Wednesday, March 30, 2016

ኣማራ ሲሞት ሌላ ኣማራ ሲፈራ ( ሄኖክ የሺጥላ )

እነዚህን ከስር የምትመለከቷቸውን ፎቶዎች ወዳጆቼ ከባህር ዳር ዛሬ ሌሊት ላኩልኝ።

ስለ ፎቶዎቹ ምንነት ባጭሩ ላስቀምጥ

ተደብዳቢው --   አማራ!
ደብዳቢው---  ወያኔ ትግሬ!
የድብደባው ምክንያት--- አማራ  መሆን!
ተጠያቂ ---የለም!!!
ይህንን ለማስቆም የሚቆም አማራ---  የለም!!!

ይህንን ኣይቶ ቁጭት ውስጥ ሊገባ የሚችል አማራ---  የለም!!!
ድብደባው ይቀጥላል ወይ?---- ኣዋ!







ይህንን ፎቶ ለብዙ ደቂቃ ተመለከትኩት ። ኣይኖቼ እንባ ተሞልተው ጥርሴን እያፋጨሁ ደግሜ ደጋግሜ ኣየሁት። ወዳጄ በውስጥ መስመር የፃፈልኝን ኣሳዛኝ ታሪክም ኣነበብኩ ። ማልቀስ ኣልችልም ፥ ኣሁንም ያለቀስኩ ኣይመስለኝም ፥ ግን ፊቴ ላይ እንባ የሚመስል ነገር እንደነበር ኣስታውሳለሁ ። መናደድም ኣልፈልግም ፥ ምክንያቱም ከመናደድ የሚመጣው ሽንፈት እንደሆነም ኣውቃለሁ ። ግን ማሰብ እፈልጋለሁ ፥ ድጋሚ ወደ ራሴ ተመልሼ እውነታውን በጥሞና ማየት እና መረዳት እፈልጋለሁ ።
 በቃላችን መሰረት የወዳጄን ምንነትም ሆነ ማንነት ለመናገር ኣሁን ጊዜው ኣይደለም ። ግን ይህ ድብደባ ምን ማለት እንደሆነ ላስረዳ።

ብዙ ለአማራ የሚጮህ ፥ እቆጫለሁ ባይ እኔ ባለሁበት ኣማሪካ ይኖራል ። እጅግ ብዙ  ነገር ማድረግ የሚችል ኣቅም ያለው አማራ  በየ ሃገሩ እንደሚኖር ኣውቃለሁ ። ትንታግ የሆኑ ፥ በሳል እና ብልህ አማሮች። ግን ደሞ ኣቅማቸውን የማያውቁ ፥ ከስብሰባ እና ጥናታዊ ፅሁፍ ከማቅረብ ውጪ  እኔ እስከማውቀው ድረስ ኣንድ  እርምጃ ወደፊት መራመድ ያልቻሉ መሆናቸውን ሳስብ ይገርመኛል። ነፃነት እና የኣማሪካ ህግ የተቀላቀለባቸው ተቆጪዎች በመሆናቸው ፥ ይቆጡና ግን መራመድ ይፈራሉ ፥ ይናደዱና ግን መተግበርን ይሰጋሉ ፥ ይበሳጩና ግን መሆንን ይሸሻሉ ። በመሆን እና ባለመሆን መሃከል የቆሙ ተቆርቋሪዎች ስለሆኑ ፥ ወገኖቻቸው ዛሬም ይደበደባሉ ፥ ይታሰራሉ ፥ ይታረዛሉ ፥ ይገደላሉ ። በመራመድ እና በመቆም መሃል ስላሉ ፥ ወገኖቻቸው እያለቁ ነው ። ይህም ፎቶ የነዚህ የኣማራ ልሂቃን ውሳኔ መዘግየት ውጤት ነው ። ሃያ ኣምስት ኣመት ለመራመድ የከበደን ፥ ሃያ ኣምስት ኣመት ቀና ለማለት የከበደን በውሳኔና በፈረንጅ ሃገር ህግ መሃል ስለቆምን ይመስለኛል ።

ኣማሪካንን ሳስብ የህግ ሃገር ነች ። የነፃነት ሃገር ነች ። የሰዎች መብት የሚከበርባት ሃገር ነች ። ይህ ሁሉ እውነት የሚሆነው ግን  በመጀመሪያ ከማንም በላይ ለኣማሪካኖች እና ኣማሪካ ውስጥ ለሚኖሩ ህዝቦች ነው ። ኣማሪካ ከኣማሪካ ውጭ ሁል ጊዜ ልክ ነች ብዬ የማስብ እብድ ግን ኣይደለሁም ። ለምሳሌ  ፕሬዝዳንት ኦባማ ኢትዮጵያ በሄደ ጊዜ የኢትዮጵያ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ ነበር ሲል  ተሰምቷል ። ምርጫው ፍትሃዊ ስለነበረ ነው ? ኣይደለም ! ኦባማ መረጃ ስለሌለው ነው ? ኣይደለም ! ዋነኛ ምክንያቱ  ለኣማሪካ ልክ የሚሆነው ኣባባል ምርጫው ፍትሃዊ ነው የሚለው ኣባባል ብቻ ስለነበረ ነው ። ኣማሪካ ውስጥ ስኖር የኣማሪካን ህግ ኣክብሬ መኖር እሻለሁ ማለት የኣማሪካ መሪ የኢትዮጵያዊያኖች ስቃይ ቸል ብሎ ሲያልፈው እቀበላለሁ ማለት ኣይደለም ። ኣማሪካን ሃገር መስረቅ ያሳስራል ። ኦባማን መተቸት ግን ኣያሳስርም ። ለነፃነት መታገል ግን ኣያሳስርም ። ቢያሳስርም ታግዬ እታሰራለሁ እንጂ ፈርቼ ዝም ኣልልም ። ከዚ በባሰ እና በተወሳሰበ ደረጃ ባንድ ጎን ለኣማሪካ ህግ ተገዥ ለመሆን ኣስበን ፥ በልላ ጎን ደሞ የህዝባችን ስቃይ ኣስቆጭቶን ፥ ፍርሃት እና ውሳኔ ተጋጭቶብን ስለመቆማችን መካዳችን ይመስለኛል ለውጥ እንዳናመጣ ያደረገን ። የኣማሪካ ህግ ንፁሃን ዜጎች ይገደሉ የሚል ኣይመስለኝም ፥ የሚል ከሆነ ግን ኣላከብረውም ፥ የኣማሪካ ህግ የኣማሪካ መንግስት የተሳሳተ መረጃ እንዲናገር ፍቃድ ኣይሰጠውም፥ የሚሰጠው ከሆነ ግን በእንደዚህ ኣይነቱ ህግ ኣልገዛም ፥ የኣማሪካ ህግ ሰዎች በዘራቸው ተቆጥረው እና ተጠርተው ሲገደሉ በማየታችንን ይህንን ለማስቆም ማንኛውም ኣይነት ትግል ውስጥ ብንገባ እና ጉዳዩን እንደ ኣንድ መንግስት ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ ገዳዮቹን እያወደሰ « ምንም የተፈጠረ ነገር የለም !» ቢለኝ ፥ ኣሁንም እንዲህ ኣይነቱን ህግ ኣላከብርም ። እኔ በግሌ  ህግ ከማይከበርበት ገነት ፥ በህግ የሚተዳደር ገሃነምን እመርጣለሁና።

ምን ለማለት ነው ፥ ኣማሮች የቱን ትመርጣላችሁ ? እንዲህ ብናደርግ ኣማሪካ እንዲህ ብታደርገንስ የሚለውን ፍርሃት ወይስ የማደርገው ነገር ህጋዊ ነው ፥ ለሰው ልጆች መብት የመቆም ትግል ነው ፥ የነፃነት ጥያቄ ነው በሚለው ላይ ኣምኖ ከፓናል ዲስኩር እና ከረባት ኣስተካክሎ ለማውራት ፥  ከመጨቃጨቅ እና ከመጠቋቆም   ይልቅ ህዝባችሁን  በቁርጠኝነት ከመከራ  ለመታደግ ትግል መታገል ? ህዝቡ ትግል ይፈልጋል ፥ ህዝቡ እናንተን ያያል ፥ የህዝቡ በትረ ሙሴ ለመሆን ግን ፥ በማንነት እና በፍርሃት መሃል ከመቆም ነፃ መውጣት ያስፈልጋል ።

የኣማራ ደም በከንቱ ፈሶ ኣይቀርም !

ፎቶዎቹ ትናንት ሌሊት  ከባህር ዳር ሆስፒታል የተገኙ ናቸው !

ሄኖክ የሺጥላ

No comments:

Post a Comment