Tuesday, March 21, 2017

ትግላችን ከሌሎች ብሄሮች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን ማዳን ነው ሲሉ የቤኒሻንጉል ህዝብ ንቅናቄ የፖለቲካ ሃላፊ ገለጹ

ኢሳት (መጋቢት 12: 2009)

የቤኒሻንጉል ህዝብ ንቅናቄ (ቤህኒን) የሚካሄደው የነጻነት ትግል ሃገራዊና ከሌሎች ብሄሮች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን የማዳን መሆኑን የድርጅቱ የፖለቲካ ሃላፊ ገለጹ።
የቤህኒን የፖለቲካ ሃላፊ አልሃጂ አፈንዲ ጠሓ በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት በህወሃት/ኢሀዴግ  የሚመራውን አገዛዝ ለማስወገድ የሚካሄደው የነጻነት ትግል ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ድርጁቱ በሃገር ውስጥ የሚካሄደው የትጥቅ ትግል በህወሃት/ኢህአዴግ ላይ ያነጣጠረ እንጂ በመሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት የማድረስ አላማ እንደሌለውም ገልጸዋል። በቅርቡ በህዳሴ ግድብ ላይ የተነጣጠረ ጥቃት ለማድረስ ተንቀሳቅሰዋል የተባለውንም ከቆምንለት አላማ ጋር የሚሄድ አይደለም ሲሉ አስተባብለዋል።

No comments:

Post a Comment