የካቲት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአርባ ምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አደራጅ የሆነው አቶ በፍቃዱ አበበ የ7 አመት እስር ቅጣት ተበየነበት፡፡
የካቲት 22/2008 ዓ.ም ከፍተኛው ፍ/ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት ቅጣቱን ያስተላለፈ አቶ በፍቃዱ ለግንቦት ሰባት ‹‹ሲያደራጅና ሲመለምል›› ነበር በሚል ነው።
አቶ በፍቃዱ ‹‹አሁንም ሆነ፣ ወደፊት አሸባሪ አይደለሁም፡፡ ግፍ ተፈጽሞብኛል›› ሲል ችሎት ፊት ተናግሯል፡፡ የዕለቱ ዳኛ በበኩላቸው ‹‹ግፍ እንደፈጸምህ የተረጋገጠብህ አንተ ነህ›› በማለት አቶ በፍቃዱን ተጨማሪ እንዳይናገር ማስጠንቀቃቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።
አቶ በፍቃዱ ‹‹አሁንም ሆነ፣ ወደፊት አሸባሪ አይደለሁም፡፡ ግፍ ተፈጽሞብኛል›› ሲል ችሎት ፊት ተናግሯል፡፡ የዕለቱ ዳኛ በበኩላቸው ‹‹ግፍ እንደፈጸምህ የተረጋገጠብህ አንተ ነህ›› በማለት አቶ በፍቃዱን ተጨማሪ እንዳይናገር ማስጠንቀቃቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።
No comments:
Post a Comment