Friday, April 21, 2017

የአቅም ችግር ታይቶባቸዋል የተባሉ የብዓዴን እና የኦህዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ስልጠና ሊሰጣቸው ነው ተባለ


ኢሳት (ሚያዚያ 13 ፥ 2009)
በጥልቅ ተሃድሶው የአቅም ችግር ታይቶባቸው የተባሉ የብዓዴን እና የኦህዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ስልጠና ሊሰጣቸው መሆኑን ተነገረ።
የመጀመሪያው ዙር ስልጠና ከብዓዴን የድርጅቱ የጽህፈት ቤት ሃላፊና አማራውን በመዝለፍ የሚታወቁት አቶ አለምነህ መኮንን ተከተዋል። የመጀመሪያው ዙር ስልጠና በመጭው ሰኞ ይጀምራል።

በሁለተኛው ዙር ደግሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በአቅም ችግር ስልጠና ይወስዳሉ ተብሏል። በሁለተኘው ዙር ስልጠናም ከ45 ቀናት በኋላ እንደሚቀጥል ያገኘነው መረጃ የመለክታል። ከኦህእዴድም ስልጠና የሚወስዱት አቅም የሚያንሳቸው ባለስልጣናት ተለይተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦህዴድና  የብዓዴን የተወሰኑ ከፍተኛ ባለስልጣናት ካድሬዎች ጥቅል የተሃድሶ መስመራችን በሚል በአሜሪካ የተለያዩ ስቴቶች ከዳያስፖራው ጋር ለመወያየት ጉዞ ሊያደርጉ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
የባለስልጣናቱ የከፍተኛ ካድሬዎች የአሜሪካ ጉዞ ልማታዊ የሚባሉት ባለሃብቶች እና ከኢህአዴግ ጋር ቅርበት ያላቸው የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ያካተተ ነው ተብሏል።
በዚሁ መሰረት በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በነቀምት፣ በባህርዳርና በጎንደር ከተሞች ተሰሚነት አላቸው የሚባሉ ባለሃብቶች ለጉዞ መዘጋቸታቸውን ምንጮች ጨምረው ገልጸዋል። የጉዞው አላማ በውጭ አገር አገዛዙን የሚቃወሙ ዳያስፖራዎችን አመለካከት ለመቀየር የሰበ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

No comments:

Post a Comment