ኢሳት (የካቲት 22 ፥ 2008)
በእስራዔል ከአንድ ኢትዮጵያዊ ሞት ጋር በተያያዘ ሲካሄድ የነበረ የወንጀል ምርመራ ኣንዲቋረጥ መደረግን ተከትሎ በእየሩሳሌም የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ማክሰኞ ምሽት ተቃውሞ አደረጉ።
በከተማዋ በሚገኘው የፖሊስ ዋና ጽ/ቤት ከተጀመረው ተቃውሞ በተገናኘ ስምንት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የእስራዔል መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
የሃገሪቱ ፖሊስ በፀጥታ ሃይሎች በደል ተፈጽሞበት ራሱን ባጠፋው ዮሴፍ ሳላምሳ ላይ ሲያካሄድ የነበረውን የወንጀል ምርመራ ምክንያቱ ባልታወቀ መንገድ ማቋረጡ ታውቋል።
ይሁንና፣ የምርመራው መቋረጥን ውሳኔ ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ማህበረሰ አባላት ማክሰኞ ምሽት ተቃውሞ መጀመራቸውን ሃርቴዝ ጋዜጣ አስነብቧል።
ተቃውሞው ወደሁከት መለወጡን የገለጸው የእስራዔል ፖሊስ በበኩሉ ሰልፈኞች ቁሳቁሶችን በፀጥታ ሃይሎች ላይ መወርወር እንደጀመሩና ስምንቱ ሰዎች ሊታሰሩ መቻላቸውን አስታውቋል።
በሃገሪቱ የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተእስራዔላውያን የዘር መድሎ ይፈጸምብናል በማለት በተደጋጋሚ መክሰሳቸው ይታወሳል።
ከቀናት በፊት የእስራኤል መንግስት ከበጀት ጋር በተያየዘ ነው በሚል ዘጠኝ ሺ ቤተ እስራዔላውያንን ለማጓጓዝ ያያዘውን እቅድ እንዲዘገይ ማድረጉን መዘገባችን ይታወቃል።
የሃገሪቱ መንግስት ለእቅዱ መራዘም የገንዘብ እጥረትን ምክንያት ቢያደርግም በርካታ ቤተ-እስራዔላውያን እርምጃው ከዘር ጥላቻ ጋር በተያያዘ ነው ሲሉ ተቃውሞን እያቀረቡ ይገኛል።
No comments:
Post a Comment