Tuesday, May 31, 2016

በደቡብ አብዛኛው አርሶአደር የታጠቀው መሳሪያ ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ ሲሆን በአማራ ክልል የእዝ ቁጥጥሩ የጠበቀ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ


ግንቦት (ሃያ ሦስ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ወይም ሜቴክ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የጸጥታ ሃይሎችን ለመለየት እንዲያስችል በሚል በደቡብ እና በአማራ ክልሎች በ2006 ዓ.ም ያደረገው ጥናት ዝርዝር ለኢሳት የደረሰ ሲሆን ፣ ጥናቱ እንደሚያሳዬው በደቡብ ክልል አብዛኛው አርሶአደር የታጠቀው  ዘመናዊ መሳሪያ ክላሽ ሲሆን፣ ይህ የጦር መሳሪያ ከመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ውጭ ነው።

“የፖሊስና የሚሊሻ ሃይል ከታጠቅው በህብረተሰቡ የታጠቀው የተሻለ በመሆኑ በፀጥታ ሃይሎች ላይ አደጋ አየደረሰ መሆኑን” ሪፖርቱ አመልክቶ፣ ትጥቅ ለመመዝገብ ቢፈለግም፣ አብዛኛው ህዝብ የማስመዝገብ ፍላጎት እንደሌለው ይገልጻል።

በክልል  ፖሊስ እና የደቡብ ክልል ፈጥኖ ደራሽና ፀረ-ሽምቅ ሃይሎች እጅ  5117 መሳሪያ ሲኖር ፣ አጠቃላይ የጸጥታ ሃይሉ ብዛት ግን  11293 ነው። አብዛኛው የጸጥታ ሃይል  በቂ መሳርያ ስለሌለው ጥበቃውን የሚያካሂደው በዱላ መሆኑን ሪፖርቱ ያሳያል።
ወደ ክልሉ የሚገባው መሳሪያም ከደቡብ ሱዳንና ከኬንያ እንደሚመጣ ሪፖርቱ ይጠቁማል።

ህዝቡ “ለቀብራችን ደርሳችሁዋል” በማለት ለኢህአዴግ “ምስጋናውን” አቀረበ

ግንቦት (ሃያ ሦስ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 25ኛ አመቱን በማክበር ላይ ያለው ኢህአዴግ ፣ ህዝቡን ለማወያየት በባህርዳር በጠራው ስብሰባ ላይ አባሎቹ “ ኢህአዴግ ለቀብራችን ደርሰህልናልና እና እናመሰግንሃለን” ሲሉ ተሳልቀውበታል።
አንድ  አስተያየት ሰጪ “ይህ ህዝብ ያለቀና የሞተ ህዝብ ነው፤  አሁን ነው እንዴ የምትመጡት? ፣ ለህዝቡ ቀብር መጥታችሁዋል ጥሩ ነው ያሉ ሲሆን መንግስት በዲሞክራሲ ረገድ አገኘሁት በማለት ያቀረበውን የድል ዜና ውድቅ አድርገውታል። በየበረንዳው ወድቀው ያሉ፣ መጠጊያ የሌላቸው ከማህበራዊ ህይወትና ከኢኮኖሚ የተገለሉ አባላት አሉን ሲሉ አስተያየት ሰጪው በምሬት ተናግረዋል ።

ከአስር ዓመት በላይ የመስሪያ ቦታ ጠይቀው ምላሽ ያላገኙ ወጣቶች ቅሬታቸውን አቀረቡ፡፡

ግንቦት (ሃያ ሦስ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአስር ዓመት በፊት በህጋዊነት ተደራጅተው ሎጂ ( የመዝነኛ ቦታ)  በመገንባት በቱሪስቱ ዘርፍ ለመስራት ጠይቀው የተሰጣቸውን ቦታ ያለ አግባብ በባለሃብት ሲነጠቁ የከተማ አስተዳደሩ ምላሽ አለመስጠቱ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው የላሊበላ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ፡፡

የገዥው መንግስት አመራሮች አርባአራት ስራአጦችን በ 1996 ዓም.እንዲደራጁ ካደረገ በኋላ በ1997 ዓም.በተካሄደው ሃገራዊ ምርጫ “ተቃዋሚን ትደግፋላችሁ!” በማለት ለወጣቶች የተዘጋጀውን አራት ነጥብ ስምንት ሄክታር ቦታ ከአጎራባች ክልል ለመጣ ግለሰብ መስጠታቸውን ገልጸዋል፡፡
ቦታውን እንዲያገኝ የተመቻቸለት ባለሃብት ያለ ሊዝ በእርሻ መሬት ሂሳብ እንዲረከብ በማድረግ ለረዥም አመታት ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረጋቸውን የሚገልጹት ወጣቶች በቦታው ላይ በተዘጋጀው መዝናኛ ለሚያድሩ እንግዶች በቀን 99 ዶላር ቢያስከፍልም ምንም አይነት ደረሰኝ ቆርጦ የማያውቅ መሆኑን የአካባቢው ባለስልጣናት እያውቁ በዝምታ መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡

ወጣት አቤል በመከላከያ ሰራዊት አባላት ታፍኖ ከተወሰደ ከ4 አመታት በሁዋላ ያላበት አለመታወቁን ዘመዶቹ ተናገሩ

ግንቦት (ሃያ ሦስ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነዋሪነቱ በሃረር ከተማ ሸንኮር ሰፈር የሆነው ወጣት አቤል ሆሶ ሁቤር በመከላከያ ሰራዊት ከእስር ቤት ተወስዶ እስካሁን ድረስ የደረሰበት አልታወቀም።

ከአራት አመታት በፊት በታክሲ ሹፌርነትና በመካኒክነት ሙያ ይተዳደር የነበረው ከኢትዮጵያዊ እናትና ከኩባዊ አባት የተወለደው በቅጽል ስሙ አቤል ኩባ መሰናዶ በሚባለው በሸንኮር ወረዳ በሚገኘው የሰራዊቱ መኖሪያ ውስጥ ይኖር ከነበረ አንድ የመከላከያ ሰራዊት ጋር በመጋጨቱ ወታደሩን በጩቤ ወግቶ እንደ ገደለው ሆን ተብሎ በሀረር ከተማ እንዲወራ በማድረግ ከከተማ እንዲሰወር ተደርጓል።
አቤልን  ከመኖሪያ ቤቱ አግተው በወታደራዊ ካምፕ እስርቤት ውስጥ ከባድ ስቃይ ከፈጸሙበት በኋላ በሀረሪ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ የአስር ዓመት እስራት ተፈረደበት ነበር። ከሁለት ዓመታት እስር በኋላ ሞተ የተባለው ወታደር ሶማሊያ ውስጥ በሰላም አስከባሪነት መሄዱና እዛ መኖሩ በመረጋገጡ በነጻ ከእስር እንዲለቀቅ ተደርጓል።

መንግስት በአንድ ወር ውስጥ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና እንደሚያዘጋጅ አስታወቀ

ግንቦት (ሃያ ሦስ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዘንድሮው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና  አስቀድሞ መውጣቱን ተከትሎ የፈተናውን መሰረዝ በተምታታ መግለጫ ያወጀው መንግስት፣ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አፋጣኝ የሆነ ፈተና እንደሚሰጥ አስታውቋል። ፈተናው ከሰኔ 27-30 እንደሚሰጥ የተገለጸ ቢሆንም፣ ሰኔ 28 ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የኢድ አል ፈጥር በአልን የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ በተማሪዎች ላይ የሚያመጣው ተጽእኖ ቀላል አይሆንም በማለት ኢትዮጵያውያን ተቃውሞአቸውን እያሰሙ ነው።

The fight with TPLF is in the heartland, not along the border, Prof. Berhanu Nega

ESAT News 
Chairman of the Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracy, Prof. Berhanu Nega reiterated that armed operations by his Movement is not along the border with Eritrea as the regime in Addis Ababa would like the people to believe, but is inside the heartland as has been seen in the recent fight with regime forces in Arbaminch, south Ethiopia.

Monday, May 30, 2016

ጠላቶቻችን ወደ ውስጥ ሰርገው በመግባት ሊያዳክሙንና ሊያሽመደምዱን እየሞከሩ ነው ሲል ኢህአዴግ አስታወቀ

ግንቦት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 25ኛውን የግንቦት20 በአል በማክበር ላይ የሚገኘው ኢህአዴግ ለውይይት ባዘጋጀው ሰነዱ ላይ ግንባሩ ከፍተኛ አደጋ ውስጥ መውደቁን አትቷል። ባለፉት 25 አመታት ከፍተኛ ድል በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መስኮች የተመዘገበ ቢሆንም፣ እነዚህን ድሎች የሚቀለብሱ እንዲሁም የአገሪቱን ህልውና አደጋ ውስጥ የሚጥሉ አዝማሚያዎች እየታዩ ነው ብሎአል።

የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና መውጣቱን ተከትሎ ፈተናው መሰረዙን መንግስት አስታወቀ

ግንቦት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ ሊካሄድ የነበረው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና መውጣቱን ተከትሎ መንግስት ፈተናውን ለመሰረዝ የተገደደ ሲሆን፣ በተማሪዎች በኩል የተለያዩ አስተያየቶች እየተስተናገዱ ነው። በወላይታ ሶዶ ፈተናው መሰረዙን የሰሙ ተማሪዎች ተቃውሞ አድርገው የነበረ ቢሆንም፣ የፌደራል ፖሊሶች በትነዋቸዋል። ከተለያዩ የገጠር ከተማዎች የመጡ ተማሪዎች፣ ከእንግዲህ ወዲያ ወደ ቤተሰቦቻችን የምንሄድበትም ሆነ ከተማ የምንቆይበት ገንዘብ ስለሌለን መንግስት አንድ ይበለን ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል።

Saturday, May 28, 2016

“በአንድ ስርዓት ሥር ይህን ያህል ጊዜ መቆየት እጅግ ያንገበግባል”

ወይንሸት ሞላ የ25 ዓመት ወጣት ስትሆን፤ በኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ ዘመን ተወልዳ አድጋለች፡፡ በሌላ አነጋገር ወይንሸት አንዳንዶቹ ‘The EPRDF Generation’ የሚሉት ትውልድ አባል ነች፡፡ ወይንሸት ብቻ ሳትሆን ስልሳ አምስት በመቶው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ወዲህ የተወለደ ሲሆን፤ ይሄም ከአገሪቱ አጠቃላይ ሕዝብ ሁለት ሦስተኛውን ይሸፍናል፡፡ ወይንሸት በዚህ ዕድሜዋ በሥልጣን ላይ ያለውን ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግን በዜጎች ላይ ግፍ ሲፈጽም አይቼ ዝም ብዮ አልቀመጥም በማለት የፖለቲካ ትግሉን ተቀላቅላ ለዛም ብዙ ዋጋ እንደከፈለች/እየከፈለች እንዳለች በመግለጽ “‹ዴሞክራሲ በዚህ አምባገነን ስርዓት ሰፍኖ፣ አገሬ እንደ አገር ሉዓላዊነቷ ተከብሮ፣ ሕዝቧ የተሻለ ኑሮ ካላቸው አገሮች ተርታ ተመድባ አያለሁ› የሚል ተስፋ የለኝም” ትላለች፡፡ እነሆ አንብቧት፡፡

የህወሃት ድል 25ኛው ዓመት ሲከበር

ህወሃት ለንግሥና የበቃበትን 25ኛ ዓመት ለማክበር ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ መድቦ ከገጠር ቀበሌ እስከ አገሪቱ ዋና ከተማ ነዋሪ የሆነውን ህዝብ በየሥርቻው ባዘጋጀው የፈንጠዝያ ድንኳን እንዲሰባሰቡለትና በዓሉን እንዲያደምቁለት በተለያዩ መንገዶች ሲያስገድድ ሰንብቶአል። "የግንቦት 20 ድል ባስገኘልን ዕድል ተጠቅመን ለዚህ ወይም ለዚያ ስኬት በቃን" የሚሉ ጥቂቶችን በቴለቪዥንና በሬዲዮ ከማቅረብ አልፎም ለቱባ ቱባ ባለሥልጣናቱና በግል ጥቅም ተጠልፈው በዙሪያው ለተሠለፉ ወፋፍራም ሎሌዎቹ ያሠራውን የኢህአደግ ባንዲራ አልብሶ በትላልቅ አዳራሾች በማጨቅ የ25ቱን አመት ገድል እየሰበከ ጣራው እስኪሰነጠቅ ሲያስጨበጭባቸውም ከርሞአል።

Friday, May 27, 2016

“ህዝቡ ከኢህአዴግ መሪዎች ይልቅ በውጭ ለሚገኙ የፖለቲካ መሪዎች እውቅና እየሰጠ ነው” ሲል የደህንነት መስሪያ ቤቱ አስታወቀ

ግንቦት ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ 25ኛ አመት በአሉን እያከበረ በሚገኝበት ወቅት እያደረገ ባለው ግምገማ የደህንነት መስሪያ ቤቱ ለስርአቱ አደጋ ሊፈጥሩ ይችላሉ ያላቸውን ጉዳዮች ለውይይት ከማቅረብ ባሻገር ፣ ህዝቡ በአገር ውስጥ ላሉ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከሚሰጠው እውቅና ይልቅ በውጭ አገር ለሚገኙ የተቃዋሚ መሪዎች እየሰጠ በመምጣቱ የስደት መሪዎችን እስከመሾም ተደርሷል ብሎአል ።

የደህንነት እና መረጃ ክፍል ባቀረበው ጥቅል ግምገማ የኤርትራ መንግስት የሚካሄደውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ስልክ ጠልፎ በማዳመጥ በኩል ውጤታማ ስራ መሰራቱን ገልጿል። “ይሁን እንጅ” ይላል ሪፖርቱ “በሰሜን ጎንደር እና በሱዳን ድንበሮች አካባቢ ብዙ ስራዎችን ለመስራት ቢታቀድም ብቃት ያለው ስራተኛ ባለመገኘቱ የታቀደውን ያህል ስራ መስራት ሳይቻል ቀርቷል፡፡”

ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያስገኛል ተብሎ የታቀደው የቆዳ እና ሌጦ ኢንዱስትሪ ውጤታማ አልሆነም

ግንቦት ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አምና ኢትዮጵያ ወደ ውጭ አገር እቃዎችን በመላክ ያገኘችው ገቢ ማሽቆልቆሉ ያስደነገጣቸው የመንግስት ባለስልጣናት በዚህ እና በመጪዎቹ አመታት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የማግኘት እቅድ ነድፈው ነበር። ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያስገኛሉ ተብሎ ተስፋ ከተጣለባቸው ምርቶች አንዱ ቆዳና ሌጦ ቢሆንም ፣ ባለፉት 9 ወራት የተገኘው ውጤት ከአምናው ጋር ሲተያይ ከ20 በመቶ በላይ አሽቆልቁሏል።

በእቅዱ መሰረት 129 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለመሰብሰብ ታቅዶ ማግኘት የተቻለው 86.3 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነው። ለውጤት መቀነስ የቀረቡት ምክንያቶች የጥራት ማነስ፣የሀይል መቆራረጥ ፣ የቆዳ እጥረት እንዲሁም በቂ የሆነ ባለሞያ እና አማካሪ ድርጅቶች አለመኖር መሆናቸው ተጠቅሷል።
መንግስት በተለያዩ ዘርፎች እንዳጋጠሙት የፓሊሲ ክሽፈቶች ሁሉ በቆዳውም ዘርፍ የታየው ክሽፈት የስርአቱ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ፓሊሲ ውድቀት ማሳያ ነው በማለት የኢኮኖሚ ባለሞያው አቶ ኤድመን ተስፋዬ ተናግሯል፡፡ አቶ ኤድመን ከሀያ አምስት አመት የኢህአዴግ አገዛዝ በሁዋላም የሀገሪቷ የውጪ ንግድ ከቡና እና ቆዳ ባልተላቀቀበት በአሁኑ ወቅት የተሰማው ይህ ዜና የሀገሪቷ የውጪ ንግድ ሚዛን ምን ያህል እያሽቆለቆለ እንደሆነ የሚያሳይ ነው ብሎአል፡፡
የውጭ ምንዛሬ ገቢው እያሽቆለቆለ ቢሆንም፣ አገሪቱ አሁንም ከአለም የግል ባንኮች ወይም በአጠቃላይ መጠሪያቸው ዩሮ ቦንድ ገንዘብ መበደሯን ቀጥላለች።
እ.ኤ.አ ከ2010 እስከ 2015 ባሉት 5 ዓመታት ኢትዮጲያን ጨምሮ ዘጠኙ ከአፍሪካ ቀንድ በታች ያሉ አገራት ወደ 20 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ብድር መበደራቸውን ሰነዶች ያሳያሉ።

የአቶ አንዳርጋቸው የ9 ዓመት ልጅ በእንግሊዝ መንግስት ላይ ክስ አቀረበች

ግንቦት ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአሜሪካና የእንግሊዝ ዜግነትን አጣምራ የያዘችው ምናቤ አንዳርጋቸው የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ በሚከታተሉ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰራተኞች ላይ በጠበቃዎቹዋ አማካኝነት ክስ መስርታለች።

ላለፉት 2 ዓመታት በእስር ላይ የሚገኘው አቶ አንዳርጋቸው ከሁለት አመት በፊት በጣም ለአጭር ጊዜ ካደረገው የስክል ጥሪ በስተቀር ከቤተሰቡ ጋር እንዲገናኝ አልተፈቀደለትም ሲል ጉዳዩን የሚከታተለው ሪፕሪቭ የተባለው የህግ ባለሙያዎች ድርጅት አስታውቋል። አቶ አንዳርጋቸው ጠበቃ እንዳያገኝና ፍርድ ቤት እንዳይቀርብ መደረጉ ብቻ ሳይሆን፣ የእስር ቤት ባለስልጣናት በእጃቸው እንደሌለ እየገለጹ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል።
የተመድ የሰብአዊ መብት ካውንስል፣ የአውሮፓ ፓርላማ እንዲሁም የአሜሪካ የኮንግረስ አባላት አቶ አንዳርጋቸው እንዲፈቱ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወቃል።
ምናቤ አንዳርጋቸው ፣ አባቷ በህገወጥ መንገድ በየመን መንግስት ተላልፎ መሰጠቱን፣ ህገወጥ በሆነ ሁኔታ መታሰሩንና የሞት ፍርድ የተፈረደበት መሆኑን በመግለጽ፣ እንግሊዝ ከዚህ በፊት ለሌሎች ዜጎች ያደረገችውን ጥረት ለአባቷ መፈታት አላደረገችም በማለት ክስ ቅርባለች።
የሪፕሪቭ የሞት ቅጣት ቡድን ዳይሬክተር የሆኑት ማያ ፎአ፣ እንግሊዝ አቶ አንዳርጋቸው ከእስር ተለቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ ጥሪ ማድረግ አለባት፣ ዝምታው ማብቃት ይኖርበታል ብለዋል።

ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በማላዊ እስር ቤትና በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ በስቃይ ላይ ናቸው

ግንቦት ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አገር አቆራርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ በማላዊ መግቢያና መውጫ ድንበሮች አካባቢ የተያዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በእስር ቤትና በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ በስቃይ ላይ እንደሚገኙ ተዘገበ። ማላዊ በሚገኘው ዲዛካ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UNHCR) ስር ባሉት የመጠለያ ጣቢያዎች ካሉ 24 ሽህ ስደተኞች ሲኖሩ፣ ከእነዚህ መካከል በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ይገኙበታል ብሎአል።

በቂ የሆነ የምግብ አቅርቦት ባለመኖሩና በተፋፈገ ሁኔታ ውስጥ ለመኖር በመገዳዳቸው ስደተኞቹ ላይ የጤና ችግሮች ተከስቷል። በአገሪቱ ውስጥ ተዘዋውረው የመስራት እድል ለስደተኞቹ ባለመፈቀዱም አማራጭ አጥተው በስቃይ እንደሚኖሩና ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ ዘሜይል ኤንድ ዘጋርዳኢያን ዘግቧል። ከዋና ከተማዋ ሊንግ ዌ 45 ኪሎ ሜትር ከሚርቀው ዲዛካ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ለማምለጥ ሲሞክሩ 9 የኮንጎ ዲሞክራቲክ ዜጎች በፓሊስ ተይዘዋል።

Wednesday, May 25, 2016

የኢህአዴግ መንግስት ወታደራዊ ሃይሉን ለማጠናከር የጦር መሳሪያዎችን በብዛት እየሸመተ ነው

ግንቦት ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመከላከያ ሰነዶች እንደሚያመለክቱት ካለፉት 2 አመታት ጀምሮ የኢህአዴግ መንግስት ከፍተኛ የሆነ ወጪ በማውጣት የጦር መሳሪያዎችን እየገዛ ሲሆን፣ የጦር መሳሪያ ባለሙያዎችንም ወደ ቻይናና ሌሎች የምስራቅ አውሮፓ አገራት በመላክ እያሰለጠ ነው።

ሰነዶቹ እንደሚያስረዱት በሁለት አመታት ውስጥ መንግስት ለታንክ መግዢያ ብቻ ከ684ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ያደረገ ሲሆን፣ ለመድፎች 896 ሚሊዮን ብር፣ ለተሽከርካሪዎች ፣ ለተለያዩ ጠመንጃዎች፣ ለቦንቦችና ለመሳሰሉት ወታደራዊ ቁሳቁሶች ደግሞ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጓል። ይህ አሃዝ ከመስከረም 11፣ 2005 ዓም እስከ 2007 ዓም ያለውን ጊዜ ብቻ የሚመለከት ነው።
በብዛት የገቡት የጦር መሳሪያዎች ሩስያ ሰራሽ የሆኑ ቲ- 172 የሚባሉ ታንኮችና 122 ሚሊሜትር መድፎች ናቸው።

በምስራቅ ሃረርጌ “ ዘረኝነት በቃ!” ያሉ ቄሶች ተቀጡ

ግንቦት ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በምስራቅ ሀረርጌ ሃገረ ስብከት ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች የሚያገለግሉ ቄሶች ፣ “ዘረኝነት ይቁም፣ አድልዎ ይወገድ፣ የሁሉም ህዝብ መብት ይከበር!” የሚሉ መፈክሮችን በማንገብ የዲሞክራሲ የለውጥ እንቅስቃሴ ጀምራችሁዋል ተብሎው ደሞዛቸው እንዲቀነስ፣ ከደረጃም ዝቅ ብለው እንዲሰሩ ተወስኖባቸዋል።

እስካሁን በ16 ቀሳውስት ላይ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፣ እርምጃው በሌሎችም ላይ ሊቀጥል ይችላል ተብሎአል። እርምጃ የተወሰደባቸው ቀሳውስት ሁሉም ከጎጃም አካባቢ የመጡ የአማራ ተወላጆች ናቸው።

ዓለምአቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር እና የእንግሊዝ መንግስት ለድርቅ ተጎጂዎች እርዳታ አበረከቱ

ግንቦት ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በድርቁ የተጎዱትን ሰዎች ሕይወት ለመታደግ ዓለምአቀፉ ቀይ መስቀል ማኅበር 35 ሽህ ለሚሆኑ ቤተሰቦች የምግብ፣ የውሃ፣ የጤና አገልግሎት፣ የቤት እንስሳት እንክብካቤ፣ ለሕጻናት ምገባ መርሃ ግብር የሚውል 2.2 ሚሊዮን የስዊዘርላንድ ፍራክ መድቧል።

ለቀጣይ አምስት ዓመታት በሚዘልቀው የቤተሰብ ምገባ ፕሮግራም ማእቀፍ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ለአንድ ሰው በነፍስ ወከፍ 12.5 ኪሎ ግራም በቆሎ፣ አኩሪ አተር፣ ሁለት ሊትር የምግብ ዘይት እርዳታውን ማከፋፈል መጀመሩን ማኅበሩ አስታውቋል።

Tuesday, May 24, 2016

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ወልደ ጊዮርጊስ ከስልጣናቸው ተባረሩ

ኢሳት (ግንቦት 16 ፥ 2008)

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ወልደ ጊዮርጊስ ከስልጣናቸው ተባረሩ ፥ በምትካቸው አዲስ ሰው ተሹሟል። ባለቤታቸው በተመሳሳይ ከስራቸው ተነስተዋል።
የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት 2ኛ ሰው የሆኑት አቶ ኢሳያስ ወልደ ጊዮርጊስ በዚሁ መስሪያ ቤት ከሚሰሩት ባለቤታቸው ጋር ከስራና ከስልጣን ከመነሳታቸው በተጨማሪ፣ በፀጥታ ሃይሎች ክትትል ውስጥ መሆናቸውንም መረዳት ተችሏል።
አቶ ኢሳያስን ተክተው ስፍራውን የያዙት አቶ ሃደራ አበራ የተባሉ በዚሁ መስሪያ ቤት ውስጥ በሃላፊነት ስፍራ ላይ የነበሩ ግለሰብ መሆናቸውንም መረዳት ተችሏል።

ኢህአዴግ የአገሪቱ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች ግንቦት20ን እንዲያከብሩ እያስገደደ ነው

ግንቦት ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 25ኛ አመት የመንግስት ስልጣን የተቆጣጠረበትን በአሉን ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ለማክበር ያቀደው ኢህአዴግ፣ የመንግስት ሰራተኞች በሙሉ ስራቸውን እየተው በአሉን እንዲያደምቁ አዟል።

ትራንስፖርት ባለስልጣን፣ መንገዶች ባለስልጣን፣ ማሪታይም ጉዳይ ባለስልጣን፣ ትራንስፖርት ሚኒስቴር፣ ሲቪል አቪየሽን፣ ስትራቴጂክ መጠባበቂያ ምግብ ክምችት፣ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ፣ ብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር፣ ቤተ መንግስትን አስተዳዳር፣ ካርታ ስራዎች ድርጅትና ሌሎችም የፌደራል ተቋማት ሰራተኞች በተለያዩ ሆቴሎች እየተገኙ በአሉን እንዲያከብሩ ታዘዋል።

በአዲስ አበባ 44 የግል ኮሌጆች የአንድ ወር ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው

ግንቦት ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአ/አ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ በዘርፉ ትምህርትና ስልጠና ለመስጠት ፈቃድ የወሰዱና በራሳቸው ምክንያት ያቋረጡ 44 የግል ኮሌጆች የመጨረሻ የአንድ ወር ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

ኤጀንሲው በዛሬው እለት በመንግስታዊ መገናኛ ብዙሀን ባወጣው ማስታወቂያ የተዘጉትን 44 ያህል ኮሌጆች ዘርዝሮአል። እነዚህ ኮሌጆች ስልጠናቸውን አቋርጠው ተቋሞቻቸውን ሲዘጉ በገቡት ውልና ግዴታ መሰረት አስፈላጊ መረጃዎችንና ቁሳቁሶችን ለኤጀንሲው ማስረከብ ይጠበቅባቸው ነበር። ሆኖም ኮሌጆቹ ይህን ባለማድረጋቸው በተቋማቱ የሰለጠኑ ዜጎች መረጃዎቻቸውን ለማግኘት ከፍተኛ ውጣውረድ ገጥሞአቸዋል። ችግሩን ለመቅረፍ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ቀርበው ንብረትና መረጃዎችን ካለስረከቡ ተቋሙን ሲመሩ የነበሩ ሀላፊዎችን በጋራና በተናጠል በህግ እንጠይቃለን ብሎአል።
ከተዘጉት ተቋማት መካከል ኩኑዝ ኮሌጅ፣ ማውንት ፉዲ ኮሌጅ፣ አወልያ ፉዲ ኮሌጅ፣ ዜጋ ቢዝነስ ኮሌጅ፣ ዳንዲቦሩ ዩኒቨርስቲና ኢንተርናሽናል ሊደርሽፕ ኮሌጅ ይገኙበታል።

Monday, May 23, 2016

በአዲስ አበባ የመንግስት ባለስልጣናትን መኖሪያዎች የሚያሳዩ ተጨማሪ ቪዲዮች ቀረቡ ( ሪፖርታዥ )

ግንቦት ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ እና በመላው አገሪቱ በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች የኢህአዴግ ሹመኞች በራሳቸውና በዘመዶቻቸው ስም ያስገነቡዋቸው ህንጻዎች የህዝብ መነጋገሪያ አጀንዳ ከሆኑ ውለው አድረዋል። በተቃራኒው ጥረው ግረው የሰሩዋቸው ቤቶች ህገወጥ ተብለው ምንም አይነት ካሳ ሳይከፈላቸው ወይም ተገቢው መኖሪያ ቤት ሳይሰጣቸው በጎዳና ላይ ላስቲክ ዘርግተው የሚኖሩ ዜጎች እየተበራከቱ ነው።

ለባለሃብቶች በተሰጡ ሱቆች ዙሪያ በተደጋጋሚ የተነሱት ቅሬታወች ምላሽ አላገኙም፡፡

ግንቦት ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለወጣቶችና ስራ አጥ ወገኖች የሚዘጋጁ የመስሪያ ሱቅ ኮንቴይነሮች በባለ ሃብት እጅ በመገኘታቸው ዙሪያ የተነሱ ቅሬታዎች ምላሽ አለማገኘታቸውን በተለያዩ ከተማዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ለኢሳት አስታወቁ፡፡
ንግድ ፍቃድ የሌላቸው ፣በጥቃቅንና ኢንተርፕራይዝ ያልታቀፉ ነዋሪዎች የመስሪያ ሱቅ እየተሰጣቸው የሚሰሩበት ሁኔታ በግልጽ እየታየ የከተማ አስተዳደር ባለስልጣናት ርምጃ ከመውሰድ መቆጠባቸው አሳዛኝ መሆኑን ቅሬታ አቅራቢዎች ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያለው የፓለቲካ ምኅዳር መጥበቡንና የሰብዓዊ መብት ጥሰቱ መባባሱን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ

ግንቦት ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገራት ውስጥ ባደረገው ጥናታዊ ሪፓርት፣ በኢትዮጵ ውስጥ ያለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ እየከፋ መምጣቱን ጠቁሟል። ድርጅቱ በኢትዮጵያ የአንድ ፓርቲ የበላይነት መንገሱንና የፓለቲካ ምኅዳሩ መፈናፈኛ በሌለው ሁኔታ በአንባገነኑ ኢሕአዴግ ብቸኛ ቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል።

Friday, May 20, 2016

More killings reported as authorities continue demolishing houses for the second day

ESAT News (May 19, 2016)

Police kill at least eight people in Addis Ababa on Thursday as residents in the Bole sub section of the capital confronted police and a demolishing team that was tearing down houses for the second day today.

Flooding displaces over 230, 000 in Ethiopia

ESAT News (May 19, 2016)

Heavy rains and flooding have displaced about 230, 000 people from their homes in the last few weeks, according to a UN report.

Thursday, May 19, 2016

በኦሮምያ ህዝባዊው ተቃውሞው አገረሸ

ግንቦት ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለሳምንታት ጋብ ብሎ የነበረው የኦሮምያ ክልል ተቃውሞ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ መጠነኑን እያሰፋ በመምጣት ላይ ሲሆን፣ ዛሬ በምእራብ ሃረርጌ የማሳለ ከተማ ነዋሪዎች ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞ አሰምተዋል። ከሁለት ቀናት በፊት በአሰቦ ከተማ ተመሳሳይ ተቃውሞ የተካሄደ ሲሆን፣ ትናንት ምሽት ደግሞ በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ የፈደራል ፖሊሶች በተማሪዎች ላይ እርምጃ ወስደዋል። በርካታ ተማሪዎችም መጎዳታቸው ታወቋል።

በአዲስ አበባ ከቤት ፈረሳ ጋር በተያያዘ በተነሳው ተቃውሞ የሟቾች ቁጥር አሻቀበ

ግንቦት ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህገወጥ መንገድ ተገንብተዋል የተባሉትን ቤቶች ለማፍረስ ወደ ወረዳ 12 የተጓዙት አፍራሽ ግብረሃይሎች እና እነሱን የሚያጅቡዋቸው በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የፌደራል ፖሊሶች ከነዋሪዎች ያጋጠማቸውን ሰላማዊ ተቃውሞ፣ በጥይት ለመመለስ በወሰዱት እርምጃ ከ8 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን፣ ከ100 ያላነሱ ሰዎች ቆስለው ሆስፒታል መግባታቸውን የአይን እማኞች ለኢሳት ተናግረዋል።

የሼር ኩባንያ ገመና ይፋ ሆነ

ግንቦት ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሆላንዱ ሼር ኩባንያ በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁ የአበባ አምራጭ ኩባንያ ነው። ድርጅቱ በፈርንጆች አቆጣጠር በ2004 ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት 1 ሺ የእግር ኳስ ሜዳ በሚያክል መሬት ላይ የአበባ እርሻ ልማት ስራ ጀምሯል። ድርጅቱ በአመት 1 ቢሊዮን 200 ሚሊዮን የጽጌረዳ አበባ ወደ ሆላንድ ይልካል። አበባዎቹን ለማሳደግ ደግሞ በእያመቱ 2 ሺ የኦሎምፒክ የመዋኛ ገንዳ የሚሞላ ውሃ ይጠቀማል። በሊትር ሲሰላ ደግሞ 5 ቢሊዮን ሊትር ውሃ ይደርሳል።

በደቡብ ሱዳን የሃይል አዛዥ የሆኑት ሌ/ተ ጄ/ል ዮሃንስ ገብረመስቀል በኬንያዊው ጄኔራል ተተኩ

ግንቦት ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ባንኪ ሙን በደቡብ ሱዳን የሃይል አዛዥ የሆኑትን ሌ/ተ ጄ/ል ዮሃንስ ገብረመስቀል ተስፋማርያምን በኬኒያው ጄኔራል ጆንሰን ሞጎአ ኪማኒ መተካታቸው ታወቀ::
ሌተናት ጀነራል ዮሃንስ ላለፉት ሶስት አመታት በደቡብ ሱዳን ያገለገሉ ሲሆን በአብዬ ግዛት የሃይል አዛዝ ሆነው አገልግለዋል:: ኒወርክ ካለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚሰሩ ሰራተኞች ባደረሱን መረጃ ጄ/ል ዮሃንስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በደቡብ ሱዳን ማላካል (Malakal) በተባለ ቦታ በተፈጸመው የሲቪሊያን ግድያ ጦራቸው ግድያውን አልተከላከለም፣ አመራርም በብቃት አልሰጡም በሚል እሳቸውና ሰራተኞቻቸው ምርመራ ላይ እንደነበሩ ታውቋል::
በሌላም በኩል ከኢትዮጵያ ተመድበው የሚመጡ ሰራተኞች (Staff Officers) ና ወታደራዊ (Military Observers) እንግሊዘኛ ቋንቋ በደንብ አለመናገራቸው ከሌሎች ዜጎች ጋር ለመግባባት ችግር በመፍጠሩ ትችት ሲድርስባቸው ቆይቷል::
ሌ/ተ ጀኔራል ዮሃንስ ከኢታማጆር ሹሙ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ ጋር የማይግባቡ ሲሆን፣ ጄ/ል ሳሞራ በመተካካት ፖሊሲው ስም ስልጣን ሲለቁ፣ ጄ/ል ዮሃንስ ይተኩዋቸዋል ተብሎ ቢጠበቅም፣ በሁለቱ መካከል ባለው አለመግባባት፣ ጄኔራሉ ምናልባትም በጡረታ ሊገለሉ ይችላሉ ሲሉ ምንጮች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

Wednesday, May 18, 2016

በአዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ ከቤት መፍረስ ጋር በተያያዘ ሰዎች ተገደሉ

ግንቦት ፲(አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ወረገኑ በሚባለው ሰፈር በህገወጥ መንገድ ተሰርተዋል የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ወደ አካባቢው የሄዱት የአፍራሽ ግብረሃል አባላት እና የፌደራል ፖሊሶች ከነዋሪዎች ከፍተኛ ተቃውሞ ያጋጠማቸው ሲሆን፣ የፌደራል ፖሊሶች ጥይቶችን ወደ ሰዎች በቀጥታ በመተኮሳቸው በርካታ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። የአይን እማኞች እንደሚሉት ወታደሮቹ ህጻናትን ሳይቀሩ ገድለዋል። እስካሁን በደረሰን መረጃ ከ3 በላይ ሰዎች ሲገደሉ በርካቶችም ቆስለዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም ተይዘው ታስረዋል።

በአማራ ክልል በሚገኙ ከተሞች የሚታየው የውሃ ችግር ተባብሷል፡፡

ግንቦት ፲(አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጎንደር፣ በባህርዳር ፣ በሰቆጣ፣ በወልዲያ፣ በከሚሴ፣ በቻግኒ፣ በቡሬና በወረታ ከተሞች ከአሁን በፊት የነበረው የውሃ እጥረት ከዕለት ወደዕለት እየከፋ ቢሔድም ለጉዳዩ እልባት ለመስጠት የተንቀሳቀሰ የመንግስት አካል እንደሌለ ነዋሪዎች በተለይ ለኢሳት ተናግረዋል፡፡

የሚጠጣ ውሃ በመጥፋቱ ምክንያት የጉድጓድ ና የምንጭ ውሃ ለመጠቀም እንደተገደዱ የተናገሩት ነዋሪዎች ፤ምንም እንኳን የቧንቧ መስመር በቤታቸው ቢኖርም ውሃ የሚያገኙት ከሳምንት አንድ ቀን ለተወሰነ ሰዓት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በ570 ሚሊዮን ብር የተገዙ መድሃኒቶች ህዝብ ጋር ሳይደርሱ ሲባለሹ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድሃኒቶች ደግሞ ለአርሶ አደሮች ተሰራጩ

ግንቦት ፲(አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ትናንት ከሰአት በሁዋላ ከፓርላማ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት መልስ ፣ በመድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ የተገዙ 570 ሚሊዮን ብር ዋጋ የሚያወጡ መድሃኒቶች ለህዝብ ሳይከፋፈሉ የአግልገሎት ጊዜያቸው አልፎ ወይም ኤክስፓየር አድርጎ በመጋዝኖች ውስጥ መገኘታቸውን አጋልጠዋል። እንዲሁም በግብርና ማሳደጊያዎች አቅራቢ ድርጅት የተበላሹና የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ኬሚካሎች ለአርሶአደሩ መሸጣቸውን ያጋለጡ ሲሆን፣ የአንዳንድ መድሃኒቶች የመጠቀሚያ ጊዜ ካለፈ ከሁለት አመታት በላይ መሆኑን በመግልጽ፣ በአርሶአደሮች ሲቀርቡ የነበረውን አቤቱታ ትክክለኛነት አረጋገጥዋል።

በሃረሪ ብሄራዊ ሊግና በኦህዴድ መካከል ያለው ሽኩቻ ቀጥሎአል

ግንቦት ፲(አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሀረሪ ክልልን በሚመሩት የሃረሪ ብሄራዊ ሊግ ( ህብሊ) እና የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ( ኦህዴድ) መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ መሄዱን ተከትሎ አንዱ ድርጅት የሌላውን ድርጅት አባል ከስልጣን እያነሳ ነው። ሃብሊ ለሁለት ቀናት ባደረገው ግምገማም ድርጅቱ ከሁለት መከፈሉ በገሃድ የታዬ ሲሆን፣ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት የክልሉ ፕሬዚዳንት እንዲወርዱ የሚጠይቁና_የእሳቸው ደጋፊዎች እርስ በርስ ሲወነጃጀሉ ተሰምቷል።

በእርስበርስ ሽኩቻው የተዳከመ የሚመስለው ሃብሊ፣ ዛሬ ከ4 በላይ አመራሮቹ ከስልጣን ተወግደውበታል። የትምህርት ቢሮ ሃላፊው አቶ ሙክታር ሳላህ፣ የፕሬዚዳንቱ አጎት የሆኑት አፈ ጉባኤው አቶ ያሲን፣ የፕ/ቱ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ አቶ ካሊድ ሃባል ከስልጣን የተነሱ ሲሆን፣ የፕ/ቱ አማካሪና የጠባቂዎቻቸው ሃለፊ አቶ ባህሩ ደግሞ በፖሊሶች ቁጥጥር ስር ውለው ወደ እስር ቤት ተወስደዋል፤፡
የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን ለማስተናገድ የተመረጠችው ሃረሪ፣ በኦህዴድና በሃብሊ ባለስልጣናት ሽኩቻ ለወራት ስትናጥ ሰንብታለች።

በአሶሣ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ሰበብ የተፈናቀሉ 400 የአማራ ብሔር ተወላጆች ካለ ፍትሕ ከስድስት ዓመት በላይ እየተጉላሉ ነው

ግንቦት ፲(አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የሚኖሩ ቁጥራቸው ከ400 በላይ የሚሆኑ የአማራ ብሔር ተወላጆች ከነባር ይዞታቸው መፈናቀላቸውን አስመልክቶ ለአማራ ክልል ብሶታቸውን አሰምተዋል።

Ethiopian regime bans 14 political parties over administrative reasons

ESAT News (May 17, 2016)
The Ethiopian Electoral Board banned 14 political parties operating in the country over what it called administrative problems.
The 14 parties, banned effective May 13, 2016, include the Ethiopian Democratic Forces Union, led by veteran politician Dr. Beyene Petros, as well as several political parties representing the people of south Ethiopia, Afar, Somali and Harar.
The Board said the parties have failed to hold their general assembly and elect new leaders as per the bylaws of the parties.
The Board also said the parties have failed to submit their audit report as well as the physical locations of their head offices and branches to the Board.
With the elimination of the 14 political parties, the regime effectively wipe out any alternative political group and any semblance of alternative voice in the country.

The Auditor General says government offices fail to balance book in the amount of over 100 million dollars

ESAT News (May 17, 2016)
The Ethiopian Auditor General said of the 145 government offices audited, 94 have not balanced their book in the amount of over 100 million dollars while 77 offices were found to have made illegal purchases in the amount of over 27 million dollars.
Presenting his report to the parliament, the auditor general, Gemechu Dubiso said the Government Procurement Office, the Ministry of Education, the Electoral Board and the Ministry of Defense, among others, were the main government offices that have not balanced their book in the said amount.
He said a number of universities, health institutions, industries, and the Ministry of Transport have made illegal purchases amounting to 27 million dollars.
In addition, six offices have made payments in the amount of over 1 million dollars without the proper documentation

የታሰረው አካሌ እንጂ ልቤ ቀይ ባሕርን ተሸግሮ ከጓዶቼ ጋር በኤርትራ በረሃ ነው !

ከእየሩሳሌም ተስፋው (ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት)


 ይህንን ደብዳቤ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት በግንቦት 7፣ 2008 እንዲታተም ያወጣችው ቢሆንም፤ በተለያዩ እንቅፋቶች በዕለቱ ለሕዝብ ሳይደርስላት ቀርቷል፡፡)

ይህቺ ቀን ከዛሬ 11 ዓመት በፊት በ1997 ዓ.ም. በዕለተ እሁድ ኢትዮጵያ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምፁን ለመረጠው ፓርቲ ሊሰጥ የተሰለፈበት ዕለት ነበረች፡፡ ሕወሓት/ኢሕአዴግ እስቲ እንያቸው ምን ያመጣሉ በማለት ከዛ በፊትም ከዛ በኋላም ተደርጎ በማይታወቅ ሁኔታ የምርጫ ምኅዳሩን ገርበብ አድርጎ ከፍቶ በሩን አልፈው እንዲገቡ ፈቀደላቸው፡፡

Tuesday, May 17, 2016

በማጀቴ ከተማ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

ግንቦት ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ሸዋ ዞን በአንጾኪያ ገምዛ ወረዳ የሚገኙ የማጀቴ ንኡስ ወረዳ ነዋሪዎች የገምዛ ወረዳ ይመለስልን በሚል የጀመሩት ተቃውሞ እየሰፋ መሄዱን ተከትሎ የመንግስት አመራሮችና ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወደ ዋናው ከተማ ሄደዋል።

ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ያልተወራረደ ሂሳብና ከ540 ሚሊዮን ብር በላይ ህገወጥ ግዢ መፈጸሙን ጄኔራል ኦዲተር አስታወቀ

ግንቦት ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌዴራል ዋና ኦዲተር ገመቹ ዱቢሶ የ2007 በጀት አመት ኦዲት ካደረጋቸው 145 የመንግስት መ/ቤቶች መካከል 94 ያህሉ ከ 2 ቢሊየን ብር በላይ ሂሳባቸውን በወቅቱ ሳያወራርዱ የተገኙ ሲሆን ፣ 77 መ/ቤቶች ደግሞ ከ546 ሚሊየን ብር በላይ ከህግ ውጪ ግዥ ፈጽመው መገኘታቸውን ይፋ አድርገዋል።

ዋና ኦዲተሩ በዛሬው እለት ለፖርላማ ባቀረቡት የ2007 በጀት አመት ሪፖርት 2 ቢሊዮን 78 ሚሊዮን 949 ሺ 440 ብር ከ60 ሳንቲም ያልተወራረደ ገንዘብ መኖሩን ገልጾ፣ ሂሳባቸውን ካላወራረዱት መካከል የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ 342 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር፣ ትምህርት ሚ/ር 315 ሚሊዮን 1 መቶ ሺ ብር፣ ምርጫ ቦርድ 172 ሚሊዮን 1 መቶ ሺ ብር፣ መከላከያ ሚ/ር 139 ሚሊዮን 2 ሺ ብር ይገኙበታል።
የግዥ አዋጅ ደንብና መመሪያ ከሚፈቅደው ውጪ ግዥ ፈጽመዋል በሚል በዋና ኦዲተር ሪፖርት ከቀረበባቸው ተቋማት መካከል ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ 161 ነጥብ 3 ሚሊየን፣ አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆ/ል 81 ሚሊየን፣ ደ/ማርቆስ የኒቨርሲቲ 45 ሚሊየን፣ ዲላ ዩኒቨርሲቲ 33 ሚሊየን፣ የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ኢንደስትሪ ልማት ኢንስቲትዪት 26 ሚሊየን፣ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ 25 ሚሊየን፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 20 ሚሊየን፣ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ 18 ሚሊየን፣ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ 17 ሚሊየን፣ ትራንስፖርት ሚ/ር 15 ሚሊየን ብር ተጠቅሰዋል። በተጨማሪም 6 መ/ቤቶች ያለውል ሰነድ 22 ሚሊየን ብር ክፍያ ፈጽመው መገኘታቸውን ዋና ኦዲተሩ አጋልጦአል።

በሃረር እና ደሴ ከተሞች ከሚፈርሱ ቤቶች ጋር በተያያዘ በርካታ ቤተሰቦች ለችግር ተዳርገዋል

ግንቦት ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ በላይነህ ተስፋዬ የተባሉ የሃረሪ ክልል ምክር ቤት አባል እና ባለሃብት፣ ህዳር 29፣ 2009 ዓም ለሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች በአል በአምስት ወራት ውስጥ 75 ሆቴሎችን እገነባለሁ በሚል ከ30 በላይ መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ድርጅቶችን እንደፈርሱ በማስደረጋቸው ከ300 ያላነሱ ዜጎች ችግር ላይ መውደቃቸውን ወኪላችን ከስፍራው ዘግቧል። የአንዳንድ ነጋዴዎች የንግድ ድርጅቶች ከ 30 እና 40 አመታትን ያስቆጠሩ ሲሆን፣ ነጋዴዎቹ ነባር ይዞታቸውን ለማልማት ቦታቸውን በሊዝ ገዝተው ግንባታ ለመጀመር እንቅስቃሴ ላይ ነበሩ።

ምርጫ ቦርድ የዶ/ር በየነ ጴጥሮስን ኢዴሃህን ጨምሮ 14 ፓርቲዎችን ከግንቦት 5 ቀን ጀምሮ መሰረዙን አስታወቀ

ግንቦት ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከቦርዱ የተሰጠው መግለጫ እንደሚያመለክተው ፓርቲዎቹ በመተዳደሪያ ደንባቸዉ መሠረት ጠቅላላ ጉባኤ የሚያካሂዱበት ጊዜ ያለፈ በመሆኑና የሥራ ጊዜያቸው በተጠናቀቀው አመራሮች ምትክ አዲስ የአመራር አባላትን መርጦ ወዲያውኑ ለቦርዱ ባለማሳወቃቸው፣ በኦዲተር የተረጋገጠና በግንባሩ መሪ የተፈረመ የሃብትና እዳ ሰነድ የጽሑፍ ሪፖርት ባለማቅረባቸው፣ ፓርቲው ያለውን ዋና ጽሕፈት ቤት እና ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች አድራሻ፣ የጽሕፈት ቤቶቹን ኃላፊዎች ወይም ተወካዮች ለቦርዱ በጽሑጽ ባለማሳወቅ፣ እንዲሁም በሚመለከተው ሕጋዊ አካል የተረጋገጠ የሞያ ብቃት ያለው በፓርቲው የተሾመ የውጭ ኦዲተርና የተሾመው ኦዲተር ሹመቱን መቀበሉን በፊርማው ያረጋገጠበት ሰነድ ባለማቅረባቸው ፓርቲዎቹ መሰረዛቸውን ጠቅሷል።

አዲስ አጭር መረጃ ስለታላቁ የነጻነት ታጋይ አንዳርጋቸዉ ጽጌ!!

ከልዑል ዓለሜ
በመላዉ ኢትዮጵያዊያን ልቦና ዉስጥ ሰርጾ መግባት የቻለና የማይበርድ የትግል ምእራፍን በመንደፍ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ነጻነትን የቀለመ አባት ነዉ ! እ.ኤ.አ በግንቦት ወር /2014 የየመን ዋና ከተማ ሰናአ ላይ ተሰወረ! የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን ለወንበሬ ያሰጋኛል ብሎ በጠላትነት የተነሳበት የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ ክቡር አንዳርጋቸዉ ጽጌ በግፍ ለወንጀለኛዉ የወያኔ ቡድን ተላልፈዉ ተሰጡ!

ነጻነት ላያንቀላፋና ነጻነት ላይታሰር አንድነትና ኢትዮጵያዊነትን በጫንቃዉ ተሸክሞ በማረፊያዉ ወቅትና ሰአት የጎረመሰዉ አባት አንዳርጋቸዉ ጽጌ ብዙሃንን አፍርቷል!! ዛሬ የፍሬዉ ትሩፋቶች አደራቸዉን ተቀብለዉ ሐገራቸዉንና ትዉልዳቸዉን ለመታደግ ዳር በደረሱበት ወቅት ወያኔያዉያን ግን ታላቁን አባት ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ላይ ይገኛሉ! ከሰሞኑ በደረሰን መረጃ መሰረት የተከበሩት የነጻነት አባት ክቡር አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ የፌደራል ፖሊስ ህንጻ ስር ምድር ቤት ዉስጥ ( underground ) ክፍል ዉስጥ መወሰዳቸዉን የሚያረጋግጡ ሲሆን የብሔራዊ መረጃ ምንጮቻችን በበኩላቸዉ ሌሎች ተጨማሪ ግለሰቦች በዚያዉ በፌደራል ፖሊስ የምድር ቤት ብቸኛ ክፍል ዉስጥ ከታላቁ የነጻነት አባት ጋር እንደሚገኙ ፍንጭ ሰጥተዋል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

Monday, May 16, 2016

በደንቢያ የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጅ መምህራን አድማ እንደቀጠለ ነው

ግንቦት ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደንቢያ ወረዳ በቆላድባ ከተማ የሚገኘው የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጅ መምህራን ባለፈው አርብ የጀመሩትን አድማ በመቀጠላቸው ተማሪዎች ወደ ቤታቸው መመለሳቸው ታውቋል። የወረዳው ባለስልጣናት አድማውን ከሚያደርጉ መምህራን ጋር ለመነጋገር ያደረጉት ሙከራ ፣ መምህራኑ ባሳዩት ጠንካራ አቋም ምክንያት አልተሳካም።

የአድማው መነሻ ኮሌጁን ሲያስተዳድሩ የነበሩት መምህር ሙሉ አበበ እና ምክትላቸው ሰይድ ካሴ ከሃላፊነታቸው በመነሳታቸው ነው። መምህራኑ “የመብት ጥያቄ አንስተናል ጥያቄያችን ካልተመለሰ ስራ አንጀምርም” የሚል ጠንካራ አቋም የያዙ ሲሆን፣ ተማሪዎችም ለመምህራን ድጋፋቸውን እየሰጡ ነው።

አሸዋ ሜዳ በሚባለው አካባቢ የተገነቡት የኮንዶሚኒዬም ቤቶች ሙሉ በሙሉ ለኢህአዴግ ካድሬዎች ተሰጡ

ግንቦት ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እሁድ ግንቦት7፣ 2008 ዓም በኦሮምያ ልዩ ዞን ወደ አምቦ መስመር መውጫ አሻዋ ሜዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የተገነቡት የኮንዶሚኒየም ቤቶች ሙሉ በሙሉ ለኢህአዴግ ባለስልጣናትና ካድሬዎች መሰጠቱን ወኪላችን ገልጿል። ቤቶቹ ከተገነቡ ብዙ አመታትን ማስቆጠራቸውን የገለጸው ወኪላችን፣ በቅርቡ በተካሄደው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ቆጠራ ይህ አካባቢ መተላለፉን ምንጮችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። እነዚሁ የመንግስት ባለስልጣናትና ካድሬዎች የተሰጣቸውን ቤት ከ2 እስከ 3ሺ ብር እያከራዩ ተጨማሪ ገቢ ያገኛሉ።

ባለፈው ሳምንት የከተማ ቤቶችና ልማት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያው ሃይሌ በቅርቡ በተደረገው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ቆጠራ 4 177 ቤቶች ጥቅም ላይ ሳይውሉ መገኘታቸውን የተናገሩ ሲሆን፣ 286 የኢህአዴግ ባለስልጣናት የተሰጣቸውን ቤቶች ለሶስተኛ ወገን አከራይተው ገቢ እያገኙ መሆኑን ተናግረዋል።

በርካታ ወታደሮች የኢህአዴግን መንግስትን በመክዳት ወደ ትጥቅ ትግሉ መቀላቀላቸውን የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ይፋ አደረገ።

ግንቦት ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትህዴን ባወጣው መግለጫ ከድተው ወደ ድርጅቱ ከተቀላቀሉት መካከል የ14ቱን የትውልድ ቦታ፣ ስም፣ የነበሩበትን ክፍለ ጦር፣ ሬጅመንትና ሻምበል በዝርዝር አመልክቷል።

ከከዱት መካከል አንዳንዶቹ ማዕረግ ያላቸው ሲሆኑ፤ ማ ዕረግ የሌላቸው በርካታ ወታደሮችም ይገኙበታል።

በአማራ ክልል የሳንቲም እጥረት ተፈጠረ

ግንቦት ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ዘጋቢያችን እንደገለጸው በተለይ በክልሉ ዋና ከተማ ባህርዳር የአንድ ብር ሳንቲም እጥረት በመከሰቱ ታክሲዎች ፣ ደንበኞቻቸውን ከማሳፈራቸው በፊት ጥያቄያቸው “ ዝርዝር ሳንቲም ይዘሃል ?” የሚል ሆኗል። ለተፈጠረው የሳንቲም እጥረት ትክክለኛ ምክንያቱን ለማወቅ ባይቻልም፣ ባለፈው አመት መጋቢት ወር ድምጻችን ይሰማ የጠራው የሳንቲም መሰብሰብ ሰላማዊ የተቃውሞ ማእቀብ ውጤት ሊሆን እንደሚችል አንዳንድ ነዋሪዎች አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።

አሜሪካ ተጨማሪ 128 ሚሊዮን ዶላር የሰብዓዊ ዕርዳታ አደረገች

ግንቦት ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (USAID) እንዳስታወቀው የሰብዓዊ ድጋፉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በ50 ዓመታት ውስጥ አስከፊ የተባለውን ድርቅ እንዲቋቋም ለማገዝ ነው።

በአሁኑ ወቅት አብዛኛው ሕዝብ ረሃቡን መቋቋም ከሚችለው በላይ እንደሆነበት የገለጸው ተራድኦ ድርጅቱ፣ የዛሬው ተጨማሪ ድጋፍ የሰብዓዊ ምግብ ዕርዳታ፣ የንጹህ መጠጥ ውኃ፣ የተመጣጠነ ምግብ አገልግሎትና ተንቀሳቃሽ የጤና ቡድንን ያካተተ ወሳኝ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ ያስችላል ብሎአል።
የዲሞክራሲ ፣ የግጭትና የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ ተጠባባቂ ረዳት አስተዳዳሪ ቶማስ ኢች ስቶል “ይህ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ የአሜሪካ መንግሥት ድርቁ ወደ ብሔራዊ የሰብዓዊ ቀውስ ደረጃ እንዳይሸጋገር “ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል።
የአሁኑን እርዳታ ጨምሮ የአሜሪካ መንግሥት እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 2014 ጀምሮ በአጠቃላይ የ705 ሚሊዮን ዶላር ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።
የሆላንድ መንግስትም የ 3 ሚሊዮን ዩሮ እርዳታ ማድረጉን የአገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ታላቁ የስፓርት አባት ዶ/ር ወ/መስቀል ኮስትሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ግንቦት ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ የሩጫ ታሪክ ሲነሳ ስማቸው በጉልህ ከሚጠሩት የመስኩ ባለሙያዎች አንዱ የሆኑት ዶ/ር ወ/መስቀል ኮስትሬ በተወለዱ በስድሳ ስድስት ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ዶክተር ወልደመሰቅል ኮስትሬ በሸዋ ክፍለሃገር ተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ሳሊት እንግዳ ዋሻ በተባለ ቦታ በ1942 ዓ.ም.ተወለዱ። ትምህርታቸውን አዲስ አበባ በመምጣት በደጃዝማች ወንድይራድ ትምህርት ቤት በኮተቤ የመምህራን ኮሌጅ ወደ ባሕር ማዶ በማቅናትም በሃንጋሪ የስፓርት ሳይንስ የተማሩ ሲሆን ድጋሚም ወደ ሃንጋሪ በማቅናት የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል።

Saturday, May 14, 2016

Government squanders 8 million dollars a month due to a corrupt contractor

ESAT News (May 13, 2016)

The Ethiopian government pays 8 million dollars a month to employees of sugar factories even when the construction of these factories have not yet been completed and none of the factories have begun production due to a corrupt contractor with direct ties to the government.

Friday, May 13, 2016

በዲላ ከተማ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መንገድ ዘግተው ፈተሻ ሲያደርጉ ዋሉ


ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጡት፣ የመከላከያ ስራዊት አባላትና የፌደራል ፖሊስ አባላት መንገዶችን ዘግተው ፍተሻ ሲያደርጉ እንዲሁም በመኪና ላይ ሆነው ቅኝት በማድረግና የሚጠርጥሩዋቸውን ወጣቶችም ይዘው ሲጠይቁ መዋላቸውን ተናግረዋል። ወታደራዊ ፍተሻውና ቅኝቱ፣ በመንግስት ታጣቂዎችና በአርበኞች ግንቦት 7 መካከል በአርባምንጭ አካባቢ የተፈጠረውን ጦርነት ተከትሎ የተካሄድ ሊሆን እንደሚችል ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ፍተሻውን እና ጥበቃውን በተመለከተ በአካባቢው ያሉ ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

በዶ/ር ቴዎድሮስ ሲመራ የነበረው ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከግሎባል ፈንድ የተሰጠውን ገንዘብ ከስምምነት ውጪ መጠቀሙና ማጉደሉ ተገለጠ


ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጤና ጠበቃ ሚኒስቴርን መርተው ለውጤት እንዳበቁት በመግለጥ ፣ የአለም የጤና ድርጅት መሪ ለመሆን የቅስቅሳ ስራ የጀመሩት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ ኤች አይ ቪ ኤድስንና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ለመዋጋት በሚል ከግሎባል ፈንድ ለህዝብ የተሰጠውን ገንዘብ ከስምምነት ውጭ ለሌሎች አላማዎች መጠቀማቸውን የሚያመለክት የኦዲት ሪፖርት ቀርቦባችዋል።
ግሎባል ፈንድ በአውሮፓውያን አቆጣጥር በ2010 ፣ 1 ቢሊዮን 3 መቶ ሚሊዮን 35 ሺ 989 ብር ለግሶአል። ጄኔቭ የሚገኘው በምህጻረ ቃሉ GFATM የተባለው የኦዲት ተቁዋም፣ የኢትዮጰያ መንግስት ገንዘቡን ከስምምነት ውጭ እየተጠመበት መሆኑን ጥቆማ ከደረሰው በሁዋላ ባደርገው ማጣራት፣ በ88 ጉዳዮች ላይ ችግሮችን ማግኘቱን በፈንጆች አቆጣጠር ኢፕሪል 19,2012 ባወጣው ሪፖርት አስታውቆአል።
የመጀመሪያው የኦዲት ሪፖርት ከመወጣቱ በፊት ዶ/ር ቴዎድሮስ እንዲያዩት ከተላከላቸው በሁዋላ ተቃውሞ በማሰማታችው ሪፖርቱ በወቅቱ በተያዘለት ቀን ይፋ እንዳይደረግ ተደርጎአል።
ግሎባል ፈንድ ለጤና ተቁዋማት ግንባታ በሚል 24 ሚሊዮን 196 ሺ 552 ዶላር መድቦ 1 ሺ 309 የጤና ተቁዋማት የተገነቡ ቢሆንም፣ መንግስት ለመድሃኒት መግዢያ የተመደበልትን ገንዘብ ወደ ግንባታ አዙሬዋለሁ በሚል ሪፖርት በማድረጉ 57 ሚሊዮን 851 ሺ 941 ብር በላይ ገንዘብ ከስምምነት ውጭ መጠቀሙንና የድርጅቱ ኦዲተሮችም የጤና ትቁዋማቱን ደረጃ ካዩ በሁዋላ መንግስት ያቀረበውን ምክንያት ሳይቀበሉት ቀርተዋል።
ኦዲተሮች ባደርጉት የመስክ ጉብኝት 165 ሚሊዮን 393 ሺ 27 ዶላር ከወጣባቸው የጤና ተቁዋማት መካከል 71 በመቶ የጤና ትቁዋማት ውሃ የሌላቸው ሲሆን፣ 32 በመቶው ደግሞ ሽንት ቤት የላቸውም። 53 በመቶው ግንባታቸው ከመጠናቀቁ ወለላቸው ተሰነጣጠቁዋል፤ 19 በመቶው ደግሞ ጣራቸው ያፈሳል። 14 በመቶው ብቻ ማይክሮስኮፕ እና የማዋለጃ አልጋዎች ያላቸው ሲሆን፣ 12 በመቶው ብቻ ትክክለኛ የመድሃኒት አቅርቦት አላቸው።
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በሂሳብ ሪፖርቱ 11 ሚሊዮን ዶላር ውጪ ማውጣቱን ቢገልጥም፣ ገንዘቡ ለምን ለምን እንደወጣ ዘርዝሮ ማቅረብ ባለመቻሉ ገንዘቡ እንደተበላ ተቆጥሮ ፣ ኦዲተሮች ገንዘቡ ለግሎባል ፈንድ እንዲመለስለት ጠይቀዋል።
እንዲሁም 7 ሚሊዮን 26 ሺ 929 ዶላር በግልጥ ጎድሎ በመገኘቱ መንግስት ገንዘቡን ለግሎባል ፈንድ እንዲመልስ ኦዲተሮች በሪፖርታቸው ጠቅሰዋል።
ሪፖርቱ የአለም ጤና ድርጅት መሪ ለመሆን ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ላሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አደጋን ይዞ መምጣቱን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታትሉ ሰዎች ይናገራሉ።

በካራሚሌ 4 ሴቶች በወታደሮች ተደፍረው ሆስፒታል ገቡ


ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ ሃረርጌ ሰሞኑን የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ከምስራቅ እዝ የተላኩት ወታደሮች 5 ውጣት ሴቶችን አስገድደው መድፈራቸውንና ጉዳተኞችም ሆስፒታል መተኛታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። አንድ የ 7ኛ ክፍል ተማሪ በ4 ወታደሮች በቡድን በመደፈሩዋ ለህይወት አስጊ በሆነ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
በከተማው ያለው ወጥረትም እንዳለ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ በርካታ ስዎች ተይዘው ታስረዋል። በከተማዋ ተነስቶ በነበረው ተቃውሞ የፖሊስ አባላትን ጨምሮ 3 የመንግስት ደጋፊዎች መገደላቸው ይታወቃል።

በደንቢያ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ መምህራን አድማ አደረጉ

ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መምህራኑ ዛሬ ከጠዋቱ 4 ሰአት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ያደርጉ ሲሆን፣ መንግስትን የሚያውግዙ መፈክሮችን ሲያሰሙ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል።
አድማውን ትከትሎ ትምህርት በመቁዋርጡ ተማሪዎች ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ ተደርጎአል።
ባድማው የተሳትፉ መምህራንን ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም፣ ከሰአት በሁዋላ ወደ ስብሰባ በመግባታቸው ሳይሳካልን ቀርቶአል። መምህራኑ መብታችን ሳይከብር ስራ አንጀምርም ማለታቸውን ተማሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል።

በጄኒራል ክንፈ ዳኘው የሚመራው ሜቴክ የአባይ ግድብ ግንባታን በሶስተኛ ኩባንያ እያሰራ ነው


ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ77 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ተከፍሎት ከ10 የስኳር ኮርፖሬሽን ፋብሪካዎች መካከል አንዱንም ማጠናቀቅ ያልቻለው የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ለአባይ ግድብ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራውን ለመስራት ኮንትራት ቢወስድም፣ ሰራውን መስራት ባለመቻሉ የውጭ ኮንትራክተር ቀጥሮ እያሰራ ነው። የውጭ ኩባንያዎች በአማካሪ ስም ቢቀጠሩም ዋናውን ስራ የሚሰሩት እነሱ ናቸው።
አዳማ የእርሻ መሳሪያዎች ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ አዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ፣ አቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ፣ ቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ፣ የኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ማሽነሪ ንኡስ ኢንዱስትሪ፣ ደጀን አቪየሺን ኢንደስትሪ፣ ኢትዮ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ፣ ጋፋት አርማመንት ኢንዱስትሪ፣ ሃይቴክ ኢንዱስትሪ፣ ህብረት ማኑፋክቸሪንግ እና ማሽን ግንባታ ኢንዲስትሪ፣ ሆሚቾ አሙኔሽንና ኬሚካል ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ፣ የብረታብረት ፋብሪኬሽን ኢንዱስትሪ፣ ኢትዮጵያ ፓወር ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ፣ የነዳጅና ፕሮፒላንት ንኡስ ኢንዱስትሪ፣ የኳሊቲ ኢንጂነሪንግ ማእከል፣ የሎኮሞቲቭ ንኡስ ኢንዱስትሪ የተባሉ በቀድሞ መንግስት የተገነቡ ኢንዱስትሪዎችንና አዳዲሶችንም ጨምሮ የሚያስተዳድረው ሜቴክ “እየተሳሳትንም እንማራለን” በሚል መርህ ከፍተኛ የህዝብ ገንዘብ እያባከነና ለሙስናው እንደ እንደ ሽፋን እየተጠቀመበት ነው።
ግንባታው የተጓተተው የያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ የሜቴክ ውጤት ሲሆን ፣ በተጨማሪም የባቡር ሎኮሞቲቮችን መገጣጠም፣ የከተማ አውቶብሶችን፣ የቤት መኪኖች፣ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች መስራት፣ ሞባይልና ቴሌቪዥን መገጣጠም የሚሉ ሰራዎች ሳይቀር ለመስራት ኮንትራት ቢወስድም፣ በምርት ጥራትና በመለዋወጫ አቅርቦት በኩል ከባድ ችግሮች እየፈጠረ መሆኑን ድርጅቱን በቅርብ የሚያዉቁ ሰዎች ይናግራሉ። በየመንገዱ የሚቆሙት በሜቴክ የተገጣጠሙት የከተማ አውቶብሶች በቂ መለዋወጫ ከድርጅቱ ሊቀርብላቸው ባለመቻሉ አብዛኛዎቹ ለመቆም በመገደላቸው ባለቤቶቻቸውን ለኪሳራ ዳርገዋል።

በዛንቢያ 41 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ተፈረደባቸው


ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሊዋንጉዋ ማጀስትሬ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በትናንትናው እለት በዋለው ችሎት በሕገወጥ መንገድ ወደ ዛንቢያ ገብተዋል ባላቸው 41 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ የፍርድ ውሳኔ አሳልፏል።
ፍርድ ቤቱ የአገሪቱን የሕገወጥ ስደተኞች ሕግ አንቀጽን በመጥቀስ እያንዳንዳቸው ስደተኞች 1 ሽህ 500 የዛንቢያ ክዋቻ እንዲከፍሉ ወይም የሶስት ወራት ጽኑ እስራት ይታሰሩ ዘንድ የፍርድ ብያኔውን ሰጥቷል። በሕገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት በዝንባብዌ አድርገው ድንበር አቆራርጠው የሚገቡ ሕገወጥ ስደተኞች ዝውውር ተባብሶ መቀጠሉንና ይህንን ፍልሰት ለመግታት ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለማሳለፍ መገደዱን ገልጸዋል። ስደተኞቹ በሚያዙበት ወቅት አንዱ ለማምለጥ ሲሞክር ጉዳት ሲደርስበት ሌላኛው ደግሞ በአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞበት ጉዳት እንደደረሰበትና ሁለቱም ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በካቶንዲዌይ ሚሽን ሆስፒታል ውስጥ ሕክምናቸው በመከታተል ላይ እንደሚገኙ የድንበር ፓሊስ ቃል አቀባይ አስታውቀዋል። የዛንቢያ የስደተኞች ጉዳይ ኃላፊ በበኩላቸው ሕገወጥ ስደተኞችን የሚያዘዋውር አንድ የአገሪቱን ዜጋ መያዛቸውንና የሕገወጥ ስደተኞች ቁጥጥርን አጠናክረው እንደሚቀጥሉበት ማስታወቃቸውን ሉሳካ ታይምስ አክሎ አስታውቋል።
በተጨማሪም በደቡብ አፍሪካ ሴንትፍራንሲስ ከተማ የሚገኝ አንድ ኢትዮጵያዊ ባለ ሱቅ ላይ ጥቃት ተፈጽሞበታል። በቡድን የተደራጁ ዘራፊዎች ኤፍሬም ማዴቦ የተባለ የ27 ዓመት ኢትዮጵያዊን ደብድበው መግደላቸውንና በሌሎች ኢትዮጵያዊና ስደተኞች ሱቆች ላይ ዘረፋ መፈጸሙን የአገሪቱን ፓሊስ ጠቅሶ ግራውንድ አፕ ዘግቧል።

“ለነፃነታችን መሞት ካለብን ገድለን እንሞታለን !!!” የአርበኞች ግንቦት 7 ወታደራዊ መግለጫ

 ግንቦት 3 ቀን 2008 ዓ.ም.
በደቡብ ኢትዮጵያ ከሚገኘው የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይል ውስጥ በአርባ ምንጭ አካባቢ የሚንቀሳቀሰው አንድ ቡድን ፋሽስታዊው የህወሓት አገዛዝ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት የመከላከል እርምጃ ወስዷል።

Thursday, May 12, 2016

በአርባምንጭ አካባቢ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ላይ ለተፈጸመው ጥቃት አርበኞች ግንቦት7 ሃላፊነቱን ወሰደ

ግንቦት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አርበኞች ግንቦት 7 ለኢሳት በላከው ወታደራዊ መግለጫ ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ከሚገኘው የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይል ውስጥ በአርባ ምንጭ አካባቢ የሚንቀሳቀሰው አንድ ቡድን ከሚያዝያ 29 ቀን እስከ ግንቦት 1 ቀን ባደረገው የመረረ ፍልሚያ ከሃያ በላይ የጠላት ወታደሮችን ገድሎ ከሃምሳ ያላነሱትን ማቁሰሉንና በጦርነቱም ከአርበኞች ግንቦት 7 ወገንም መስዋዕትነት ተከፍሎአል ብሎአል።

በሃረሪ ክልል በኦህዴድና በሃብሊ መካከል ውጥረት ተፈጥሯል

ግንቦት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን እንደገለጸው፣ ክልሉን በሚያስተዳድሩት በኦህዴድና በሃረር ብሄራዊ ሊግ ፓርቲዎች መካከል የተፈጠረው ውጥረት በሃረር ከተማ ዙሪያ ከተገኑበት ቤቶች ጋር የተያያዘ ነው።

በአማራ ክልል ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ መዝነቡ ድርቁን ለመከላከል እንደማያግዝ ተነገረ፡፡

ግንቦት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ አማራ በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ሰሞኑን በመጣል ላይ ያለው ዝናብ ተጠቅመው ልዩልዩ ዘሮችን ቢዘሩም ዝናቡ ወቅቱን ያልጠበቀ በመሆኑ ቡቃያው በሚፈልገው መጠን ፍሬ ሊያፈራ የሚችልበትን የዝናብ መጠን እያገኘ እንዳልሆነና የድርቅ አደጋውን ለመከላከል እንደማያግዛቸው ተጎጂ አርሶአደሮች ተናግረዋል፡፡

ከእስር በተለቀቁት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ክስ ተመሰረተ

ግንቦት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክስ ዝርዝሩ እንደሚያሳየው 15 ተማሪዎች ፣ “በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሴኔት ህግ አንቀጽ 177. ቁጥር 2 ንጹስ ቁጥር .15 መሰረት ከሚመለከተው የዩኒቨርስቲው ዲን ፈቃድ ሳያገኙ በቀን 08/04/ 2007 ዓም በግምት ከቀኑ 7 ሰአት ሲሆን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6 ኪሎ ካምፓስ ውስጥ በተደረገ ሰልፍ እያወቁ የተካፈሉ በመሆኑ በፈጸሙት የተከለከሉ ስብሰባዎች ላይ መካፈል ወንጀል “ ተከሰዋል።

Wednesday, May 11, 2016

በኢትዮጵያ የተሰከሰተው ድርቅ በህጻናት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያደረሰ ነው ተባለ

ኢሳት (ግንቦት 3 ፥ 2008)

በኢትዮጵያ በተከሰተው ከፍተኛ የዝናብ እጥረት የህጻናትን ህይወት ለአደጋ እያጋለጠ መገኘቱን   ዩኒሴፍ አስታወቀ።የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጀት UNICEF ይህንን ያስታወቀው በሳምንቱ መጀመሪያ በድረ ገጹ ላይ ባቀረበው ዘገባ ሲሆን፣ህጻናቱም ሆነ ቤተሰቦቻቸው ችግሩን ለመቋቋም ቀዬያቸውን ጥለው ለመሰደድ መገደዳቸውንም አስፍሯል።

በባሌ ዞን የጎርፍ አደጋ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

ኢሳት (ግንቦት 3 ፥ 2008)

ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን ለተከታታይ ቀናት የዘነበውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተው ጎርፍ፣ ቁጥሩ  ያልታወቀ የሰው ህይወት ማለፉና ከአንድ ሺ በላይ የሚሆኑ የቀንድ ከብቶች በጎርፉ መወሰዳቸው ተገለጸ ።  በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ ኣብርሃም ሃይሌ APA ለተሰኘው የዜና አውታር  ማክሰኞ እንደገለጹት፣ ጎርፉ ቁጥራቸው እስካሁን ያልታወቀ የሰዎችን ህይወት አጥፍቷል፣ በ559 ሄክታር ማሳ ላይ የነበረውን አዝመራ ሙሉ በሙሉ አውድሟል።

በአርባምንጭ የነጭ ሳር ፓርክ አካባቢ በተደረገው ጦርነት ከ20 ያላነሱ የመንግስት ታጣቂዎች ተገደሉ

ግንቦት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ታማኝ ምንጮች እንደገለጹት ታጣቂዎቹ ባደረሱት ድንገተኛ ጥቃት 20 የመንግስት ወታደሮች ሲገደሉ፣ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል። ከተገደሉት መካከል የአካባቢው ወታደራዊ አዛዥም ይገኝበታል። የተኩስ ልውውጡ ለረጅም ሰአታት የቀዬ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች፣ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ የመንግስት ታጣቂዎች ወደ ህክምና ተወስደዋል።

ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ያልተወራረደና የተበላሸ ሂሳብ ያለው ንግድ ባንክ ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ወጪ ማውጣቱ ታወቀ

ግንቦት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለኢሳት የደረሰው የባንኩ የውስጥ ኦዲት ሪፖርት እንደሚያሳየው በበጀት አመት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2013 እና 2014 ባንኩ ያላወራረደው 11 በሊዮን ብር እንዲሁም የተበላሸ ገንዘቡ 1 ቢሊዮን ብር ቢደርስም፣ የባንኩ ባለስልጣናት ከተመደበላቸው መደበኛ በጀት ውጭ 729 ሚሊዮን ብር አውጥተዋል። “ሙስናን በመዋጋት አገራችንን ከዘላለማዊ ከእዳ እንታደግ “ በሚል የባንኩ ሰራተኞች የውስጥ እንቅስቃሴ የጀመሩ ሲሆን፣ ከመንግስት ባለስልጣናትና ከህወሃት ታዋቂ ባለሀብቶች ጋር ከፍተኛ የጥቅም ቁርኝት የፈጠሩት የንግድ ባንኩ ስራ አስኪያጅ፣ ባንኩንና አገሪቱን ለከፍተኛ እዳ እየዳረጉዋት ነው ይላሉ።

በመከላከያ አዛዦች የሚመራው ሜቴክ አገሪቱን ለከፍተኛ እዳ እየዘፈቃት ነው ተባለ

ግንቦት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህወሃቱ ጄኔራል ክንፈ ዳኘው የሚመራውና በአንድ ወቅት አቶ መለስ ዜናዊ “የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ እድገት አቅጣጫ የሚቀይስ ተቋም” ብለው ያሞካሹት በመከላከያ ስር የሚገኘው የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ( ሜቴክ) በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገነቡ ፕሮጀክቶች መጓተት እንዲሁም በማህበራዊ አገልግሎት ዘርፍ ለሚታዩ ችግሮች ዋና ተጠያቂ መሆኑን የመንግስት ባለስልጣናት መናገር ጀምረዋል። ይሁን እንጅ የሜቴክ አመራሮችን ደፍሮ የሚጠይቃቸው በመጥፋቱ፣ አገሪቱ ዋጋ እንድትከፍል እየተደረገ ነው።

መንግስት ቤቶችን ስርቶ ለማስረከብ የገባውን ቃል ማክበር ሳይችል ቀረ

ግንቦት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ160 ሺ በላይ ህዝብ በየወሩ እየቆጠበ ከዛሬ ነገ ቤት አገኛለሁ በሚል እየተጠባበቀ የሚገኘውን 40 በ60 ተብሎ የሚታወቀው የቤቶች ፕሮጀክት ትክክለኛ የማስተላለፊያ ጊዜ መቼ እንደሆነ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ሀይሌ አለመናገራቸው ቆጣቢዎችን አስቆጥቷል።

Monday, May 9, 2016

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያልተወራረደና የተበላሸ ብድሩ ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል።

ሚያዚያ ፩(ግንቦት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በየአመቱ በሚያወጣቸው የሂሳብ አያያዝ መግለጫዎቹ ከፍተኛ ትርፍ እንዳገኘ ሲናገር የቆዬው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2006 እና 2007 ዓም ባሉት 2 ዓመታት ብቻ 11 ቢሊዮን 273 ሚሊዮን ብር ያላወራረደው ገንዘብ ሲኖር፣ 1 ቢሊዮን 300 ሚሊዮን ብር ደግሞ የተበለሻ ብድር እንዳለው ሰነዶች አመለከቱ።

በአውሮፓውያን አቆጣጠር እስከ ሰኔ 30፣ 2014 ድረስ የተለያዩ የድርጅቱ ቅርንጫፍ ባንኮች 3 ቢሊዮን 590 ሚሊዮን ከ30 ሳንቲም ፣ በ2013 ደግሞ 6 ቢሊዮን 956 ሚሊዮን ከ20 ሳንቲም ያላወራረዱት ገንዘብ መኖሩን ከንግድ ባንኩ ሰራተኞች የተገኘው የሂሳብ መዝገብ ያሳያል።
ብድር ወስደው መክፈል ያልቻሉት ድርጅቶችና ብድራቸው በተበላሸ ብድር መዝገብ ከሰፈሩት መካከል፣ ሳይጀን ዲማ ቴክስታይል ፋብሪካ 437 ሚሊዮን ብር፣ ሙሉነህ ካካ ላኪ ድርጅት 94.2 ሚሊዮን ብር፣ አኪር ግንባታ 87.1 ሚሊዮን ብር፣ ካራቱሬ እርሻ ደርጅት 55.3 ሚሊዮን ብር፣ ባዘን እርሻ እና ኢንዱስትሪ ልማት የግል ማህበር 42.1 ሚሊዮን ብር፣ የጌታ ትሬዲንግ 39.3 ሚሊዮን ብር፣ ማሜ ብረታብረት ፋብሪካ 39.2 ሚሊዮን ብር፣ የገነት ላኪና 62 ሚሊዮን ብር፣ ሸበሌ ትራነስፖርት 17.2 ሚሊዮን ብር፣ ፍጹም ዘአብ አስገዶም 14.2 ሚሊዮን ብር ቤድፋም ኢንተርናሽናል 21 ሚሊዮን ብር ይገኙበታል።
ባንኩ በ2013/14 በጀት አመት 17.2 ቢሊዮን ብር እንዳተረፈ ቢገልጽም፣ የባንኩ ሰራተኞች እንደሚሉት ግን የተበላሸው ብድርና ያልተወረራደው ገንዘብ ግምት ውስጥ ሲገባ ባንኩ ያተረፈው ከ5 ቢሊዮን ብር አይበልጥም።

አቶ ዳንኤል ሺበሺና የሽዋስ አሰፋ ተፈቱ


ሚያዚያ ፩(ግንቦት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምርጫ 2007ትን ተከትሎ በሽብርተኝነት የተከሰሱት የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሃላፊና የደቡብ ተወካይ አቶ ዳንኤል ሽበሺ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ም/ል ሰብሳቢ አቶ የሺዋስ አሰፋ የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው ተፈተዋል።
አቶ ዳንኤልና አቶ የሽዋስ ነሃሴ 14 ቀን 2007 ዓ•ም ፍርድ ቤት ነጻ ቢላቸውም፣ በችሎት መድፈር በተላለፈባቸው ውሳኔ እስከዛሬ በእስር እንዲቆዩ ተደርጓል። በተመሳሳይ ወንጀል የተከሰው አቶ አብርሃ ደስታም ከሁለት ወራት በሁዋላ ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል።

ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት መረጃ በማቀበል ወንጀል ተከሰሱ


ሚያዚያ ፩(ግንቦት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራሉ አቃቤ ህግ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14ኛ ወንጀል ችሎት ምክትል አስር አለቃ አጃናው ታደሰና ምክትል አስር አለቃ ቻሌ ነጋ ላይ ለአርበኞች ግንቦት7 ወታደራዊ መረጃዎችን ሲያቀብሉ ነበር የሚል ክስ ተከፍቶባቸዋል።
ሁለቱ ተከሳሾች 6ኛ እና 25ኛ ክፍለ ጦር ስር የሚገኙ ሬጅመንቶችን ብዛት እና መገኛ ቦታ በስልክና በቫይበር ማስተላለፋቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።
ተከሳሾቹ የአገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር የገቡትን ቃል ኪዳን ወደ ኋላ በመተውና የአርበኞች ግንቦት ሰባት ድርጅትን ተልዕኮ በመቀበል፣ የመከላከያ ሠራዊትን አደረጃጀትና የሚገኝበትን አድራሻ መረጃ አሳልፈው በመስጠት፣ ከድርጅቱ ታጣቂዎች ጋር ለመቀላቀልና የድርጅቱ ተስፋ በመሆን በሽብር ወንጀል መከሰሳቸው ተዘግቧል። ፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ለማዬት ግንቦት 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የማላዊ መንግስት ያሰራቸውን ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የሚያስችል ገንዘብ ማጣቱ ተዘገበ።

ሚያዚያ ፩(ግንቦት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዘ ሰን ዴይ ታይምስ እንደዘገበው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2015 ያለህጋዊ ወረቀት ወደ ማላዊ የገቡ 40 የሚሆኑ ህጻናት ኢትዮጵያውያን በሉሊዌንጌ በሚገኘው የካቸረ ጂቬኒለ እስር ቤት ታስረው ይገኛሉ።
ኢትዮጵያውያኑ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚያደርሷቸው ቃል የገቡላቸው የህገ- ወጥ አሻጋሪዎችና ደላሎች ተጠቂዎች መሆናቸውን ጋዜጣው ጠቅሷል።
ማላዊ በክፍለ አህጉሩ ከአንድ ሀገር ወደ ሌላ ሀገር ለሚደረጉ እንዲህ ያሉ እንቅስቃሴዎች እንደ መሻገሪያ እንደምታገለግል ይታመናል። ይሁንና የማላዊ መንግስት በገንዘብ እጥረት ሳቢያ ኢትዮጵያውያኑን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እንደተቸገረ ተገልጿል።
ኢትዮጵያውያኑን በአየር ትራንስፓርት ወደ ሀገራቸው ለመመለስ 16 ሺህ ዶላር ያስፈልጋል።ህጻናቱ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ ካላቸው ፍላጎት በመነሳት በራሳቸው መንገድ ከኢትዮጵያ ኬንያ፣ከኬንያ ታንዛኒያ ከገቡ በኋላ በህገ ወጥ አሻጋሪዎቹ ይወሰዳሉ።
ይሁንና እንደ ጋዜጣው ዘገባ፤ ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ቢያዙም፤ ህገ ወጥ አሻጋሪዎቹ ተሰውረዋል። አልፎ አልፎ አንዳንድ ህገወጥ አሻጋሪዎች የፍርድ ቤት ቅጣታቸውን ከጨረሱ በኋላ በተመሣሳይ መንገድ ህገ ወጥ ስደተኞች ሊያሻግሩ ሲሉ ድንበር ላይ የተያዙበት አጋጣሚ እንዳለ ተመልክቷል።
በማላዊ የሰብ ዓዊ መብት ኮሚሽን የህጻናት መብት ጥበቃ ዳይሬክተር ኖሪስ ችርዋ በህገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊሄዱ ሲሉ የተያዙት ህጻናት የተጣለባቸውን ቅጣት እንደፈጸሙ ተናግረዋል።
“የህጻናቱ ቤተሰቦች ልጆቻቸው ደቡብ አፍሪካ እንዲሄዱላቸው ያላቸውን ዕቃ እየሸጡ ከ2ሺህ እስከ 4 ሺህ ዶላር ይከፍላሉ፤ አንዳንዶቹ እንደ ሁኔታው ማላዊ ለመግባት ብቻ እስከ አንድ ዓመት ይፈጅባቸዋል።” ብለዋል ዳይሬክተሯ።
ህጻናቱ ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ እስኪላኩ ድረስ በሰብዓዊ መብት ኮሚሽኑ የህጻናት ጉዳይ ግምገማ ቦርድ ጊዜያዊ መጠለያ እያፈላለገላቸው እንደሆነ ዳይሬክተሯ ገልጸዋል። “የመንግስት ፍላጎት ህጻናቱ ቅጣታቸውን እንደጨረሱ ወደ ትውልድ ሀገራቸው መላክ ነበር;ይህን ለማድረግ ግን ገንዘብ አልተገኘም።መንግስት ከዚህም በላይ በሌሎች ሀገራት እንደሚደረገው ሁሉ ህገ ወጥ ስደተኞችን በወህኒ ከማቆየት ውጪ ለእነሱ የሚሆን የተለየ መጠለያ አላስገነባም።ለዚህም ነው ህጻናቱ በካቻረ ወህኒ ቤት እንዲቆዩ የተደረገው”ብለዋል- ኖሪስ ችርዋ።
የዓለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት የማላዊ ኃላፊ ስቲፈን ትሮቸር ባለፈው መስከረም በማላዊ እስር ቤት ለሚታየው አስጨናቂ ሁኔታ የረዥም ጊዜ መፍትሄ እንዲፈለግለት አሣስበው ነበር።
“ከአስር ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ታሳሪዎች መካከል አንዱ ህጻን የመሆኑ ነገር እጅግ ይረብሸናል፤ ህገ ወጥ ስደት ህጻናቱን ለበሽታ፣ለጉልበት ብዝበዛ ፣ለአደጋና ለእስር እያጋለጣቸው ነው።የተጨናነቁት የማላዊ እስር ቤቶች ለዚህ ምስክሮች ናቸው።” ብለዋል- ስቲፈን።
በህገ ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት የሚፈልጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በየ ዓመቱ ህይወታቸውን አደጋ ላይ እየጣሉ እንደሆነ የሰን ዴይ ታይምስ ዘገባ ያመለክታል። ማላዊ፦”የትራንስፖርት ገንዘብ ስለሌለኝ ወደ ሀገራቸው ልመልሳቸው አልቻልኩም” ባለቻቸውና በእስር እየተሰቃዩ በሚገኙት ህጻናት ኢትዮጵያውያን ዙሪያ እስካሁን የኢትዮጵያ መንግስት የሰጠው አስተያዬት የለም። ይልቁንም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ለልማት ገንዘብ ለማሰባሰብ በሚል ኢትዮጵያውያን በስደት ወደሚገኙባቸው ሀገራት በመሄድ ስብሰባ እያደረጉ ይገኛሉ።
በሌላ ዜና ደግሞ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲያቀኑ የነበሩ 34 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዛንቢያ የድንበር ፓሊስ አስታውቋል። ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በሕገወጥ መንገድ መነሻቸውን ታንዛኒያ በማድረግ የዛንቤዚን ወንዝ ተከትለው ወደ ዝንባብዌ አቆራርጠው ሲገቡ በናኮንዳ ድንበር አቅራቢያ ተይዘዋል።
በፓሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ውስጥ አንዱ በአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞበታል። የድንበር ፓሊስ ቃል አቀባይ የሆኑት ሙላታ እንዳሉት ከሆነ ጉዳተኛው ኢትዮጵያዊ የሕክምና እርዳታ እየተደረገለት መሆኑንም አስረድተዋል።
ባለፈው ወርም 19 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ተይዘው አንድ ሽህ የዛንቢያ ክዋቻ ወይም የስድስት ወር እስራት እንደተፈረባቸው ሉሳካ ታይም ዘግቧል።
የገዥው ፓርቲ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ ታአምራዊ የምጣኔ ሃብት እድገት አምጥታለች እያሉ በመገናኛ ብዙሃን ዘወትር ቢናገሩም ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ግን ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው በአራቱም ማእዘናት መፍለሳቸውን ቀጥለዋል። እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ መንግስት ኤንባሲም ሆነ ቆንስላ በኩል በእስር ላይ ያሉትን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ጉዳይ የሚከታተል አልተገኘም።

Saturday, May 7, 2016

ኢትዮጵያውያን በየመንና ሶሪያ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ ሆነው እንኳን ወደ ሃገራቸው መመለስ እንዳማይፈልጉ ተገለጸ


ኢሳት (ሚያዚያ 28 ፥ 2008)
በመካከለኛው ምስራቅ በችግር ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያዋውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን CAJ news Africa የተሰኘ ጋዜጣ ዘገበ። ባለፈው መጋቢት ወር ብቻ በጦርነት በምትናጠው ሶሪያ ችግር ውስጥ የነበሩ ከ1220 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ታውቋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚታየው ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ለመላቀቅ ወደመካከለኛው ምስራቅ አገሮች የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ መሄዱንም መረዳት ተችሏል።
ኢትዮጵያውያኑ ለህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ዳጎስ ያለ ገንዘብ በመክፈል ወደ የመንና ሱዳን እንደሚጓዙም ታውቋል። ሆኖም ህገወጥ አዘዋዋሪዎቹ ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን ለሌሎች ህገወጥ አዘዋዋሪዎች አሳልፈው እንደሚሰጡና እነዚሁ ህገወጥ አዘዋዋሪዎችም ተጨማሪ ገንዘብ ለመቀበል ሲሉ በስደተኞች ኢትዮጵያውያን አካል ላይ ጉዳት እንደሚያደርሱና ለረጅም ጊዜ እንደሚያስሯቸው ለማወቅ ተችሏል።
ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለው ወደ የመን የገቡት ኢትዮጵያውያን ስደተኞችም ወደፈለጉት አካባቢ እንዲሄዱ እንደሚለቀቁና፣ ገንዘብ መክፈል ካልቻሉ ግን ጀበል ወደሚባል ቦታ ተወስደው በአስከፊ ሁኔታ እንደሚቀመጡም CAJ news Africa የተባለው ጋዜጣ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ከስፍራው ዘግቧል።
የመን፣ ሶሪያ፣ ሶማሊያ የመሳሰሉ አገራት በጦርነት እየታመሱ ባለበት ሰዓት እንኳን አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን በየመን ያለውን ጦርነትና፣ የሚደርስባቸውን ግፍ እንደምንም ሳይቆጥሩ አካባቢውን አቋርጠው ወደሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ለመድረስ ጥረት እንደሚያደርጉ ይኸው CAJ news Africa የተባለው ጋዜጣ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ መንግስት በቡና ነጋዴዎች ላይ እስከ 5 አመት ድረስ የሚያስቀጣ አዲስ መመሪያ ተግባራዊ አደረገ


ኢሳት (ሚያዚያ 28 ፥ 2008)
የኢትዮጵያ መንግስት ከቡና ንግድ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለማሳደግና በቡና ነጋዴዎች ላይ እስከ 5 አመት እስራትን የሚያስቀጣ አዲስ የቁጥጥር መመሪያን ተግባራዊ አደረገ።
በሃገሪቱ በቡና ንግድ ላይ ተስማርተው የሚገኙ አካላት ደረጃቸውን ካልጠበቁና ካልተሰባበሩ ቡናዎች በስተቀር ሁሉንም ምርቶቻቸውን ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንዳለባቸው መመሪያው ማስገዱዱን ዘ-ዎል ስትሪት የተሰኘ ጋዜጣ ዘጓል።
አዲሱን መመሪያ ተግባራዊ በማያደርጉ ቡና ነጋዴዎች ላይም ከ40ሺ ብር በላይ የገንዘብ ቅጣትና እስከ አምስት አመት የሚደርስ የእስር ቅጣት ሊተላለፍ እንደሚችል የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ልማት ባለስልጣን በመመሪያው ደንግጓል።
ይሁንና፣ በቡና ንግድ ላይ ተስማርተው የሚገኙ አካላት የአለም የቡና ዋጋ በመቀነሱ ምክንያት ምርታቸውንለሃገር ውስጥ ገበያ ቢያቀርቡ የተሻለ ዋጋን ሊያገኙ እንደሚችሉ በመግለጽ በመመሪያው ላይ ያላቸውን ቅሬታ ገልጸዋል።
የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው ከቡና ንግድ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ ለማሳደግ ሲባል አዲሱ የቁጥጥር መመሪያ ተግባራዊ መደረጉን  ለጋዜጣው በሰጡት ምላሽ አስረድተዋል።
በተያዘው የፈረንጆች አመት ሃገሪቱ ከቡና ንግድ ወደ 800 ሚሊዮን ዶላር ገቢን ለማግኘው እቅድ የያዘች ሲሆን፣ እቅዱም ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ13 በመቶ ብልጫ እንዳለው ታውቋል።
በአለም የቡና ምርት ላይ የታየው የአስር በመቶ የዋጋ ቅናሽ ኢትዮጵያን ጨምሮ በብራዚልና በሌሎች የቡና አቅራቢ ሃገራት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሮ የሚገኝ እንደሆነም ዘዎል ስትሪት ጆርናል ጋዜጣ በዘገባው አመልክቷል።
የዓለም ዋነኛ የቡና ላኪ ሃገር የሆነችው ብራዚል የመገበያያ ገንዘብ ከዶላር ጋር ያለው የመግዛት አቅም በቅርቡ በ30 በመቶ መቀነሱ የለም የቡና ዋጋ እንዲቀንስ ማድረጉንም ለመረዳት ተችሏል።
ይህም የዋጋ መቀነስ በኢትዮጵያ ላይ ተፅዕኖን ያሳደረ ሲሆን መንግስት ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና በመላክ ገቢውን ለማካካስ ጥረትን እያደረገ እንደሆነም የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች አስረድተዋል።
በሃገሪቱ ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ በዚሁ የግብርና ምርት ላይ የራሱን አሉታዊ ጎን እንደሚያሳድርም ባለሙያዎች ይገልጻሉ።