(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
በላይ አርማጭሆ ትክል ድንጋይ ይጠቃለሉ የነበሩ 8 ቀበሌዎች ወደ ታች አርማጭሆ በመከለላቸው ከ700 በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቀሉ፡፡
ከቅኝ ገዥዎች በወረሰው የከፋፍለህ ግዛው መርህ አገሪቱን ለመምራት እየሞከረ የሚገኘው የህወሓት አገዛዝ የስልጣን እድሜውን ለመቀጠል በማለም የኢትዮጵያን ህዝብ እንደ ተራራ የገዘፉ የጋራ ማንነቶችና እሴቶች በመግደፍ ጤፍ፣ ጤፍ የሚያካክሉ ልዩነቶች ላይ በማተኮርና በማጉላት በህዝብ አንድነትና ህብረት ላይ አሉታዊ ሚና ሲጫወት ሩብ ምዕተ ዓመት ሊሞላው ሁለት ወራት ብቻ ቀርተውታል፡፡ በመሆኑም የጎንደር ህዝብ እርስበርሱ ጎራ ለይቶ እንዲሰላለፍ ለማድረግ ያልተቋረጠ ጥረትና ሙከራ ያደረገ ሲሆን ከዚህም አልፎ ሰሞኑን የቅማንትና የአማራ ምድር በሚል መሬት እየሸነሸነ በአንድ ማህበረሰብ መካከል ድንበር ማበጀት ጀምሯል፡፡
በላይ አርማጭሆ ትክል ድንጋይ ይጠቃለሉ የነበሩት አይኳ ጫቅርን፣ ከች ከንፈንታ፣ ወርቅ ምድር፣ ሌዳሆ፣ ገንበራ፣ ዳዚሆን፣ ማሂን እና መሬና ባጠቃላይ ስምንት ቀበሌዎች ወደ ታች አርማጭሆ ሳንጃ በአገዛዙ ተዕዛዝ ተከልለዋል፡፡
የእነዚህ ቀበሌዎች ነዋሪዎች የሆኑ ትክል ድንጋይ ይማሩ የነበሩ ከ700 በላይ ተማሪዎች ሁለተኛውን ወሰነ ተምህርት አዲስ ወደ ተከለሉበት ታች አርማጭሆ እንጂ በትክል ድንጋይ መማር እንደማይችሉ ተነግሯቸው ከትምህርታቸው ተስተጓጉለዋል፡፡
ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ በአገዛዙ የተመደቡት በሙሴ ባምብ ከተማ ነው፡፡
በሙሴ ባምብ የሚገኘው ትምህርት ቤት አይደለም ከሌላ አካባቢ የተፈናቀሉ ከ700 ተማሪዎች በላይ ቀርቶ የአካባቢውን ተማሪዎችም መሸከም የሚችል አቅም እንደሌለው ታውቋል ስለዚህም ተማሪዎች በመጉላላት ላይ ናቸው፡፡
ሙሴ ባምብ ከዚህ ቀደም በላይ አርማጭሆ ወረዳ ስር የቆየች ከተማ ስትሆን አሁን ደግሞ በታች አርማጭሆ ንዑስ ወረዳ ለማድረግ አገዛዙ ውሳኔ ላይ መድረሱ ታውቋል፡፡ አሁን በሙሴ ባምብ ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ውድነት ተከስቷል፡፡ የቤት ኪራይ ዋጋ ከአቅም በላይ ከመሆኑ ባሻገር እጥረትም ተፈጥሯል፡፡

No comments:
Post a Comment