Friday, March 11, 2016

እጅግ በርካታ የቆዳ ፋብሪካዎች የአካባቢ ጥናት ሳይደረግባቸው በመቋቋማቸው በህዝብ ጤና ላይ ችግር እየፈጠሩ ነው

መጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መረጃዎች እንዳመለከቱት በመላ አገሪቱ 90 በመቶ የሚሆኑ የቆዳ ፋብሪካዎች የአካባቢ ደህንነት ጥናት ሳይደረግባቸው የተቋቋሙ በመሆኑ፣ በህዝቡ ላይ ችግር እያስከተሉ ነው። በአማራ ፣ በደቡብና በኦሮምያ ክልሎች ችግሩ እየተባባሰ ሄዶ ለሰዎችና እንስሳት ሞት ምክንያት እየሆነ ነው።

በባህርዳር ከተማ የቆዳ ፋብሪካዎች በሚለቁት ኬሚካል የሚጠጡት ውሃ የተበከለባቸው ዜጎች በተደጋጋሚ አቤት ቢሉም የሚሰማቸው አላገኙም። በደቡብ ወሎ ዞን ሃይቅ ከተማ የሚገኘው የቆዳ ፋብሪካ በህዝብና በእንስሳት ላይ ጉዳት ማስከተል ከጀመረ ውሎ ያደረ ቢሆንም እርምጃ የሚወስድ አካል በመጥፋቱ ነዋሪዎች ለችግር ተዳርገዋል።
ተመሳሳይ አቤቱታዎች ለመንግስት በየጊዜው እየቀረበ ቢሆንም፣ በመንግስት በኩል ችግሩን ለመቅረፍ የሚወሰድ በቂ እርምጃ አለመኖሩን ነዋሪዎች በምሬት ይገልጻሉ።

No comments:

Post a Comment