የካቲት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአስተዳደር ጋር በተያያዘ የኮንሶ ህዝብ ያነሳውን ጥያቄ ተከትሎ በአካባቢው የሚታየው ውጥረት የቀጠለ ሲሆን፣ በደቤና ቀበሌ አቶ ሷይታ ጋራ የተባሉ ሰው በአካባቢው በሰፈሩት ፖሊሶች ተገድለዋል። ትምህርት ቤቶች አሁንም እንደተዘጉ ሲሆን፣በርካታ ሰዎችም ታስረዋል።ባለፈው ቅዳሜ የአካባቢው ህዝብ ከአርባምንጭ ጂንካ የሚወስደውን መንገድ በመዝጋት ተቃውሞውን የገለጸ ሲሆን፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት መንገዱን በመክፈት በርካታ ቁጥር ያላቸው ወታደሮችን አንቀሳቀስዋል።
የህዝቡን ጥያቄ ለመንግስት ሲያቀርቡ በነበሩ 12 የአገር ሽማግሌዎች ላይም ክትትሉ ቀጥሎአል።የአካባቢው ህዝብ በሽማግሌዎች ላይ አንድ እርምጃ ከተወሰደ፣ አጸፋዊ እርምጃ እንወስዳለን በማለት እያስጠነቀቀ ነው። ከህዝብ ጎን ቆመዋል የተባሉ የወረዳው አመራሮች መታሰራቸውን መዘገባችን ይታወቃል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአካባቢው ያለው ውጥረት እየጨመረ በመምጣቱ ሰራተኞቹ እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአካባቢው ያለው ውጥረት እየጨመረ በመምጣቱ ሰራተኞቹ እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል።
No comments:
Post a Comment