የካቲት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ጸረ- ድራግ ኤጀንሲ ጀነራል ሴክሬታሪን ጠቅሶ ዘጋርዲያን እንደዘገበው ምርመራ እየተደረገባቸው ካሉት ዘጠኝ አትሌቶች መካከል አምስቱ ታዋቂና ስመ-ጥር አትሌቶች ናቸው።
ሴክሬታሪው አቶ ሰሎሞን መአዛ ለአሶሲየትድ ፕሬስ እንደተናገሩት ታዋቂዎቹ አምስት አትሌቶች አስደናቂ ድል አስመዝግበው መመለቸውን ተከትሎ አበረታች መድሀኒት ወስደዋል የሚል ቅድመ-ምርመራ ውጤት በመደረጉ ነው በኤጄንሲው ምርመራ እየተደረገባቸው ያለው።
ይሁንና ጀነራል ሴክሬታሪው የአትሌቶቹን ማንነት ከመግለጽ ተቆጥበዋል። በትውልድ-ኢትዮጵያዊ የሆነችውና ለስዊድን እየተወዳደረች ያለችው አትሌት አበባ አረጋዊ በተደረገባት ምርመራ ድራግ በደሟ ውስጥ በመገኘቱ ከአትሌቲክስ ውድድር የመታገዷ ዜና የተሰማው ከትናንት በስቲያ ነበር።
ቀሪዎቹን አራት አትሌቶችም በተመለከተ ዓለማቀፉ የአትሌቲክስ ማህበር ዝርዝር መረጃ እንዲቀርብለት መጠየቁን የጠቀሱት አቶ ሰሎሞን፤ ዓለማቀፉ የአትሌቲክስ አካል በነሱም ላይ ምርመራ እያደረገ እንደሆነ ተናግረዋል።
አቶ ሰሎሞን የአትሌቶቹን ስም ብቻ ሳይሆን ወስደውት ይሆናል ተብለው የተጠረጠሩበትን የድራግ ዓይነትም ከመናገር ተቆጥበዋል። ይሁንና የምርመራው ውጤት ሲገለጽ የሆነ ነገር ይገኝ ይሆንን የሚል ትክክለኛ ስጋት ማደሩን አልሸሸጉም።
የምርመራ ውጤቱ አትሌቶቹ እጽ መውሰዳቸውን ካመላከተ ከሩሲያና ከኬንያ አትሌቶች የድራግ ቅሌት ቀጥሎ የኢትዮጵያ ጉዳይ በመጪው ክረምት በሪዮ ዲጄኔሮ ለሚካሄደው ኦሎምፒክ እንደ ትልቅ ውድቀት ይሆናል።

No comments:
Post a Comment