ተከትሎ የእሳቸው ደጋፊ ይሆናሉ የተባሉ ወጣቶች እየተለቀሙ በመያዝ ላይ ናቸው።

ኅዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የታሰሩት የደ/ር መረራ ጉዲናን መታሰር ተከትሎ የእሳቸው ደጋፊ ይሆናሉ የተባሉ ወጣቶች እየተለቀሙ በመያዝ ላይ ናቸው። እስሩ እርሳቸው በተያዙ ማግስት የጀመረ ሲሆን፣ እስከዛሬ ድረስ በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ የኦሮምያ ወረዳዎች እንዲሁም በአምቦና አጎራባች ቀበሌዎች በርካታ ሰዎች ተይዘው ታስረዋል። በተመሳሳይ ዜና በደቡብ ወሎ ሃይቅ ከተማ በርካታ ወጣቶች በአዲሱ ወታደራዊ እዝ አማካኝነት መሰታሰራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። እስካሁን በደረሰን መረጃ ከ50 ያላነሱ ወጣቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል። በሌላ በኩል በተለያዩ መስሪያ ቤቶች በዘበኝነት ተቀጥረው ስራ የሚሰሩ የቀድሞ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንደገና መታዋቂያ እንዲያወጡና እንዲመዘገቡ እየተደረገ ነው። ሰራተኞቹ ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት ጋር አዲስ ውል እንዲፈርሙ እየተደረገ ሲሆን፣ በተለይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚሰሩ ሰራተኞች የጦር መሳሪያ እንዳይዙ ፣ በስራ ወቅትም ወታደሮች ካልሆኑት ጋር ተመድበው እንዲሰሩ መመሪያ ተላልፏል።

No comments:

Post a Comment